ልጥፎች

ነገረ ዛለአንበሳ፤ ነገረ አልበሽር እና ዕድምታው

ምስል
ነገረ የዛለአንበሳ         እና       ዕድምታው እንደ ሥርጉተ ዕይታ። „ብዙ መከራ የተቀበለ ሰው ብዙ ትምህርት ይማራል።“ መጽሐፈ ሲራክ ፴፩ ቁጥር ፲፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.01.2019 ከእማ ዝምታ - ተሲዊዝ ። ·        እንደ መግቢያ። እንዴት አላችሁልኝ ቅኖቹ። ዝምታው ቀጥሏል። እሰከ ረፋዱ ድረስ የመኪና ጩኸት እንኳን አልሰማሁም። ኳኳ - ኳኳ  አደረኩኝ - በቀስታ፤ ደወሉን አልጫንም። በእጄ ነው እማንኳኳው። ጉዳዬ ለጎረቤቶቼ አላችሁን ልል ነው እገረ መንገዴንም እንኳን አደረሳችሁ ልል? „አለን ደህና ነሽ ግቢ“ አሉኝ። ልጆች አሉን ስል ቀጥዬ ጠዬቅሁኝ። እነሱ ረበሹሽ ይሉኛል እዬተሳቀቁ እኔ ደግሞ የቤተ ክርስትያን ማህሌት የመስማት ያህል ደስ ይለኛል ልጆች ሲጫወቱ ሳዳመጥ። ልጆቼ ናቸው አትሳቀቀሙ እላቸዋለሁኝ - አዘውትሬ። ጥያቄዬ ቀጠለ ትላንት ነበራችሁ? „ቤት ውስጥ ነበርን። ምናው አንኳኩተሽ ነበርን፤ አልሰማነሽም አሉኝ“ ሲሉ ጠዬቁኝ። ቀልጠፍ ብዬ አላንኳኳሁም ድምፃችሁ ስለጠፋብኝ ነው። „የስልክ ደወል እንኳን አለሰማሁም አልኳቸው።“ የእማ ዝምታ ነገር ሰውንም አደበኛ ነው እምታደርገው አብሶ እንዲህ የዓውዳ ዓመት ሰሞናት ጭር ነው። ዝጉም ሁለት ቀን። ዛሬም ጥር 2 ቀን 2019 ነው ሥራ የለም በገዳማዊቷ ሰፈር ከሆስፒታል እና ከድንገተኛ ክሊንኮች በሰተቀር ሱቁ ሁሉ ዝግ ነው።  ·        ጉዳይ - ለማዕልቲ። ዛሬ እንደ ጉዳይ እማነሳ...

ምርጫ ለዋንጫ ወይንስ ...

ምስል
ምርጫ ለዋንጫ ወይንስ ለመበላለጫ ወይንስ ለመፋ ጠ ጫ ወይንሰ ለ ር ጋ ወይንስ ለርቱ -በሰላም ግቡ? „እግዚአብሄርን የምትፈራ ሰውነት የተደነቀች ናት።“ መጸሐፈ ሲራክ ፴፩ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie  01.01.2019 ከእመ ዝምታ - ከሲዊዝ። ·        ጠ ብታ። ቅኖቹ እንዴት አደራችሁ? በዚህች ቅጽበት እኔ በምኖርበት ገዳማዊ ከተማ ነፍስ በዓዋጅ ጸጥ እንዲል የታወጀ ይመስላል። ኮሽ አይሏ ባዕት ከተፈጥሯዋ በላይ በድርብ ላይ ትገኛለች። ጸጥ፤ ረጭ፤ ዝም። መኪና እንኳን የለም።  ከቶ ሲዊዚሻን እማ ዝምታ እንበላትን ይሆን? ግዴላችሁን እንበላት። ጎረቤቶቼ እራሱ ልጆች አሏቸው። ቤት ውስጥ እንዳሉ አውቃለሁኝ። ነገር ግን ልጆችም ዛሬ ከተለመደው ውጭ ሆነዋል? የጣሪዬ ጉጉቶችም የሉም። እንሱ ደግሞ ምን ሆንኩ ብለው ይሆን። አዬሩ እራሱ ጫን ያለ ነው። ደመመን ተጭኖታል። ከብዶታል እንደማለት። አይዋ ሻሾ ም ትውር አላለም። እናም አገር ምድሩ እንደ ራስ ዳሽኑ ወይንም እንደ ኪሎ ማንጃሮ ነፋ እደርጓል የጉሮሮን ማዋኛውን ሁለት የደጀሰላም አዋራ በር። አኔስ? ተምን ላይ ነኝ። እኔ ደግሞ ቅልል ብሎኛል። ጸጥ ረጭ የምመኘው የገነት የተድላ ኑሮዬ ነው። ግርግር ሁካታ አልወደም። አራት ነጥብ የሌላቸው ተናገሬዎችም ግጥሜ አይደሉም። በር ስትከፈት እና ስትዘጋ በእኔ ቤት ስለምን ይሰለቅ የበር አወቃቀር ብዬላችሁ እኔ እህታችሁ የህፃን ልጅ ያህል ብርቱ ጥንቃቄ ነው … ምችት ብሎኛል። በር ለ አኔ ቤቢ ነው። ይህን መሰል ጸጥተኛ ርጉ ዓለም እውደዋለሁኝ - ኮሽ አይሌውን። ·      ...