የድህነቱ ልዑል።
ዬድህነቱ ልዑል *** ከሥርጉተ © ሥላሴ 30.06.2018 (ከኮሽ አይሏ እናት ሲዊዝ።) „የእሳቱንም ዋይ ሲነድ አዬሁት ይኸውም የሚአስፈራ ነው። እንደሚያስፈራሩ ተራሮችም በእሳት ተከበዋል ወዲያና ወዲህ እያሉ ይተዋወካሉ።“ (መጽሐፈ ሄኖክ ምእርፍ ፵፪ ቁጥር ፬) የክትክታ እንጨት ጥሩ ለማጠኛ ካለ አግባብ ነሰተኝ ያ ... ክፉ መጋኛ። ወይራውም ለሁል ይጠቅም ነበረ ጊዜ በሰጠው ቅል በግፍ ተቀበረ። ብሳና አባሎ፤ በሐገሩ ተዳብሎ ታመሱ በበቀል፤ በዛ በአለሎ። ግራሩ ላንቁሶው፤ በአንድ ያለቃቅሳሉ ዘመን እንዲያቸው እንዳይዘለሉ። ኡኡታ ኡኡታ ኡኡታ ነገሰ ሐገሩ ተምደሩ ምሾ ተላበሰ። እህ እህ - እህህ፤ አረ ተጠበሰ ጭሱ ሲበዛበት እየተጨናበሰ ዋይታ እዬጨሰ። ዋዬ ! ዋዬ ! ዋይ - ዋይም ፋፍቷል በደብሩ በበቀል በቋሳ መታረስ ሆኖበት አዳሩ። መጠጊያ ...