ልጥፎች

ኦ!

ምስል
ኦ! – ከሥርጉተ ሥላሴ June 2, 2015 |  Filed under:  ነፃ አስተያየቶች  |  Posted by:  ዘ-ሐበሻ 307 SHARES Facebook Twitter 02.05.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/ ይድረስ ለፓን አፍሪካኒስቱ ወገኔ ለተከበሩ አቶ ቴወድሮስ ዳኜ – „እንዳላፍር ልቤ በሥርዓትህ የቀና ይሁን“ / መዝሙር ምዕ. 118 ቁ. 80 / „ እንዳያመም ጥራው እንዳይበላም ግፋው“ በቅድሚ እንዴት ሰነበቱ። ለአፍሪካውያን የስደትና የሰቆቃ መከራ የበኩለዎትን ድርሻ ለመወጣት በማድረግ ላይ ያሉትን ዬሰብዕዊነት  ጥረት አብዝቼ አከብራለሁ፤ ኢምንት ብሆንም አመሰግናለሁ። ከመልካም ነገር ፍቅርና ተስፋ መኖርና መሆን አሉና። እኔ ብዙን ጊዜ የኢትዮጵያ ሙሑራን በሰብዕዊ መብት እረገጣ፤ በዘበጠ አስተዳደር ጉዳይ ላይ ያላቸው ተስትፎ አናሳ ነው፤ የበቃም አይደለም በማለት ወቀሳን ከወገኖቼ ሳዳምጥ የአያያዝ አቅም ከሙሁራዊ ሥነምግባር ውስጠት ጋር የማጣጣም ብቃት አንሶን ሊሆን ይችላል የሚል ዕድምታ ስለነበረኝ ምንም ብዬ አላውቅም። ዛሬ ግን ተናጠሉን ሙሁርነት ብቻ ሳይሆን እንደ ቀደምቶቹ ኢትዮ – አፍሪካውያን ዕንቁዎች መስመሩን ለመከተል መቁረጥ ብቻ ሳይሆን ተግባር ላይ በተገኙት ወንድሜ ላይ ቅሬታዬን ከዕንባዬ ጋር ልልክለው እንሆ ወደድኩኝ። ሃዘኔ የምር ልቅሶዬም ከቁስለት – የተቀዳ ነው። ውድና የተከበሩ ኢትዮ አፍሪካዊው አቶ ቴወድርስ ዳኜ – ጎሰኝነት ወይንም መንደርተኝነት ያልተመጣጠነ የአስተሳሰብ እድገት ወይንም የአስተሳሰብ ድህነት ጽንስ ነው። እድገቱም ከቤተሰብ ቀጥሎ ያለ ስለሆነ ሁለመናው በእንጭጭ ዕጭ ተፈጥሮው ላይ ስለሚወሰን አህጉራዊ ኃላፊነትን በተቆርቋሪነት ላበ...

ፕ/ ዶር. ፍቅሬ ቶሎሳ።

ምስል
                     ብሩክ ቀን – ሥርጉተ ሥላሴ                   „ … እኔ ግን እግዚአብሄርን እለምን ነበር፥ ነገሬንም ወደ እግዚአብሄር አቀርብ ነበር።                                   ዬማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቋረጠውን ተአምራት ያደርጋል። …“                                                 ( መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፭ ከቁጥር ፰ እስከ ፱ ) ይድረስ ለኢትዮጲያኒዝም አባት እና የአብሮነት ሐዋርያ ለሆኑት ሊቀ – ሊቃውንት ፕሮፌሰር ዶር . ፍቅሬ ቶለሳ – ባሉበት። ሊቀ – ሊቃውንት ፕሮፌሰር ዶር . ፍቅሬ ቶለሳ እንደምን   ሰነበቱልን ፤ እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።    „ የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ “   በዚህ በአዲሱ መጸሐፍዎት ዙሪያ ከኢትዮዽያ ኃብታት ከሆኑት ሁለት ሊቀ – ሊቃናት ጋር ያደረጉትን ክርክር ግራ ቀኙን – ታደሜበታለሁ። ከሥር ዬሚታከሉ ዬአንባብያንን አስተያዬትንም በማከል ነበር – ዕድምታዬ። ...