#ፖለቲካ #ብልህነት #ይጠማዋል። እንደ መከወኛ።

 

ቅንነት የህሊና #ቀበቶ ቢሆን፤ አቅልም ቢፈቀድለት ስል በትህትና ቤተ- ሥርጉትሻ ታዳሚወችን እጠይቃለሁኝ።
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 May be a black-and-white image of one or more people and people smiling
 
የበደሉ መነሻ እና መድረሻ በጥልቀት ሊጠና የሚገባው ነው። ባለፋት ፰ ዓመታት የሆኑት ነገሮች ሁሉ በተለይ እንደ እኔ ከሁሉም ነገር እራሱን አግልሎ ግን የአገሩን፤ የአህጉሩን፤ የዓለምን ሁኔታ የሚከታተል ሰብዕ አደብ ገዝቶ፤ በጥሞና ሆኖ የቀውስ ወጀብ መነሻውን ይሁን መድረሻውን ሊመረምር ይገባል። አቅም የወንዝ ዳር #አሽዋ አይደለምና። 
 
በገፍ ሌት እና አቅም መግበን፤ ልዩ ልዩ ስለ ሰብ ግድ የሚላቸውን ተቋማትን አስተባብረን፤ የተከበሩ የዓለም ሊቃናትን በር አንኳኩተን፤ ደፍረን #መስክረንም መንበር ላይ ካስቀመጥን በኋላ፤ በዓለም መድረክ እናት አገር ኢትዮጵያ እንደባይታዋር ሆና "#ኢትዮጵያ #አጀንዳዬ አይደለችም" የሚልን መርዶ ነው እኔ ያዳመጥኩት። ሰውነቴ ነበር የተንቀጠቀጠው። ለእኔ ከኢትዮጵያ በላይ አጋይስትዓለሙ ሥላሴ ቅድስት እናቴ ድንግል ማርያም እና ቅዱሳን ፃድቃን እና ሰማዕታት ነው ያሉት። 
 
የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ እንደ ነውር ይታይ በነበረበት ጊዜ ተማግደንበታል። ዛሬ ከሚዲያ ላይ፤ በየፖለቲካው ፎረም ያለው #መቧደኑም፤ ወጨፎውም ማንን እንደሚገርፍ በጥሞና እየተካተትልኩት ነው። ቢያንስ እቆምለታለሁ ለሚባለው ማህበረሰብ #አንዱን ጥሎ ሌላውን አንጠልጥሎ ሊሆን አይገባም ነበር። እንመራለን ካሉ። እኛማ አማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰው ሁለገብ በደል በአመክንይ ስንሞግት፤ ስለአፋሧ እናትም፤ ስለ ጌዲዋ እናትም፤ ስለተጋሩ እናትም፤ ስለኦሮሞ እናትም፤ ስለ አማሮ እናትም ወዘተ እንደምንታገለው ነበር የታገልነው። 
 
እንታገልለታለን ካሉ ስለዛ አሳረኛ ማህበረሰብ ወጥ በሆነ አክብሮት፤ ወጥ በሆነ የአያያዘ ቀመር "አንድ አማራ፤ አንድ ፋኖ" ሊባል ይገባ ነበር። ከአዲስ ገቦቹ የአማራ ታጋዮች፤ በፊት ገድል የሰሩ፤ ጥቃት ያወጡ የአማራ ልጆች ጭምቶቹ ዝም ብለው እስኪ ሜዳውም ፈረሱም የሚሉት ነገር ተሰውሮባቸው፤ ወይንም ጠፍቷቸው፤ ወይንም የተደማጭነት አቅም ገዶቸው አይደለም። ይህን #አይሰቡት
 
አቅም አለ። በቂ ተደማጭነትም ሊኖር ይችላል የአበው እና በእመው የዊዝደም ጎዳና ከተከበረ። ግን ለማን? ግን ለምን? #ከዚያስ። የኢትዮጵያ እናቶች በምርኩዝ አጎንብሰው እዬሄዱ ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት፤ ጫካ ለጫካ በየዓውድዓመቱ፤ እንዲከራተቱ አልነበረም ወጣትነቴን የገበርኩት። ወይንም እንዲህ ደማቸው ደመ ከልብ የሆኑ ታናሽ ወንድሞች እና እህቶች እንዲኖሩን አልነበረም። እኔ በአብይዝም አንድም የፖለቲካ እስረኛ ሊኖር አይገባም ብዬ ነው እማምነው። አብይዝምን ወደ ሥልጣን ካመጡት መሠረታዊ ጉዳይ ኢትዮጵያ ላይ ፖለቲካ ነፃነቱን በህወሃት ስለተዘረፈ ነበር።
 
ሌላው በገፍ ትውልድ በጦርነት፤ በቀውስ፤ በግርግር፤ በእስር ቤት ይሞታል። #ገዳዩ ማን እንደሆን አናውቅም። ሆስፒታል ሄዶ በሰላም የሚመለስ የለም። ማን ምን እየሠራ እንደ ሆን የምናውቀው ነገር የለም። ጥልቅ በሆነ ችግር ውስጥ እናት ኢትዮጵያ። ትናንት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ዛሬ የትጥቅ ትግል የሚዲያ መሪ፤ ወይንም ማህበርተኛ። ጠበንጃ እኮ ስለሰብአዊነት ግድ አይሰጠውም። ጠበንጃ የተፈጠረው ለግድያ ነው። ሌላ ተልዕኮ የለውም የጠበንጃ። አንድ የሚዲያ ሰብዕና ያለው ነፍስ ደፍሮ "እርምጃ ይወሰድበት" ሲል፤ የእንቶኔ ሠራዊት ረገፈ፤ አለቀ፤ በቁስለኛ ተጥለቀለቀ ሲል ሰውን ቢቀር እግዚአብሄር፤ አላህ እንዴት አይፈራም????
 
ሌላው የኤርትራ መንግሥት እና የኢትዮጵያ መንግሥት ሲስማሙ ደስተኛ ነበርኩ። ብሎጌ ላይ አለላችሁ። አልሰረዝኩትም። አልሰርዘውም።እልል ነበር ያልኩት። አብረን አድገን፤ ተምረን፤ ኑረናል። እኔ አሁንም የመነጠል ስሜት የለብኝም። እንደ ግለሰብ።
 
ነገር ግን መንግሥት እንደመንግሥት አቅሙን ለክቶ፤ እንደምን ማኔጅ ማድረግ እንዳለበት አስቦበት፤ ልክ ያለው፤ ፈርጁን ያደራጄ፤ ህዝቡን አማክሎ የስምምነቱን፤ የንግግሩን፤ የድርድሩን ሂደት በጥንቃቄ መከወን። ለኢትዮጵያ፤ ለአፍሪካ ለዓለም ህዝብም ማሳወቅ ይገባ ነበር። የተዘጋ። የተደፈነ። የተከረቸመ ሁነት ተፈጠረ። ለምን? አሁን ሁለቱም አገሮች ህዝባቸውን ብቻ ሳይሆን ወዳጆቻቸውን ሁሉ ድረሱልን እያሉ ነው። #ሽሚያ ላይ ይገኛሉ።
 
#በዛን ጊዜ በሙሉ አቅሙ ነበር የኤርትራ መንግሥት የገባው። የኢትዮጵያ የደህንነት ተቋማት፤ የኢትዮጵያ የሠራዊቱን አቅም፤ አባይ ግድብን እንዲጎበኝ በይፋ ተፈቅዷል። ሆድዕቃህን ናኝበት ተብሎ ማለት ነው። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ ፈጽሞ አያከስርም ነበር።
 
የኤርትራ መንግሥት ሙሉ አካሉ በዕድሜም፤ በተመክሮም በካበተው የፖለቲካ ልም፤ መሪው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ የስለላ ሙያ ያላቸው ሆነው በርህን #ቧ አድርገህ #ፏ አድርገህ ስትቀበል ያን ማስተዳደር፤ በቁጥጥርህ ሥር የማድረግ አቅምን #መዝኖ መነሳት ይጠይቅ ነበር። አልሆነም። 
 
ሌላው የህወሃትን መዋቅር እንደ አለ ስትቀበል፤ ይመቸኝ ብለህ መዋቅሩን እንዳለ ስታስቀጥል፤ ለጊዜው በቁጥጥር ሥር ያዋልካቸውን ቁንጮ ሊቆቹን ቢዛቸውን አመቻችተህ እልል ብለህ አሜሪካ ስትሸኝ፤ አገር ውስጥ ያለውን የህወሃት አካላት ሥልጣን፤ ክብር ሞገስ ሰጥተህ ይቀጥሉ ስትል ቢያንስ የስልክ #ሴሚ ካርዱን ሳታስቀይር መቀጠልም ሌላው የፈተና ኔት ነው። 
 
እኛም ብንሆን በቅንነት ህወሃት በአዲስ ረቀቅ ባለ በተጠና ልዩ ስልት የሰባዕዊ መብት ተሟጋች አዲስ ገጸ ባህሬ ይዞ ከች ሲል የሰናፍጭ ታክል ጥርጣሬ ሳይኖረን እንዳለ ተቀብለን እንክህ እንክህ ብለን እንደታቦት መከብከብ ብቻ ሳይሆን ማንም ዝንባቸውን እንዳይነካ ማለት ብቻ አይደለም ከቅዱሳን ያልተለየ ክብር ሰጥተን ቁንጮ ስናደርግ ማስተዋላችን ዝሎ ነበር። 
 
ህወሃት እና ብልጽግና ሲዋጉ "ጦርነት አያስፈልግም " ያለ ነፍስ፤ ፋኖ እና ብልጽግና በአማራ መሬት ላይ ሲፋለሙ፤ እሳተ ጎመራ ሲንቀለቀል፤ " ቀጥል ጦርነት፤ የምን ድርድር፤ የምን እርቅ፤ ድርድር ፖለቲካ ሆኖ ይቀነቀናል" እያሉ ሲያውጁ ማን ምን እንደሆነ ጊዜ ራዲዮሎጂ ነውና በዓይናችን በብሌኑ አየን። ጦርነት አያስፈልግም የፖለቲካ አቋም ከሆነ ያን አጽንቶ መቀጠል ይገባ ነበር። #ለአንጀቴ ሃራም ጦርነት፤ ለገራገሩ ግን ተማገድ? ይህ ነው ሰብአዊነት? ይህ ይሆን የሚዲያ ሰውነት፤ ለዛውም ያሸለመ? 
 
በተለይ ከጎረፈው ጋር ልንጎርፍ የማንፈቅድ፤ ከአጎፈረው ጋር ልናጎርፍ ይሁን ለማንል ሰብዕናወች ይህ ዘመን በራሱ የፖለቲካ ትግል #ካሪክለማችን ሊሆን ይገባል። የሰውን ልጅ "ይሙት በቃን!" የሚፈቅድ ማንኛውንም መንፈስ #አክ እንትፍ ልንለው ይገባል። 
 
በብዙ ሁኔታ ባሳለፍናቸው አስጨናቂ ዓመታት እራሱ እና መሰሎቹ ጋር ቀውሱን ጸንሶ፤ አደራጅቶ እና መርቶ፤ ሞጋቹ የእሱ አዲስ ተዋናዮች ነበሩ። ነፍሳችን ከሰብአዊ መብት ጋር በተክሊል ለተጋባው ጉዳዩ #ሴንሲቲብ ነበር። አቅማችን ለዚህ አስመሳይ ትዕይንት ገበርን። እኛው እራሳችን ሰብዕና እንገነባለን፤ ቁጭ ብለን የሰቀልነው፤ ማውረድ አቅቶ ኤሉሄ፤ ኤሉሄ ሰርክ የሚሆነው። ይህን ድፍርስርስ ሁነት አጥርቶ መጓዝ ይጠይቃል።
 
ህወሃትን - ታግለን፤ በፈጣሪ በጥበብም ከመንበሩ ፈቅዶ፤ ድምጽም ሰጥቶ ተሰናቤቶ፤ ግን የእሱን አዲስ ተዋናይ ገጸ - ባህሬወችን በሙሉ አቅም ደገፈን። ቅንነታችን እኛኑ #በደለን። ቢያንስ አሁን በሽታ ሽቶ የዶግ አመድ የሆነው በዕታችን የአማራ ክልል፤ ለወደፊትም የታጨለትን አመድነት በጥንቃቄ ልናየው ይገባል።
 
እንዲህ እንደወጡ ወደ አፈር የሚላኩ #ታናናሾቻችን ነፍስ ለማዳን ከውስጣችን፤ ውስጣችን አጥርተን ልንታገል ይገባል። ከሁሉ በላይ አቅሜ የትኛውን ኃይል ያፋፋል ብለን ልናስብበት ይገባል። ነገስ የማን? ለማን ሊሆን ይችላል የሚለውን በተደሞ ልንመረምረው ይገባል።
አንድ ሰው ይሁነኝ ልትሉ ትችላላችሁ። የዛን ሰው ቲም ግን አታውቁትም። "ኢትዮጵያ ሱሴን" ሆ! ብለን አብዛኞቻችን ደገፍን። 
 
አሁን ያሉትን ሰርክ የሰርግ ቅልቅል፤ እና ግጥግጥ ይመስል የሽርሽር፤ የግብረ - ሰላም፤ የፌስታ ኢቬንቶች፤ የፋሽን ትዕይንት፤ የማዕረግ እና የክብር ተክሊል ላይ የምናያቸውን የአብይዝምን ሹመኞች አንዳቸውንም አናውቅም። ነገም - ይኼው ነው። ማን የትኛውን ሰብዕ ይዞ እንደሚመጣ አናውቅም። አንድ ቀንጣን ነፍስ ተከትሎ መንጎድን ልናስታግሰው ይገባል። ለዚህ ነው አደብ ገዝቶ መርምሮ መነሳት የሚያስፈልገን። ቢያንስ እንደ ኩርድሾች #የብትን አፈር ለማኞች እንዳንሆን። 
 
ክስተቶችን አስታግሶ በማስተዋል መመርመር በአጽህኖት ያስፈልገናል። ህወሃትን ያህል #ቤርሙዳ ትርያንግል የሆነ ድርጅትን የተሸከመች አገር ማን በምን ዓይነት ሴራ - በምን መልክ ሼሩን አበጃጅቶ ፈጸመ የሚለውን በአቅል ሊመረመር ይገባል። ህወሃት ሠራሽ ቀውሶች ብቻም ሳይሆኑ ኦነግ ሠራሽ መከራወችን ሊኖሩ እንደሚችሉ፤ ከኬንያ በስተቀር የቅርብ ጎረቤት አገራትም መቸውንም ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም መሆን እረፍት እንደማይሰጣቸው ዕውቅና ልንሰጠው ይገባል። በዚህ ውስጥ ብሄራዊ ጉዳይን ከግለሰብ ሰብዕና በላይ የማዬትን አቅም አምጠን ልንወልድ ይገባል። 
 
ነገ ከነገ ወዲያ አደራን ለማን የሚለው የዕለት ተለት ጉዳያችን ሊሆን ይገባል። ኢትዮጵያ በደቡብ #ስክነት ብቻ ለመቀጠል አትችልም። በአስተውሎት ብትመረምሩት የሚሞገቱት ምርጫ ለምን እንገባለን አላችሁ ተብሎ የአማራ ልጆችን ነው??? የአማራ ወጣት ስለምን ከተማ ታያ ተብሎ ይከሰሳል? 
 
ደቡብ ላይ በጸጥታ፤ ጨምቶ የሚማረው፤ የሚኳለው፤ ሙሉ የፖለቲካ ውክልና ያገኜው አይነካም። እሰቡት ብዙ የአማራ ክልል የምርጫ ጣቢያወች፤ የትግራይ ክልልን ሙሉውን አክሎ ምርጫ ማካሄድ ካልተቻለ ዕድሉን ማን ይወስደዋል? ደበቡብ በሙሉ አቅሙ፤ ሱማሊያ አዲስ ጉድ ያለው የሊቃናት ብቁ ኃይል ወደ ፊት እየመጣ ነው። እሰየው። ህብርነቱ ነው ውበቱ። ግን በማን ጎደሎነት? የአማራ ውክልና ነው ለቀደሙትም ለአዲሶቹ ክልሎች በብሄራዊ ደረጃ ሹመት የሚሰጠው። 
 
አብይዝም ሥልጣን አጋራሁ ሲል የኦሮሞ፤ የደቡብ ውክልና አልተነካም። በአማራ የፖለቲካ ውክልና ነው አብይዝም ሁሉይዝምን ማጽናት የሚፈለገው። የአማራ የፖለቲካ ውክልና ጭላጭ ላይ ነው ያለው። አሁን "በምንም አትሳተፋ" ሲልህ ሙጣጭ አይኑርህ ልቀቅ እያለህ ነው። ከተፈጠረበት ቦታ የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች ምንም ጫና የለባቸውም። አንዲት የፋኖ ጠሽ ጧም የለም። ይህን ጅልነት አዝሎ ይሁን አሽኮኮ አድርጎ መጓዝ በፖለቲካ ብልህነት አይደለም። ልብ ይገዛ።
 
እዚህ ላይ ሁለት ምሳሌ ላቅርብ።
 
1) የአንካራ ዲክላሬሽን ለአገረ ሱማሌ እረፍት ሰጥቷል። ማን ተገብሮ? የኢትዮጵያ ወሳኝ ፖለቲካዊ ፍላጎት ተገብሮ። ከዛ ቱርክ ምን አደረገ፤ አዲስ እኔ ነኝ ያለ ፕሮጀክት ሱማሌ ላይ ዘረጋ። አሁን ትልቅ መርከብ ተንቀሳቅሷል።
 
2) የጋዛ እና የእስራኤልን ጦርነት ለማስታገስ ሞደሬተር የግብጽ መንግሥት ነበር። ምዕራፍ ፩ ጥሩ እየሄደ ነበር። ለዚህ ካሳ ወይንም ግብር ማን እንዲከፍል ተፈለገ ኢትዮጵያ?
 
አሁን የሚግባባ ይመስለኛል፤ የብልጽግና ፓርቲ ብሄራዊነት በማን ኮታ? የአማራ የፖለቲካ ውክልና ተገብሮ። የአማራ ክልል የትግራይ ዕጣ ፈንታ ልሙጥ ይሆን ዘንድ ነው አሁን እርብርብ እየተደረገ ያለው። ይህ ፍሬ ዘር ዕሳቤ የገባው፤ የተረዳው ነፍስ ቢያንስ አቅሙን እንደ ወንዝ ዳር አሽዋ የትም አይበትንም። 
 
ትግራይ ላይ ምን ያህል ቀን ጦርነት ነበር? አፋር ላይስ ለስንት ወራት ዘለቀ? አማራ ላይስ? ዘመነ አብይዝም ፱ኛው ዓመት ዋዜማ ላይ ነን። ከስሜን ተራራ ቃጠሎ፤ የባህርዳር ከተማ የተለያዩ ቀበሌወች ቃጠሎ፤ የማዕከላዊ ጎንደር የ80 ሺህ ህዝብ መፈናቀል፤ የአማራ ዩንቨርስቲ ተማሪወች መፈናቀል እና እገታው፤ የወሎ በጦርነቱ ያስተናገደው አሳርን፤ የኮንበልቻን "የሰው ልጅ አካልን #ጭስ አስሉት????????" 
 
ህዝባችን እንዲያለቅስ እንጂ እንዲስቅ አይፈቀድለትም። በልደት እና በጥምቀት ሳቁ የሚያንጨረጭራቸው ህውሃት ገብ ሰብዕናወች፤ ሚዲያወች ተመልክተናል። አመድነቱ ይናፈቃል። ጠቀራ መልበሱ ይበረታታል። በዛ ዋጋ የተባበሩትን ህወሃት ቁብ ለማድረግ ወጀቡ አይሏ እናያለን፤ በዝምታም እናስተውላለን። አደብን እንፍቀድ። ተግም ብለን እናዳምጥ። እንደ ዕምነታችን ለጸሎት እንተጋ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁኝ። 
 
#ፖለቲካ #ብልህነት #ይጠማዋል። እንደ መከወኛ።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
19/02/2025
መረጃውን ከሃኪሞች ድምጽ ያገኜሁት ነው። አሁን በኢትዮጵያ የገዘፈ የሱባኤ፤ የድኦ ወቅት ስለሆነ ሁሉም እንደ አቅሙ ዕንባ በአገራችን ይቆም ዘንድ በጸሎት አገራችነን ኢትዮጵያን ማገዝ፤ ስለ ህዝባችን ማሰብ ከእያንዳችን በግል ከሁላችንም በጋራ ጥረት ይጠበቅብናል። ጸሎት ብዙ መከራን አሸንፎ የመውጣት አቅም አለው። ግን ንጹህ ልብ፤ ንጹህ ህሊና፤ #ንጹህ ቅንነት ይሻል።
 
"Medical education already comes with a lot of pressure. When you add the difficult situation our country is facing, we understand that it can expose students to depression and even serious mental health struggles that may lead to loss of life.
Please, our students, whenever you face illness, family problems, or any other challenge, come and talk to us, your teachers. Share your thoughts with us. Maybe we are a little older and more experienced, and perhaps we can help you find a solution. See us as your older brothers, as your family.
And we, as a medical school, both as individual instructors and as institutions, must advise one another and remember that we have a responsibility. At the very least, we should do what we can to prevent this repeated tragedy and protect our students from such loss.
Rest in peace dear our student 💔
Dr. Tewodros Ayenew
Assistant Professor of Internal Medicine @BDU"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።