ርትህ ክፍል አንድ።

ርትህ።
ክፍል አንድ።
ከሥርጉተ © ሥላሴ 30.06.2018 (ከመንኩሲያዋ ሲዊዘርላንድ።)
„በብርሃን ሲያበሩ ሲያመስግኑም ጻድቃን በድንቁርና ከዲያቢሎስ
   የተወለዱ ኃጣዕንን በገኃነም ሲወድቁ ያዮዋቸዋል ኃጣዕንም
       ጻድቃንን በመንግሥት ሰማያት ሲያበሩ ያይዋቸዋል።“
           (መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፵፪  ቁጥር ፲፭ )


  • ·      ፍታ!


እንዴት አላችሁልኝ የአገሬ ልጆች? ደህና ናችሁ ወይ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ዛሬ በርካታ ነገሮች ቢኖሩም ቅድሚያ ሰጥቼ ምልከታዬን ላጋራችሁ የምሻው የአፋሩም የሠመራ ጉባኤ ጥያቄ እና የመልሱን ዕድምታ ነው።

እርግጥ ነው ይሄ መቅድም ስለሆነ ተያያዥ ነገሮች ማንሳቱ ግድ ይለኛል። የክልሎች ማሰረጊያም ጉባኤ ስለሆነ አፋር። ምክንያቱም የጠ/ ሚር አብይ የመንፈስ ነፍስ እኔን እንደ ገባኝ በሁለመና የተቃኘ ንድፍ አለው። የሠመራው ከክልል አንፃር ማጠቃለያው ነው። ስለዚህ በውል ሊፈተሽ ይገባዋል። በምልሰትም አንዳንድ ነገሮችን በብዕረ ብራና ቅኝት ...

ቀጣዩ የተጎዱ የቀደሙ የክ/ አገር ከተሞችን እና በአቻነት የሚታዩት ላይ ቢሆን የሚል እሳቤ አለኝ። ቢሆን ምርጫዬ ነው እንደ ማለት። ደሴ፤ ጅማ፤ አሰላ፤ መቱ፤ ድሬድዋ፤ ሻሸመኔ፤ ሙያሌ፤ ነቀምት፤ ማርቆስ፤ ደብረታቦር፤ አርባምንጭ፤ ደብረብርሃን እንደዚህ በዓመቱ መርሃ ግብር ቢካተቱ መልካም ነው። አሁን ደሴ ሰሞኑን አቶ ገዱ አንዳራጋቸው ጋር ውይይት ነበራቸው፤ ተዜትኛው ምዕተ ዓመት እንዳለች ደሴ ግራ ያጋባል። አሁንም ሜዳ ላይ ነው ጉባኤው የተካሄደው። ይሰቀጥጣል።
  • ·      ጣዝማ።

„ዙረት አበዙ“ እዬተባሉ የተወቀሱት ጠ/ ሚር አሜኑ አብይ አህመድ አፋሮችም በዚህው አሉታዊ ማዕቀፍ የነበሩ መሆኑ ተመልክቷል።  ለአዲሱ መንፈስ ባይታዋር የሆኑ ብቻ ሳይሆኑ አቅማቸው ስለተፈራ አቅማቸው ማረጋገጫ ሳይኖረው፤ ጥቂት ሰዎች ሥማቸውን ለጠጡት አንዳሉት ሆኖ ውሃ የበላው ቅል ለማድረግ ታስቦ ነው ይሄ አፍ እላፊ የመጠው። 

ለነገሩ "ሲያጣ የጦመውን" ይሉታል ጎንደሬዎች። አንዲት ስብባ በተብታ የተኖረበት እኮ ይታወቃል። በ አንድ ጹሁፍ 6 / 7 ስብሰባም ያው እዬተደገመ እዬተሰለሰ ...  ሃተታ።

ጉልቻ እኮ ለድስት መጣጃ ብቻ እንጂ ህዝብን ለመምራት ለሙሴነት የሚያሳጭ  አይደለም። አለትም ለልብስ ማጠቢያ የተፈጥሮ ጢሽትንት ነው። በሌላም በኩል ሎቱ ስብሃት ለእነሱ ፈጥሪ/ አላህ ይቅር ይበላቸው "ለጠ/ ሚር ቦታ አይመጥንም፤ ሰብዕናውም፤ ተመክሮውም፤ ተቀባይነቱም የሌለው ከዬትም አምጥተው ሊሾሙት ያሰቡት፤ ልምድ ብናኝ የሌለው፤ ህዝብ የማያውቀው፤ ተቀባይነት የሌለው፤" እንዲያውም ከሌላ መንፈስ አቅም እና ቡቃያ እንደሆነ ተድርጎ በድፍረት ሲገለጥ ነበር። 

አንድም ቀን መሬት ላይ በህዝብ አገልግሎት ያልሰራን መሪዬ ተስፋዬ ብለህ ቆልለህ ግን በተወራራሽ ሁኔታ ከራዲዮ ኦፕሬተርንት ጀምሮ ከታች ከሥር ከህዝብ መንፈስ ጋር በውል የተዋህደ እስከ ግሎባሉ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የዲጅታል ዓለም መሪነት የደረሰን አንድ ሰብዕና ቆልፎ፤ አጣባቆ፤ ያዬው መንፈስ ሁሉ የተከደነ ሲሳይ የሸረሪት ድር ሲያደራበት ውሎ እንዲያድር ምኞቱ ስለነበር ነበር "አበዛ ጉዞ፤ አበዛ ሽርሽር"የወልዮሽ መጣጠያ ወስከንቢያ የነበረው። ፍሬ ነገሩ ግን … በጥቂቱ እንዲህ ነበር ታሪክ መጸሐፉን የጻፈበት የገደል ሰሞናት …

የአገር ቤቱ ህዝብ ከመሪው ጋር የነበረው ቆይታ … ዕድማታው።

  v አዲሱ የሹመት መንፈስ እና የህዝብ ግብረ ምላሽ ሰርቨዬር ለመስራት፤ ለምህንድስና አገልግሎት ጥናት ለመውሰድ።

  v የጠፋ የእናት እና የልጅ መንፈስን በእትብታዊ ሃዲድ ለማስተሳስር። የተበተነውን መንፈስ ለማሰባሰብ። ሥነ - ልቦናዊ አቅም ለመፍጠር።

  vክፍት የሆኑ የመንግሥት እና የህዝብ ግንኙነቶችን ቆሻሻቸውን እያጸዱ በንጹህ ልብ አዲስ የመግባቢያ ሃዲድ ለመዘርጋት።

  v የህዝብን ስሜት ከመሠረቱ በውስጥነት ለማጥናት፤ ለመመርመር፤ ክህሎትንም የራስንም ለማሳዳግ፤ ዕውቀት ከማህበረሱቡ ህሊናን አለምቶ ተደራጅቶ ስለሚገኝ፤ ያን ጥቅም ላይ ለማዋል፤ ለመቀበልም።

  v ተወረራሽ፣ ወላዊ፣ ሁልአቀፍ፤ ሁለንትናዊ ችግሮችን ቋት ሰርቶ የመፍትሄ ርምጃ ለመውሰድ ከድምጻቸው፣ ከነፍሳቸው ለማጥናት፤ ከወረቀት እና ከቁጥር ዘገባ ወጥቶ ነፍሱን ከነፍሱ ለማዋደድ፤ ይሄ ረቂቅ ነገር ነው። ለምሳሌ ሁለት ቁጥር ቁጥር ነው። ግን ሁለትን ለማግኝት የሚፈጠረብት መንገድ ግን በፋክት ማህደር ነው። ዝም ብሎ ሁለት አልተፈጠረም። የሚያዳምረው አንድ ክስተት መኖር አለበት። አሁን ተዚህ ላይ ጋብቻን እና ሚስጢሩን ማሰብ ይቻላል። ሩቅ የሆኑ ፍልስፍናዎች በዚህ የአመክንዮ ማዕዶት ውስጥ ይገኛል፤

  v የተነጠሉ አካባቢያዊ ችግሮችን በአቅማቸው ልክ የመፍትሄ ሃሳብ ለማመንጨት ከመረጃ እጥረት የሚመጡ መዘናጋቶችን ለመቀረፍ፤ ለመርሃ ግብር ንድፍ ናሙና ለመሰብሰብ።

  v የተዛባውን የሃብት፣ የአስተዳደር፣ የሚዛናዊነት ችግር መሠረታዊ የመፍትሄ አቅጣጫ ለመድፈር እና የሚያዘልቅ ተግባራዊ የጥናት ናሙና ለመውሰድ፤ በህግ መሠረትነትም ለማጽናት። ይሄ ዕለትኛ፤ ሰሞንኛ፤ ወረትኛ ሳይሆን አጅግ ዘለግ ባለ ክህሎት እና ዕውቀት በሥር - ነቀል የህለና ለውጥ፤ የተደላደለ ርጉ የእችላለሁ፤ የአድረጋለሁ መንፈስ ተንጠልጣይ ሳይሆን ወላዊ አድርጎ መሠረት ለመጣል።

  v የተበተነውን የሃሳብ አመክንዮ ማእቀፉን በኢትዮጵያዊነት የውል ቀለበት ለማስተሳስር፤

  v ማግሥታዊነትን ለማደራጀት የህግ መሠረት ያላቸውን አምክንዮዎች በሁለመናነት አትኩሮት ለመስጠት፤ ህዝብ እና ህግ፤ ህግ እና ህዝብ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉም ህመም እና ህመምተኛውን የማጥናት ብሂልነትን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ። ለማከም።

  v አመራር እና ተመሪነትን፤ ፈጻሚ እና አስፈጻሚነትን፤ አድራጊ እና ተደራጊነት ተከታታይነት፤ ሚዛናዊነትና እና ተጠያቂነትን የማድርግ ባህልን ለመጀመር የሚያስችል የክህሎት አቅጣጫን ለማመንጨት፤ የምርምር ሥራ ለመሥራትም ነው። መንገዱ ፍልስፍናዊ ነው ለገባው። ከተለመደው የሆያ ሆዬ ፖለቲካ፤ ከተለመደው የግብር ይውጣ ፖለቲካ  በእጅጉ የተለዬ ነው። ጥሞናዊ ነው!
  •      አንድ ምሳሌ ላቅርብ ...ይሄንን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሶ ነቀምት የሄደው ኦፌንኮን የተጠቀመበትን መንገድ እና ህልም በፍጹም ሁኔታ የሚንድ ነው። ፖለቲካ በአጋጣሚ ግርግር፤ በሽሚያ፤ በገጠመኝ ወጀብ አይመራም። ሰው በአንድ ቀን አይፈጠረም፤ አገርም በአንድ ቀን አይሠራም። መምራት የንፋስ ወጀብ አይደለም። ኳኳቴው የዛን ሰሞኑ ይሄው ነበር። ይህን ስክነትን አውኮ የፈረሰ የገብያ ወይንም ቀዬ መናፈቅ ነበር … ህልሙም ወከባውም የነበረው። ይሄ ብቻ ሳይሆን የዛን ሰሞናቱን ግርፍ የፖለቲካ ሙቀት ስታዳምጡት አውሌያው ይሄው ነበር። እርጋታ የጎደለው፤ ስክነት የተባረረበት የጨበራ ተዝክር፤ ልትፈርስ አፋፍ ላይ ለደረሰች አገር … የቀውስ ቅርጫ ስጋ እንድትሆን ነበር የተፈለገው። ወደ ቀደመው …

  v በዬክልሉ ያሉ የበሰሉ እና ጥሬ አቅሞችን በመለዬት ኢትዮጵያ ጥሬዎችን ለጋ አቅሞችን ለማብሰል በጥናት የተመረኮዘ ቀጣይ አቅጣጫ እንድትነድፍ፤ የበሰሉትን ፍሬዎቿ ደግሞ ቦታ በመስጠት በማዋዕለ ሃብቷ ቀጥተኛ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ጠንከር ያለ የግምገማ ማህደር ነበር፤

  v የማይታዩ ግን ነገ ሊቀጥሉ የሚችሉ የችግር ፍንጮችን ከሥራቸው ለመንቀል የሚያስችል ሁኔታዎችን በቂ ጊዜ ሰጥቶ ከመሰረታቸው በጥሞና እና በአጽህኖታዊ የምርምር ሁነቴ ለማጥነት፤

  v በማለት እና በመሆን መካከል ያሉ ልዩነቶችን በማጥበብ ማለት መሆንን አሸነፊ ሆኖ እንዳይወጣ፤ ይልቁንም መሆን ማለትን አሸናፊ አድርጎ አንግሦ የሚያወጣበትን ሁኔታ ለማመቻቸት፤

  v በስማ በለው ሳይሆን በቀጥታ ከመረጃው ከመንጩ ዳታዎችን ከተለያዬ አቅጣጫ አስባበስቦ፤ ማዕከላዊ በሆነ ሁኔታ ለመምራት፤ ለማስተዳደር የሚቻልበትን ሁኔታ ለመቀየስ፤ የአማራርም -የተመሪነትም - የደጋፊነትም - የተባባሪነትም - የአጋዥነትም፤ የቅይሳ ተግባር ለመከወን።

  v በማዕከላዊ ደረጃ አቅም ያላቸው እና የሌላቸውን ለይቶ አንዘርዝሮ አቅም እና ቦታን በማመጣጠን ፍትሃዊ ማድርግ እንዲቻል እቅምን ጊዜ ሰጥቶ ለማድመጥ፤ አቅምን ለመገምገም፤ አቅምን ለመደልድል፤ አቅምን ለመሰብሰብ ሰፊ በር ከፈቱለት፤ እድሜ ልኩን ተዘግቶበት ነበር የኖረው። ይሄ እንግዲህ ለረዥም ጊዜ እኔ ስጮኽበት የነርኩበት አመክንዮ ነው። በግልም ጆሮ ያላቸው መስሎኝ የጻፍኩላቸው አንቱዎች ነበሩ ግን ልምዱ ከምን ይመታል፤ አንድ አጋጣሚ ላይ  ያወጣል እንዲህ አይነት ዓይነተ አምክንዮን ነገር ሲመጣ ወገቤን ነው።

   ልግመኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ መንፈስ አቅሙን የማያወቅ ብቻ ሳይሆን ከእጁ የገባውን አቅም የሚያሳድድ ፖሊሲ ነበር ሲከተል የነበረው። በዚህ ነው እኮ ራሱን እያሟሟ ሥም ብቻ ተሸክሞ የሚኖረው።  ኢትዮጵያ ራዕይ ጉዞም ስደት ላይ የባጀው በዚህ ነው፤ ብልሃት የሌለው ቅላት እንዲሉ። አቅም ምን ማለት ስለመሆኑ መሪዎቹ ራሳቸው በቂ ግንዛቤ የላቸውም። 

   የዛሬው ጭብጨባ ነገን ሊያስቀጥል በሚችል መልክ የመመራት የክህሎት ደሃዎች ናቸው። አቅም ፈሶ መና ቀርቶ መንኖር አስተክዞ የኖረበት የፖለቲካ ህይወት ማስቀጠል አለመቻል በልግመኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ መርህ ነበርነ። አቅምን ማሳዳድ፤ ምክሰል፤ ማክሰም። አቅም ከዬትኛውም አቅጣጫ ይምጣ ያ ማገሬ ነው የለም። ይህን ባለቤት ያልነበረው ቦታ ነው አሁን ባለቅኔው ጠ/ ሚር የተገባውን ደረጃ ሰጥተው በክብር ያነገሱት። 

   የመደመር ፍልስፍናዊ አስኳልም ይሄው ነው። አንተ ያለህን እኔ የሌለኝን ደምረን ኢትዮጵያ አቅም ያላት አገር እናድርጋት ሩቅ ነው ... ፍልስፍናው። ሌላው ደግሞ አቅም ያለው ከሚመራት እንደምንም ቢመረንን ታቱ ዥግራዎችን 50 ዓመትም እንጠብቅ እስኬዚያው ማህበረ እርኩሞች በያዙት ይቆዩልን ነው። ወይ ደግሞ አቅም ያለው ታውኮ በቃኝ ብሎ እንዲተው ከሥሩ እዬተከተሉ መበከል መንፈስን መበትን ... ተስፋ ቆራጭነትን መከብከብ። 

  v በስማ በለው ሳይሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትን አክሎ ህዝብ ምን ይላል - በስክነቱ፤ ህዝብ ምን አስቧል - በቁጭቱ፤ ህዝብ ምን ይላል - በእልሁ፤ ህዝብ ምን ይላል - ስለበደሉ፤ ህዝብ ምን ይላል - በግለቱ፤ ህዝብ ምን ይላል - በተስፋው፤ ህዝብ ምን ይላል  -በተገባለት ቃል ኪዳን የሚለውን በማድመጥ ወጥ አመራር ለመስጠት መረጃዎችን ለመሳባሰብ የልብ ለልብ ግንኙነትን ለመጀመር፤

  v አፍንግጠው እንዳይውጡ የሚፈለጉ እይታዎችን፤ አሰተሳቦችን፤ ምልከታዎችን ለማረቅ እና ለማስተካከል።

  v ኢትዮጵያን ተስፋ ያደረጉ ነፍሶች ተስፋቸውን በአቅሟ ልክ መመጠን እንዲችሉ ለማድረግ፤

  v መሪ መሪነቱን ሲወጣ ህዝብ ደግሞ የተመሪነቱን ግዴት ጋር መተላለፍ እንዳሌለበት ለማስገንዘብ፤

  v ከህግ በላይ ማንም ስለሌለ የዜጎች ህግ አክባሪነት እና ለህግ ተገዢነት መሠረቱ ማንም ዜጋ ላይ ቢሆንም፤ ቁንጮ ቢሆንም፤ አራጊ ፈጣሪ ቢሆንም፤ የህግ አምንጪ፤ አስፈጻሚ ቢሆንም ከህግ በታች እንጂ በላይ አለመሆኑ በአጽህኖት ለማስገንዘብ እና በተዛባው የፍትህ ዘመን የነበረውን ክፍተት ለመድፍን የሚያስችሉ የመንፈስ መግባባቶችን ለመፍጠር፤ የከረሩትን ለማርገብ፤ የጠነዘሉትን ለማነቃቃት። መስናዊ መስመር ለመዘርጋት።

  v ህዝብ የፖለሲ ሃሳብ የማመንጨት አቅሙን በውል እንዲጠቀምበት በተከፈተለት የህዝብ አደባባይ የዚህ ተሳትፎ ጅማሮን ለማብሰር፤

  v የሴቶችን አቅም ለመምርም፤ ለማጥናት፤ ዕውቅና ለመሰጠትም፤ ተደማጭነታቸውንም ለማሳደግ። 

  v ሰው መሆን ከሁሉ የላቀ ስለመሆኑ መርህ ስለማድረግም፤

  v ተፈጥሮ እና ሰው በክብራቸው ልክ ህሊናዊ ጥሪት እንዲሆኑ ለማስቻል፤

  v የማግሥትን ተረካቢ ርክክብ በሰለጠነ መንገድ ለመምራት የሚያስችሉ ግንዛቤዎችን ለመፍጠር። አበሶ ይሄ የሥልጣን ጥመኝነት የወረርሽኝ በሽታን መስመር ለማስያዝ - ለመቅጣት፤ የባለይ እና የበታችን፤ የጌታ እና የሎሌን ሳንኮች በቤተሰባዊ ፍልስፍና ቅጥ ለማስያዝ።

  vይቅርታ የተደረገለት ግንባር ኢህአዴግ ይቀርታ ላደረገለት ህዝብ ክብር መስጠቱን ለማረጋገጥ፤

  vይቅርታ ሰጪ ህዝብም ይቅርታ ያደረገበት መንፈስን ተግባራዊነት የሚለካበት፤ የሚሰፍረበት ሚዛን እንዲኖረው ለማድረግ። ለነገ ተጠያቂነት የዛሬው ቃል ውሎ እና አዳሩ መፈታተሽ እንዲችሉ መንገድ ለመክፈት። የተስፋ በርን ቧ አድርጎ፤ ፏ አድርጎ ለመክፈት።

  v ሳቅን ለማዋጣት፤ ፈገግታን ለመከብከብ፤ ለማጽናናት። አይዟችሁ ለማለት። ለማጠንከር።  

  v ጠ/ ሚሩ ከዚህ ቀድም የሚያውቁትን ከማያውቁት ችግር ጋር በውል ማዋህድ እንዲችሉ ብሄራዊ ዕድል ለመፍጠር።

  v ጠ/ ሚሩ ከህዝብ ለመማር ፈቃደኝነታቸውን ለማሳዬት፤
ጠ/ ሚሩ ህዝብንም ለማድመጥ ብቻ ሳይሆን ህዝብም አድማጭ መሪ ሲኖረው ግዴታው እና መብቱን በአግባቡ እና በወጉ አንዲለማመድ ለማድረግ። የፊደል ገበታዊነት። በ አናባቢ እና በተባቢ መሃከል የተመሰጠረ ውህድትን አህዱ ለማስኘት።

  v የአገልጋይነትን ጽንሰ ሃሳብ መሰረት ለመጣል፤

  vጠ/ ሚሩ የአገራቸውን ህዝብ በተለያዬ አጋጣሚ ካገኙት በላይም፤ በሚደያ ከሚዩት ከሚያደምጡት በተጨማሪ ዓይን ለዓይን፤ ገጥ ለገጥ፤ ትንፋሽ ለትንፋሽ፤ ጠረን ለጠረን ተገናኝተው የልብ ለልብ የሆነ ግልጥ እና ቀጥተኛ መስመር ለመፍጠር፤ በቅንነት - በታታሪነት - ከብረት ቁርጥራጭ በተሰራ ጥንካሬ እና ብርታት፤ እንቅልፍ አልባ ሆነው ህልም በሚመስል ሁኔታ ነበር ተልዕኳቸውን በአግባቡ በርጋታ ሲፈጽሙ የታዩት።

   ተልዕኳቸውን ለማሳከት በሙሉ የሰብዕና አቅም እና አቋም፤ ታይቶ በማይታወቅ ርህርህና፤ ቅድስና፤ ቅንነት፤ በሰላም መውደድነት፤ በእኛዊነት፤ በውስጣዊነት፤ በፍጹም ሁኔታ በማክብር፤ በደልዳለ ፍቅር፤ በልበ ብርሃን ሙሉነት፤ በፍሬያማ የራስ መተማመን መንፈስ፤ በበዛ መቻል፤ በበዛ ማድመጥ ልምዳቸውን - ተመክሯቸውን - ሃሳባቸውን -ራዕያቸውን ለማጋራት ነበር ጥቂት ቀናት ቢቀሩትም … የ100 ቀኑ ትልም በክልል ደረጃ ጉዞ አንድ ጅጅጋ ጉዞ ማጠቃለያ ሠመራ ላይ የተከወነው። 

    በማህል እጅግ ብዙ ነገሮች ተከውናዋል። ዛሬ ጉዞን ብቻ ነው ለመግለጽ ያሰብኩት። በዚህ ሂደት በየዕለቱ በሚጓዙባቸው ቦታዎች ወቅታዊ መልስ ለመስጠት ካቢናቸውም ባትሎ ነው የከረመው። ከዛ በፊት ደግሞ ተንጠልጥለው የኖሩ ገመናዎች ሲታከሉ ሰው ከሚችለው በላይ ነው።

    አንዳንድ ጊዜ ፍጡር ስለመሆናቸው ሁሉ እጠራጠራለሁኝ? ግን ዶር አብይ አህመድን እንደ ፍጡር እንያቸውን? አይደክማቸውንም? ምን ያህል ቁጭት እንዳለባቸው በባከነው ዘመን ያሳያል። መቼም ኢትዮጵያዊነት ተለጠፈባቸው ተዋሱት ለሚሉት ለ እነ አቶ ሃብታሙ አያሌው እና ለመሰሎቹ የእፍረት ዘመናቸው እንደሚሆን ነው ቀጣዩም ዘመን ...

   ለእኔ ዶር አሜኑ አብይ አህመድ ቅዱስ መንፈስ ናቸው።  በዛ ላይ የለውጥ ፈላጊ ታታሪዎች ጦሮ የወያኔ ሃርነት ፈንጅ እና ቦንም … ህሊና ካለን እኛ እና ዘመኑ ምን አንደምንመስል፤ ስለመልካም ነገር ያለን የፍልስፍና ድህነትም ግብረ ምላሹ ከመዳፍ ላይ ያለ ይመስለኛል።

የኔዎቹ ይቀጥላል … 

ውዶቼ ተከታታይ እንዲሆንላችሁ አብረን አበረን ብያለሁኝ። 

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

እልፍ ነን እና እልፍነታችነን እልፍ እናድርገው!
ኑረሉልኝ መልካሞቹ። መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።