የድህነቱ ልዑል።

ዬድህነቱ ልዑል
***
ከሥርጉተ © ሥላሴ 30.06.2018 
(ከኮሽ አይሏ እናት ሲዊዝ።)

                   „የእሳቱንም ዋይ ሲነድ አዬሁት ይኸውም የሚአስፈራ ነው። 
                      እንደሚያስፈራሩ ተራሮችም በእሳት ተከበዋል ወዲያና 
                                   ወዲህ እያሉ ይተዋወካሉ።“
                              (መጽሐፈ ሄኖክ ምእርፍ ፵፪ ቁጥር ፬)



የክትክታ እንጨት ጥሩ ለማጠኛ
ካለ አግባብ ነሰተኝ ... ክፉ መጋኛ።
ወይራውም ለሁል ይጠቅም ነበረ
ጊዜ በሰጠው ቅል በግፍ ተቀበረ።

ብሳና አባሎ፤ በሐገሩ ተዳብሎ
ታመሱ  በበቀል፤ በዛ በአለሎ።
ግራሩ ላንቁሶው፤ በአንድ ያለቃቅሳሉ
ዘመን እንዲያቸው እንዳይዘለሉ።

ኡኡታ ኡኡታ  ኡኡታ ነገሰ
ሐገሩ ተምደሩ ምሾ ተላበሰ።
እህ እህ-እህህ፤ አረ ተጠበሰ
ጭሱ ሲበዛበት እየተጨናበሰ
ዋይታ እዬጨሰ።

ዋዬ! ዋዬ! ዋይ -ዋይም ፋፍቷል በደብሩ
በበቀል በቋሳ መታረስ ሆኖበት አዳሩ።
መጠጊያ መሸሻ ጥግም ጠፋ አሉ
መታሰር መገደል በአንድ ሲጠመዱ።

ስጋት ዘመን ሰጥቶት ቀዬውን ሲያካልል
በጠኔ ይፈጫልይታመሳል ሐገር
በለስም የሰጠው ልዬነትሚሉት
ሳይዳር ሳይኳል ቀብር ሆነበት።

የድህነቱ ልዑል ኢትዮጵያዊነት
ካባህን ደርበው ልይህ ወደፊት!
  • ·      ስታወሻ። የኔዎቹ …

ተጣፈ ሚዚያ 17/2001 .. ሄርሽን ሆቴል
ሄርሽን ሆቴል የወያኔ ሃርነት ትግራይ የማንፌሰቶ ማህበርተኞች ስደት ላይም ለዛውም በኤርትራዊያን ሥም እጃቸውን ሰጥው ግን አላስቀምጠኝ ሲሉ በመነግሥት ተወስኖልኝ ቤት እስካገኝ ድረስ እናታለም ሲወዝዬ ሆቴል ተከራይታ ለ8 ወር ለሆቴል እዬከፈለች አኖረችኝ። ከዛ እያለሁ የጻፍኩት ነው። በስደት ስደት የተጣፈ ማለት ነው። መጽሐፉ በነፃነት ሃይሎች የትንሳኤ እና የህይወት ባለመንገዶች ግዞት ተፈርዶበት ደግሞ መጋዝን ያሞቃል። ይሄው ነው የአላዛሯ ኢትዮጵያ አቅም፤ ክህሎት፤ ችሎታ ዕጣ ፈንታ እንደ አባይ ወንዝ በመና የተባዛ ... 
  • ·      እንደ አወሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2010 ተስፋ መጸሐፌ ላይ ለህትምት የበቃ ነው መደቡ ገጽ 17 ነው።

   መኖርን ለማኖር በመኖር መኖር! 
   ቅኖቹ ባለ አደቦቹ ኑሩልኝ።
    መሸቢያ ጊዜ።




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።