ልጥፎች

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ የኋንስ በሰላም ደረሳችሁ።

ምስል
    የ እኔ ክብሮች እንዴት ናችሁ፧ እንኳን ከዘመነ ማ ርቆስ ወደ ዘመነ የ ኋ ንስ በሰላም ደረሳችሁ። እንቁጣጣሽ። ኑሩልኝ። አሜን። መጪው ዘመን የቅንነት፤የሐሤት ይሁንልን። አሜን።  

ቡርሽ።

ምስል

ስለምን ኃላፊተት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማብቀል ተሳነን?

ምስል

ትውልዱ እና የአቅም መዋጮው የአስተዳደር ክራሞት። (30.07.2023.)

ምስል

ስለምን ኃላፊተት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማብቀል ተሳነን?

ምስል
  ስለምን ኃላፊተት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማብቀል ተሳነን?   "በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀምጠን ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን። (መዝሙር ፻፴፯ ቁ ፩) እንዴት አደራችሁልኝ ማህበረ ክቡራን እና ክቡራት? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ አምላኬን ተስፋ አድርጌ ደህና ነኝ። ሰሞናቱ እንደ ደመናም፤ እንደ ወጀብም፤ እንደ ዝናብም ይቃጠዋል በቅድስቷ በዕቴ በቪንተርቱር ከተማ። ማሰብ። ማሰብ። ማሰብ። እያሰብኩ ሃሳብን አስበዋለሁኝ። ስለምን ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማፍራት ተሳነን? እኛም ሆን የቀደሙት ስለምን መዝራትን ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ከማብቀል፤ ተጠንቅቆ ከማሳደግ ጋር ምኑ አፋተን? #በኃላፊነት እና በተጠያቂነት መሐል ጉልቻው ከፈረሰ ቆዬ። ግን ለምን?   #አደራ ምንድን ነው? #ትውፊትስ ምንድን ነው? #ትሩፋትስ ምንድን ነው? #ቅርስ ውርስስ ምንድን ነው? #ታሪክስ ምንድን ነው? #ባህልስ ምንድን ነው? #ወግ - ልማድስ ምንድን ነው?   ግን ምንድን ነው እራሱ #ምንድን ነው? መልስ ይሻል? እንጀራን እዬበሉ እንጀራ የተፈጠረበትን ሥልጣኔ ማብጠልጠል? አማርኛ ቋንቋን እዬተናገሩ አማርኛ ቋንቋን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት መፍጨርጨር? ሰንደቅ ዓላማው ባስገኜው የነፃነት ትንግርተ ቤተ - መንግሥት ተቀምጦ ሰንደቅ ዓላማን መፎካከር? ግን ምንድን ነው? እራሱ ምንድን ነው ምንድን ነው?   ኢትዮጵያ በሚለው ሙሉ አቅም ባለው ኃይለ ሚስጢር ለሥልጣን ተበቅቶ፤ ለሽልማት ተበቅቶ፤ ለክብር ለዝና ተበቅቶ አዬር ላይ ተንሳፎ በቅሎ ዙፋን የተጨበጠ ይመስል "የራሴ ጥረት ስኬት" እያሉ መጎረር በማጓራት መጯጯኽ ምንድን ነው? ግን እራሱ ምንድን ነው ምንድን ነው?   የተሰደደውም ኢትዮጵያ በሚል ኃይ...

#ጎንደር ትናንት ዛሬና ነገ #ጎንደር ከ1624 እስከ 1792 ዓ.ም ድረስ የሀገራችን መዲና ነበረች፡፡

ምስል
  #ጎንደር ትናንት ዛሬና ነገ #ጎንደር ከ1624 እስከ 1792 ዓ.ም ድረስ የሀገራችን መዲና ነበረች፡፡ የጎንደር የከተሜነት ታሪኳ የሚጀምረው በአፄ ፋሲለደስ የንግስና ዘመን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ይሁንና ጎንደር የሚለው ስያሜ በአፄ አምደፂዩን የንግሰና ዘመን ማለትም ከ1312 አስከ 1342 በዜና መዋዕል ተጠቅሶ መገኘቱ የጎንደርን ዕድሜ ለማሰላት በርካታ ዓመታተን ወደ ኋላ መመለስን የሚጠይቅ እንደሆነ አመላካች ነው፡፡   ጎንደር ፋሲለደስ የነገሱበትን 36 ዓመታት ጨምሮ የልጃቸው የፃዲቁ ዮኃንስና የልጅ ልጃቸው የታላቁ እያሱ 75 የንግስና ዓመታት የጎንደር ወርቃማ ዘመናት እንደነበሩ ታሪክ ይዘክራል፡፡ #የጎንደር የጨለማ ዘመን ተብሎ የሚታወቀው ደግሞ አፄ ተክለ ጊወርጊስ ስልጣን ከለቀቁበት ከ1792 ዓ/ም ጀምሮ አንደነበር ይነገራል፡፡ ኢትዮጵያ በዛጉየ ስረዎ መንግስት ማለትም ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ ቋሚ የማዕከላዊ መንግስት መቀመጫ አልነበራትም፡፡ በአፄ ፋሲለደስ የንግስና ዘመን ጎንደር የሀገሪቱ ዋና ከተማ መሆኗ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት መመስረት አዲስ ምዕራፍ መክፈት ችሏል፡፡ #የጎንደር ከተማ ከ200 ዓመታት በላይ በተከታታይ ለአስራ አራት ነገስታት መቀመጫ መዲና በመሆን አገልግላለች፡፡ የጎንደር ከተማ ጥንታዊ ስልጣኔ ሰላም የሰፈነበት ህግና ፍትህ የተከበረበት ኪነ-ጥበብና እውቀት ለማስፋፋት እድል የተገኘበት ጊዜ መሆኑን ጥንታዊ የታሪክ አሻራዎች ይዘከራሉ፡፡ የጎንደር ጥንታዊ ስልጣኔ ሲዘከር የኪነ-ህንፃ ጥበብ፣የእደ-ጥበብ ቱርፋቶች፣የንግድ ማዕከልነቷና ዘመናዊ የከተሜነት ይዞታዋ ተጠቃሾች ነበሩ፡፡ የጎንደር የእደ-ጥበብ ውጤቶች ከጎንደር ወርቃማ ዘመን አስከ ዘመነ መሳፍንት ድረስ ከፍተኛ እምርታ የታየ...