ልጥፎች

Alemneh Wasse ለዛሬ ሰበር የለንም!ልባችን ተሰብሯል!!

ምስል

"52 አመት በሀኪምነት አገልግያለው" - ኘ/ር ማለደ ማሩ | Prof. Malede Maru | Season 2 Epis...

ምስል

BBC "በሰሜን ጎጃም በድሮን ጥቃት ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ 50 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ" የምስሉ መግለጫ, ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል የተባሉትን አካባቢ"

  https://www.bbc.com/amharic "በሰሜን ጎጃም በድሮን ጥቃት ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ 50 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ" የምስሉ መግለጫ, ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል የተባሉትን አካባቢ የሚያሳይ ካርታ 8 ህዳር 2024, 07:14 EAT በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በተፈጸመ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ህጻናትን እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። ጥቃቱ ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም. ከወረዳው ዋና ከተማ ዱርቤቴ 40 ኪሎ ሜትር ገደማ በምትርቀው አርጌ (ዝብስት) በተባለች ታዳጊ ከተማ በተከታታይ ሦስት ጊዜ መፈጸሙን እማኞች እና ነዋሪዎች ገልጸዋል። ጠዋት 1፡10 አካባቢ በከተማዋ ገበያ አካባቢ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና ጤና ጣቢያ ላይ ጥቃቱ እንደተፈጸመ እማኝነታቸውን ለቢቢሲ የተናገሩ የአካባቢው ነዋሪዎች፤ “ከልጅ እስከ አዋቂ ያለቀበት” ነው ብለውታል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስለ ጥቃቱ ጥቆማ እንደደረሰው ጠቁሞ መረጃ እያሰባሰበ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግሯል። በድሮን ጥቃቱ መረብ ኳስ ይጫወቱ የነበሩ ልጆች፣ ለሽምግል እና የተቀመጡ ሰዎች፣ ህክምና ላይ የነበሩ እናቶች፣ የጉልበት ሠራተኞች፣ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ እና እርሻ ቦታ ላይ የነበሩ ሰዎች ሰለባ እንደሆኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃት የደረሰባቸው ሦስቱም አካባቢዎች በቅርብ ርቀት ላይ እንደሚገኙ ነዋሪዎች የጠቆሙ ሲሆን፤ ቢቢሲ አካባቢዎቹ ከ300 ሜትር ራዲዬስ ባነሰ ርቀት እንደሚገኙ በካርታ እና በሳተላይት ምሥል አረጋግጧል። ከጥቃቱ አንድ ቀን አስቀድሞ የድሮን ቅኝት እንደነበረ ለማመልከት “አየሯ ስትዞር ነበር” ያሉት ነዋሪዎች ጥቃቱን “ከተ

የፍቅርን ተፈጥሮ የሚያበረታቱ መዳረሻወች። Zugang, die die Natur der Liebe fördern.

ምስል

«በአማራ ክልል አራት ካምፖች “ለጅምላ ማሰሪያነት” መዋላቸውን አምነስቲ አስታወቀ

  https://www.bbc.com/amharic/articles/ce9gxlvyyzro «በአማራ ክልል አራት ካምፖች “ ለጅምላ ማሰሪያነት ” መዋላቸውን አምነስቲ አስታወቀ በአማራ ክልል ለአንድ ወር በዘለቀው “ የዘፈቀደ እስር ” የተያዙ “ በሺዎች የሚቆጠሩ ” ነዋሪዎች በዳንግላ፣ ኮምቦልቻ እና ሸዋ ሮቢት ከተሞች እንዲሁም በጭልጋ ወረዳ በሚገኙ ጊዜያዊ የእስር ካምፖች ውስጥ እንደሚገኙ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። አምነስቲ፤ “ ኢትዮጵያ ለአገራዊ፣ ለአህጉራዊና ለዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ግዴታዎች ግድ የለሽ ወደመሆን አዲስ ምዕራፍ ገብታለች ” ሲል ወቅሷል። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም ይህንን ያለው ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለውን “ የዘፈቀደ እስር ” በተመለከተ ትናንት ረቡዕ ጥቅምት 27 ፤ 2017 ዓ . ም . ለሁለተኛ ጊዜ ባወጣው መግለጫው ነው። ተቋሙ፤ በክልሉ እየተፈጸመ ያለውን እስር እና የእስረኞች አያያዝ በተመለከተ ከእስር ካምፖች የወጡ ሰዎችን ጨምሮ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን አካላት እንዳነጋገረ በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። አምነስቲ፤ እስሩን አስመልክቶ ባደረገው ጥናት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ አራት የእስር ካምፖች ውስጥ እንደሚገኙ እንደደረሰበት አስታውቋል። “ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባደረገው ጥናት፤ ግብረ ኃይሉ በመላው አማራ ክልል የሚገኙ አራት ጊዜያዊ የእስር ካምፖችን በሺዎች በሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች መሙላቱን አረጋግጧል ” ሲል በጥ

የአለምን አትኩሮት ስቦ የቆዬው የአሜሪካ የ2024 ፕሬዚዳንታዊ እና በዬደረጃው ያሉ ምርጫ አካቶ #በሰላም ተጠናቋል። ተመስገን። አሜን።

  የአለምን አትኩሮት ስቦ የቆዬው የአሜሪካ የ2024 ፕሬዚዳንታዊ እና በዬደረጃው ያሉ ምርጫ አካቶ #በሰላም ተጠናቋል። ተመስገን። አሜን።    አሜሪካ ለዴሞክራሲ የምርጫ ሥርዓት መንፈስም ነው። የሚስብ ነገር አለው።    "አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሄር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።" (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር፯)   የእኔ ጭንቀት ምን ይፈጠር ይሆን የሚል ነበር። እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን በሰላም ተጠናቋል። እርግጥ ነው ዴሞክራቶች በሰፋ ልዩነት ተሸንፈዋል። ውድድር ለመሸነፍም // ለማሸነፍም ነውና ዴሞክራቶች መሸነፋቸውን በፀጋ ስለሚቀበሉ የምርጫው ውጤት #በሰላማዊ ሽግግር ይፈጸማል። ሪፕብሊኮች ተሸንፈው ቢሆን ግን ከባድ ችግር ይከሰት ይሆን በሚል ስጋት አድሮብኝ ነበር። እግዚአብሄር የወደደው ተፈጽሟል። የእግዚአብሄር ፈቃድ ከእኛ በላይ ለአለሙ ሰላም ይጠናቀቃል - እና።   በተረፈ ይህን መሰል ዕድል ለአገሬ ለኢትዮጵያም ይገጥማት ዘንድ እመኛለሁ። ህዝብ ካለምንም ጠበንጃ የፈለገውን፤ ያሻውን ደስ ብሎት መምረጥ የሚችልበት የዴሞክራሲ ጥበብ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ #ህልም ነው። የአሜሪካ አገር የየዘመኑ የምርጫወች ሂደት እጅግ አጓጊ እና ቀልብን የሚይዝ ነው። የዘንድሮ ምርጫ ፋክክሩ በጠሩ ፋክቶች ላይ ስለነበር መሳጭ ነበር። ስለሆነም ከውስጤ ነበር የተከታተልኩት። የሴት እጩ ፕሬዚዳንትም መኖር የበለጠ አትኩሮቴን ስቦት ነበር።    ዴሞክራቶች በእጩ ፕሬዚዳንታቸው ጎን በምክትል ፕሬዚዳንትበክብርት ወ/ ሮ ካሜላ ሃሪስ (ኮሚላ ሃሪስ) ዙሪያ ተግተዋል። ተጽዕኖ ፈጣሪወች አብዛኞቹ ከጎናቸው አሰልፈውም ነበሩ። በተደጋጋሚ ሴት የዴሞክራሲ እጩወች ለፕሬዚዳንትነት ተወዳድረው አልተሳካላቸውም። ብላቴ ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህ