ርትህ ክፍል ሁለት።
ርትህ።
ክፍል ሁለት።
ከሥርጉተ © ሥላሴ 30.06.2018
(ከመንኩሲያዋ ሲዊዘርላንድ።)
„ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብጹዕን ናቸው“
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭
ቁጥር ፮)
- · እፍታ
እንዴት አላችሁልኝ የአገሬ ልጆች? ደህና ናችሁ ወይ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።
ዛሬ በርካታ ነገሮች ቢኖሩም ቅድሚያ ሰጥቼ ምልከታዬን ላጋራችሁ የምሻው የአፋሩም የሠመራ ጉባኤ ጥያቄ እና የመልሱን ዕድምታ ነው።
እርግጥ ነው ይሄ መቅድም ስለሆነ ተያያዥ ነገሮች ማንሳቱ ግድ ይለኛል። የክልሎች ማሰረጊያም
ጉባኤ ስለሆነ። ምክንያቱም የጠ/ ሚር አሜኑ አብይ የመንፈስ ነፍስ እኔን እንደ ገባኝ በሁለመና የተቃኘ ንድፍ አለው። የሠመራው
ከክልል አንፃር ማጠቃለያው ነው። ቀጣዩ የተጎዱ የቀደሙ የክ/ አገር ከተሞችን እና በአቻነት የሚታዩት ላይ ቢሆን የሚል እሳቤ አለኝ።
ቢሆን ምርጫዬ ነው እንደ ማለት።
ደሴ፤ ጅማ፤ አሰላ፤ መቱ፤ ድሬድዋ፤ ሻሸመኔ፤ ሙያሌ፤ ነቀምት፤ ማርቆስ፤ ደብረታቦር፤ አርባምንጭ፤
ደብረብርሃን እንደዚህ በዓመቱ መርሃ ግብር ቢካተቱ መልካም ነው።
አሁን ደሴዎች ሰሞኑን ከአቶ ገዱ አንዳራጋቸው ጋር ውይይት ነበራቸው፤
ተዜትኛው ምዕተ ዓመት እንዳለች ደሴ ግራ ያጋባል። አሁንም ሜዳ ላይ ነው ጉባኤው የተካሄደው። ይሰቀጥጣል።
- · ክብረቶቼ።
ክፍል አንድ ላይ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ „የዙረት አበዙ“ መንፈስ አባዜም አፋር ላይም ተደምጧል።
በክፍል አንድ የጉዞውን ዓላማው አቅጣጫ በሥርጉተ ግንዛቤ አቅርቤያለሁኝ።
ቀጣዩ ደግሞ ምምን እንኳን የኤርትራ እና የደቡብ ሱዳን ገና የቀረ ነገር ቢኖርበትም። የእነሱም ቢሆን ሰሞናቱን
ባለ ቅኔው ጠ/ ሚር አሜኑ አብይ አህመድ አዲስ አበባ ላይ ታድመወበት ሰነባብተዋል። ስለዚህ ክፍ አካልነቱ ሙሉ ነው።
በኤርትራ በኩል ያልተጠበቁ (an unexpected or
astonishing event, facts) ይኖራሉ ብዬ ነው የማስበው። ምንም እንኳን ዶር አሜኑ አብይ አህመድ በቁስ ላይ ብዙም ቢሆንም ከመንፈሳዊ
ትርፉም በላይ የትውልድ ሃዲድ በጠራ የፍቅራዊነት መስመር ዘላቂ የመሰረት ድንጋዮች ይጣላሉ ብዬ አስባለሁኝ።
የቀረው መሬታቸው ላይ መገኘት ነው ደቡብ ሱዳን ላይ እና ኤርትራ ላይ። ይህም ቀጣይ ሲሆን የጉዞውን አጠቃላይ የዓላማው አቅጣጫ ግን
በስክነት ልናዬው እና ልንመረመረው ስለሚጋባ ለመነሻ የሚሆኑ ሃሳቦችን ከዚህ ቀጥዬ ለማቅረብ እሞክራለሁኝ።
ባለሚደያዎች መቼም ሃፍረት
የላቸውም ሃሳቡን እንደሚሰርቁት ይታወቃል። ነገር ግን ህልም ተፈርቶ ስለማይሆን የግድ ወጣ ገብ የሆነውን ዕይታ አቅጣጫ ማስያዝ
ግድ ይላል።
- ውጪ አገር።
በምዕራቡ ዓለም የመረጃ ቋት ወሳኝ የሆነው ጉዳይ ኢትዮጵያ ከሚጠፉት፤ ከሚከስሙት አገሮች ተርታ
የነበረች አገር መሆኗ ነው። ኢትዮጵያ ገደል አፋፍ ላይ ነበረች። እኔ ይሄን ዛሬ አይደለም የተናገርኩት በ2009 ግንቦት 7 መሥራች ስብሰባውን
ሲያካሂድ የፍራንክፈርቱ አማይን ሥብሰባ ላይ ሰብሳቢ ስለነበርኩኝ የመክፈቻ ንግግሬ ጭብጥ በዚህ ላይ ያተኮረ ነበር፤ ገላጩ አርበኛ አንዳርጋቸው
ጽጌ ነበሩ።
እንዲያውም እኮ ደፍሬ መናገር የምችለው የዛ ስብሰባ ስኬት ነው ግንቦት 7 ለወቅቱ በሁለት እግሩ
ቆሞ አውራ ፓርቲ ለመውሆን የጥርጊያ መንገዱን መሃንዲስ የሆነለት። የስብሰባው ሂደት ያው እኔ ያለሁበት ፍሬ ሥራ ሁሉ ከምድረ ገጽ
ስለሚጠፋ ዩቱብ ላይ ይኑር አይኑር አላውቅም።
በሲዊዝ የቅንጅት መሥራች
ጉባኤም የሆነው ይሄው ነው። እኔን ለማጥፋት ሲያስቡ ታሪካቸውም አብረው እንደሚያጋዩት ልብ አይሉትም ተቀናቃኞቼ። ያን ጊዜም አርበኛ
አንዳርጋቸው ጽጌ ዶር. አሰፋ ነጋሽ ገላጭ ነበሩ በቅንጅቱ፤ እኔም ትምህርት አቅራቢ ነበርኩኝ፤ ያችን ቁምነገር ከከውንኩኝ በኋዋላ
በሽታሽተሽቶሽ ትጥፋ ነው ብይኑ። የርትህ ያለህ እንላለን … ሌላው ቀርቶ ሰላማዊ ስለፉ ላይ የ እኔ ፎቶ ተቆርጦ ነው የሚቀርበው።
ግን ለመቅበር እንዳሳቡት አልተሳካላቸውም። የትም ቦታ ፎቶዬም አሻራዬም አለ። ህሊና ያላቸውም ሥርጉተ ማን ናት ለምን እንዲህ ተዘመተባት የሚለውን ከልቦናቸው ሆነው ይመረምሩታል።
ተሸጉጬላቸው ብቀር ግን ይሳካላቸው ነበር። አሁን እንኳ መሸነፋቸው ሲተናነቃቸው ማቋረጥ ፈለጉ። እነ የድል አጥቢያ አርበኞች። ግን አልቻሉም ጉግሌ ሥራውን በትጋት ጀመረ። ብቻዬን ስለምሠራም እንደ ወትሮው እንደ ጸጋዬ ድህረ ገጽ ተጀምሮ አይቀርም። አፋኞች እንደ ተሸነፉ ይቆዝሙ። ውልቅልቃቸው ነው የወጣው ...
ክብረቶቼ ...
ወደ ቀደመው ምልሰት ኢትዮጵያ አፋፍ ላይ ናት ካልኩኝ በኋዋላ ያለውን ያላችሁበት ስለሆነ ማብራሪያ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፤
በቀን 600 ነፍስ ከመቅበር እስከ 700 ሺህ ወገን መፈናቀል ተድርሷል። አዲስ አባባ ለይም ስንት ዓለም አቀፍ ሁነት በሚከውናበት
መዲናዋ በፈንጅ እና መንፈስን በመፈንቀል የቦንብ ጥቃት ለዛውም ታቅዶ ተካሄዷል። ቁልጭ ያለ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ። ለዛውም አዲስ አበባን የጦርነት አውድማ በማድረግ።
ውዴቼ እንደ ሥርጉተ ዕድምታ ሰው ሃብት ብቻ አይደለም። ሰው የሰማይ እና ምድር መፈጠር ምክንያት አንጎል ነው። ሰው ፈጣሪ እንዲያመስግነው የፈጠረው ነው።
ሰው ኬለበት ፕላኔቶችስ ስለምን ተፈጠሩ? ሌሎችም ተፈጥሯዊ ሁነቶችም ለሰው ልጅ አገልግሎት እና ደስታ የተፈጠሩ ናቸው። ስለዚህ
ባልረጋ የትውስት ንድፈ ሃሳብ የኢትዮጵያ እናቶች የሰው ብርንዶ ሲያቀርቡ ነው የኖሩት።
ስለዚህም እዬቆዬ ሲሄድ ጭንቀታችን በተለያዬ ሁኔታ እኛም ከመግለጽ አልተቆጠብንም። የዓለም ህዝብም
ጭንቁን እያዬ አላዛሯ ኢትዮጵያ ከፈረሰች ለመካከለኛው አፍሪካ አለመረጋጋት፤ የቀውስ ቀጠና መሆን ሰፊ የሆነ ስጋት ነበር። የስደቱም
ማዕበል ሌላው እንደ ጦር የሚፈሩት አመክንዮ ነው ምዕራባውያኑ።
„ሽብርተኝነትም“ ሌላው የስጋት ምንጭ ነው። በቀጠናው ጉልበታም
ተግባር የምትከውን አገር ናት ኢትዮጵያ። በዛ ላይ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የምትገኝ አገር ናት በቀጥታም ባይሆን … ስለዚህ
ይህን ስጋት ለመቅረፍ የዓለምን ዓይን፤ መንፈስ፤ ውስጥ ለማረጋጋት የውስጡን መታወክ ብቻ ሳይሆን የውጩን መታወክም ለማስከን በተወራራሽነት በትንግርት ለማያያዝ የታቀደ፤ በውል የታሰበበት፤ የሰከነ፤ ብልህ
የንጉሥ ሰለሞን፤ የንጉሥ ዳዊት ጥበብ በሚያስብል ደረጃ ነበር የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጉዞው በሚገርም ረቂቅ ሚስጢራዊ አምክንዮ የታቀደው።
የውስጡም የአገሩ እንደገናም የውጪውም ትስስር ጉዞ ወረቃማ መፍቻ ቁልፍ ነበረው። እኔ የነበረኝ ስጋት የአውሮፕላን አደጋ ሊኖር ይችላል፤ የምግብ ብክለት ሊገጥም ይችላል ነበር
ሌላው ደግሞ በቅናት ጦሮ የተናጠ ስለነበር „ዙረት አበዛ“ „መናገር አበዛ“ „ቃል ብቻ“ በማለት ነበር በግራ ቀኙ ወጀም በልገመኛው እና በሴረኛው በተለመደው ፖለቲካዊ
ትርምስምስ የተባጀው።
ለዘመናት በታቆረ Stagnate አመክንዮ ዳዴ ሲል የከረመው
ልግመኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ፖለቲካኛው አመክንዮ የወለሌ ገበታው ይኽው ነበር። የገረመኝ በባህርዳሩ ስብሰባ አንዲት እናት ገና ከመባቻው ይህን ስለ ጉዞ ሲያነሱት
ምን ያህል የተነሳፈፈ ፍላጎት እንደለን ነበር ያዬሁት። ስለሄዱ እኮ ነው ያ ዕድል የተገኘው። እይደለምን?
በዚህ ስሌት ሲኬድ እኛ ካሰብነው ውጪ ብዙ ግልጽ ያልሆኑ ያልተነገሩን ሰብሎች ተሰባስበዋል።
የዶር አብይ አህመድ መንፈሳቸው የአሮን በትር ነው - ለእኔ፤ የነኩት፤ የረገጡት ሁሉ ለምለም ስኬት ነው ማግኔት ነው። ያጓጓል፤ ይስባል። ልብ ያንጠለጥላል። መንፈስን ይገራል። በሚገርም ሁኔታ ያሳምናልም። ትዕይንት
ነው የሚመሰል። ኪኖ! ብዙው የሚያቀርቧቸው ሃሳቦች ከነበራችሁ አቋም ጋር ቁጭ አድርጎ ይሞግታችኋዋል።
ጸጋው የሚደፈር አይደለም። ግዕዝ፣ አራራት፣ እዝል
ነው ለእኔ። ለፈቀዱ የካቢኔው አባላትንም እያበቋቸው ነው። ኮትኩተው እያሳደጓቸው ነው። መቼም ከሳቸው ጋር መሥራት ዩንቨርስቲ መግባት
ማለት ነው። ታድለዋል። ዕድሉን ከተጠቀሙበት። ዕወቅታቸውን ለማከፈል ስስታም አይደሉም።
- · የውጭ ጉዞው እና ዕድማታው በጥቂቱ።
v የመጀመሪያው እና ትልቁ ነገር ኢትዮጵያዊነት ደመቀ፤ ከበረ፤ ቆመሰ፤ ቀሰሰ፤
አጬጌ፤ አሰበለ፤ ከፍ አለ መንበሩን አደላደለ። ተመስገን!
v ሥሙ
„DW ተለጠጠ“ እንዳለው ሳይሆን ኢትዮጵያን የዓለም ሚደያ አውታር አደረጋት። መቼም የኬኒያው ከሁሉም የላቀ ነበር። ኬኒያ የፓን
አፍካኒስት ቀንድነቷን ብቻ ሳይሆን የደም ሐርግነትንም በውል ሰገነት ላይ አዋለችው። በተጨማሪም የአረብ ኢሚሪቱ አልጋ ወራሽ ጠ/ ሚር አሜኑ አብይ አህመድን አራሳቸው በሚደንቅ
ክብር ተቀብለው ነበር ሾፍረው ከማረፊያቸው ያደረሷቸው።
ከወንድምነትም በላይ ነበር የነፍስነት ጉዳይ ነው። ያደረጉትም ፈጣን እገዛ
እና ግብረ ምላሹ ያው የእዮር ነው። እኔ እያንዳንዱን ቅንጣት አንቅስቃሴ ከመንፈሳዊ ጉዳዮች ጋር ነው እማዋድደው። ከዚህ የቅንነት
ወተት ጋር መንፈሴ በጽኑ የተቆራኜ ስለሆነ።
v የዜግነት ትቢያ መሆን በባዕድ መንደር ላርመጠመጠው መንፈስ ተቋርጠው የቀሩ
እጅግም ከሌላው የስደተኛ በላይ ሰቆቃ የከረመበትን አካባቢ ማስጠገን በጥረት ይጠይቅ ስለነበር ያ ነበር በፍጹም ተቆርቋሪነት ስሜት
እና ትጋት የተከናወነው።
v የአፍሪካ ቀንድን አቅም በአፍሪካውያን መዳፍ ላይ የማድረግ ረጅም እጅግም
ዘለግ ያለ የቀደመ ልበላው እሳቤን ለማሳካት ድልድዩን ለመዘርጋት ነው። በግለሰቦች እንደ ፕሮፌስር ሞሞ ሙጬ ያሉ ቅኖች ከሚያደርጉት
ጥረት በስተቀረ የህብረቱ አገሮች መሬት ላይ የመንፈስ ትስስሩን መሬት ለማዋል አልደፈሩትም። አሁን ግን ከሱዳን ኢትዮጵያ፤ ከኬንያ
ኢትዮጵያ (ከኤርትራም ኢትየጵያ ምኞት) ሊዘረጋ የታሰበው የባባቡር መስመር እና ሌሎች የትብብር ውሎች በር ከፋችነተቻው ለኢንተግሬሽን
የተስፋ ማህደር ነው።
v ኢትዮጵውያን ስደተኞች ኤርትራውያንም ጨምሮ ሲሰደዱ በመከራ ውስጥ ከሞት ሞትን
መርጠው ነው፤ የሚወጣውም ገንዘብ ልክ የለውም፤ ሶቆቃውም የዚያን ያህል ነው፤ የመኖር ተስፋውም እንዲሁ። መሸጋጋሪያ አገራት ዜጎቻቸው
የጋራ ሸንጋይ ቢዜ ከኖራቸው ደላላዩም፤ ክልትሙም፤ ህገ ወጥነቱም የኢትዮጵያ እናቶች ሰቀቀንም ከሥሩ ይነቀላል። ስለዚህ በዚህ ዘርፍ
አዲስ የአህጉራዊነት መንፈስ በመስመር፤ በደንበር በክልል ሳይሆን አስተሳሰቡም ሥነ - ልቦናውም ወርደ ሰፊ፤ ዘለግ ያለ ቁመና እንዲኖረው
ለማድረግ ነው ሃሳቡ።
አሁን በዚህ መስመር ዞጋዊነት በዓዋጅ ሳይሆን በራሱ ጊዜ ይከስማል።
ሱዳንም፤ ሱማሌም፤ ጁቡቲም፤ ኤርትራም ሄዶ መስራት መውጣት መግባት
እንደልብ ከተቻለ መንፈስ አህጉራዊነትን ፓን አፍሪካዊነትን አቀንቃኝነት
ይታትርበታል።
v የኢትዮጵያ ህልውና የስጋት ቀጠናዎችን ወደ ሰላም መስመር በማስገባት ለ43 ዓመት የነበረውን የቀጣናውን ህውከት አስወግዶ ፍቅርን ለዳመዳር፤ ለመኮል ሰላምን
ደግሞ ለማንገሥ ነው። ስጋትን ፍርሃትን ገድሎ የኢትዮጵያ እናቶችን የምጥ ዘመን እንዲከትም ለማድረግ ነው። ባለፈም ዘለግ ባለው ሁኔታ የ አፍሪካን ተውልድ ከስጋት ነፃ ለማድረግ ነው።
v አፍሪካ እያላት ድሃ አህጉር ናት። አፍሪካ በሥልጣን በሽታ የምትናጥ መከረኛ አህጉር ናት። አፍሪካ በዘረፈ ብዙ ፈተናዎች የምትማቅቅ ፍደኛ አህጉር ናት። አፍሪካ ግን ሁሉ ያላት ናት። ስለዚህ አፍሪካ አቅሟን ከሚቀሙ
ተባይ መንፈሶች ተላቀ ለህዝቧ አቅም ለህዝቧ እናት የመሆን ብቃቷን በፍቅር ለማስተሳስር ነው።
v አፍሪካውያን አንድነታቸው ከቃላት አልፎ በኤኮኖሚ፤ በባህል፤ በማህበራዊ ህይወት፤
በመኖር አብረው አህጉራቸውን ማሳደግ ማበልጽግ እንዲችሉ የመሰረት ድንጋይ ለመጣል ነው። አፍሪካዊ ሐሤትን ለማምጣት። በ እጅ አዙር የተያዙ ቅኝነትንም ሙሉ ለሙሉ ከዛ አላቆ የራስን ዕድል በራስ ለመወሰን የሚያስችል የአፍሪካዊነት ዳግም የመወለድ ዋዜማዊ ሂደት ነው።
v አፍሪካውያን የጥበብ፤ የቴክኖሎጂ ማዕከላቸውን በአህጉራችን መፍጠር እንዲችሉ
መንፈስን ለማሰባሰብ ነው። አሁን እኔ ኢሮ ቪዢን አውሮፓዊ ውድድር እጅግ አድርጌ የምመሰጥበት ጉዳይ ነው። በዚህ ዝግጅት ያሉት የሥነ ጥበብ ሥልጣኔ እና እድገት ተቋም ነው።
v አፍሪካ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን አጎልበተው ማውጣት
እንዲችሉ አቅማቸውን በአቅማቸው ለመጠቀም ፊደል እንዲቆጥሩ ለማስቻል ነው።
v መሰረቱ የዚህ ደግሞ የሰው ዘር መገኛ ኢትዮጵያ ስለሆነች የአፍሪካ ህብረቱም መዲና ስለሆነች ያ ሃላፊነቷ ዛሬ ላይ ቁልቁል እዬወረደ
ስለሆነ፤ መፍረሱ አደጋ ቢጥል ቢሮውም ወደ ኪጋሊ መዛወሩ አይቀሬ ነበር። አሁን ይህን ድርሻ ኢትዮጵያ መወጣት ስትጀምር፤ ሃላፊነቱን
ስትወስድ፤ እንደ እናት አሰባሳቢ ስትሆን የአፍሪካ መሪዎችም አቅላቸው፤ ሥነ - ልቦናቸው በቀለማቸው ውስጥ ይሰክናል ማለት ነው። መረጋጋት ይፈጥራል።
v የሁለቱ ሱዳን መልከ መያዝ መግባባት መቻል ኢትዮጵያ ለተሸከመችው የስደተኛ
ጉዳይም፤ ለወደፊት ያለውን ስጋትም ይገታዋል። በሌላ በኩል የተሰረቁ ልጆች ሁሉ አሉን። ከእትብታቸው የተነጠሉ። ይሄ ለባለቅኔው ጠ/ ሚር የልብ ቁርጠት የሆነ ነገር
ነው። ለቀጠናውም ቢሆን የተሻለ የሰላም ተስፋ እንዲያቆጠቁጥ ያደርጋል። ይሄን መፍትሄ ከሳጠች የነጭ አምላኪነት ሁሉ ይሟሽሻል። አፍሪካ ብቁ አቅም እንዳላት ዓለም እንዲያ በተጨባጭ ያስችለዋል።
v ርትህን ላጡ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች እረኛ፤ ሙሴ፤ እናት የፈጠራላቸው ታላቅ
አጋጠሚ ነበር ጉዞው። እኔ ሊንኩን አላገኘሁትም እንጂ ሊቢያ ለቀሩት ሰማዕታት አጥንታቸውን ለሀገራችው አፈር አበቃለሁ የማለት ህልምም
ዶር አብይ አህመድ እንዳላቸው ተረድቻለሁኝ። ድርብ ጭንቅላት ነው ያላቸው። እኔ ይሄን የኦህዴድ ጽ/ ቤት እያሉ ነበር የጻፍኩት።
v የግብጽ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ታላቁ ስጋት የተቆለለበት መከራ ለዘመናት
የነበረበት ዓውድ ነበር። አሁን ግን በአላህ ተምሎ ሌላ ጣጣ ምንጣጣ የለውም። ይህ ለግብጽ እና ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ህዝብም እፎይ ያሰኜ ብጡል ጉዳይ ነው። ለግብጽ
እናቶችም መረጋጋትን አድሏቸዋል።
v ባዶ ካዝና በታሪክ የተረከቡ መሪ ናቸው የፈረደባቸው። አሁን በዚህ የውጭ
ጉዛቸውም ይህን ችግር በባለቤትነት ለመወጣት መንገድ ለመክፍትም ነው። የውጪ ምንዛሬ እጥረት፤ የእዳ ክምር … የድህነት ጣሪያ ነክ
… መለያችን ነው። ግን ይሄ ሊያመን ቀርቶ እኛ ...
v የውጭ ባለሃብቶችን በመሳብ እና አፈጻጸሙን በተመለከተም በስማ በለው የሚከወን፤
በዘር ብቻ በተዋቀረው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ያልተከወነ፤ ኢንባሲው ሥራፈት ሆኖ እኛን ሲሰልል ብቻ ነበር የኖረው። ስለዚህ እርሾ አልነበረውም
ይህ ዘርፍ። በዛ ላይ የዘረፋ ውልም በስውር የድላላ ሸቀጣዊ ዝርፊያ ይከውንበታል። ሚዚናዊነቱንም የጠበቀ አልነበረም። በዘርፉ የነበረው
የቢሮክራሲ ማነቆንም ማጥናት ሌለው ብሂላዊ ጉዳይ ነበር። አሁን ግን በቀጥታ ግንኙነት ይህን የመረጃ ፍስት ቀጥቶ ወጥ እና መንግሥታዊ
ለማድረግ የሚያስችል መስመር ለመዘርጋትም ነው።
v አስኳሉ ጉዳይ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጉዳይ ነው። ከኖሩበት ዘመን በላይ
በልቅና፤ በሰላም ፈላጊነት ሪከርድ የበጠሰ ዓለም አቀፍ በቂ ሽፋን ያገኜ ነው። እኔን የመሰጠኝ ድንግልናው ነው። ኤርትራም በቅንነት
ነው የተቀበለችው። ይሄ ለአፍሪካ ቀንድ፤ ለመካካለኛው አፍሪካ፤ ለመላ አፍሪካ፤ ለሉላዊነትም እጅግ አምርቂ ውሳኔ እና ተስፋ ሰጪ
የምስራች አውድ ነው። በዚህ ውስጥም የኤርትራ እናቶች እፎይ ይላሉ። እነሱም መከረኞች ናቸው። የወሉ ቤተሰባዊ ዕሴት፤ ማህበራዊ
ዕሴት፤ ባህላዊ ዕሴት፤ ሃይማኖታዊ ዕሴት ታማው ነበር። አሁን ግን መፈወሻ መዳረሻ ላይም ናቸው።
- · የ21ኛው የህሊና ሰብል በፓን አፍሪካኒዝም ህይወታዊነት።
በዴፕሎማሲው ዘርፍ የ21ኛው ምዕተ ዓመት የህሊና ሰብል ሊባል ያስችለዋል። በተለይ የኤርትራ
እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ቁርሾ የመከነበት ንጽህናው ከድንቀነሽ በላይ ነው። በአፋሩ ጉባኤ ላይ „ሰው የተበጃበት ምድር“ ብለውታል
ጠ/ ሚር አሜኑ አብይ አህመድ። እኔ ደግሞ ይህን የዲፕሎማሲ ትርፍ ፍቅር የተበጀበት ልበለው።
ሌላው የግብጹ መቼም ከልጅነት እስከ አውቀት ግብጽ የኢትጵያ የስጋት ምንጭ ሆና ነው የኖረች፤
ሊያጠቁን የሚሹትም የመንፈስ ድልድያቸው ግብጽ ናት „እስኪ በኣላህ ማልልኝ“ የመንፈስ
ቀለበት ዘውድ የደፋበት ነበር። የኬኒያው የኢትዮጵያ ክብር ወደ ሰማይ ያረገበት ነው።
በእጅ
ዬያዙት ወርቅ ከመዳብ ቁጥር ነው ሆኖ ነው እንጂ በዘመኔ ሐሤት የሚባለውን እውነተኛ ደስታ ጋር የተገናኘሁበት ነው ማለት እችላለሁ።
ድሃ በመሆኔ ብቻ፤ ላደርገው የምችለው የሌለኝ በመሆኔ ብቻ እንጂ እኔ ሳልሆን መንፈሴ እንደገና ተወለደልኝ ማለት እችላላሁኝ። ይህን
የፍቅራዊነት ሰብል ለማዬት ያበቃኝ አምላክ የተመሰገነ ይሁን። „አሜን“
ኡጋንዳ ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ ተሸላሚ ነበረች። በክብረ በ እላቸው ላይ ይህን ግርማ እና ሞገስ የ ኡጋንዳ መንግሥት ህዝብ ለኢትዮጵያ ሲያስብ ሌላ የኤዶም ገነት ነበር።
እኔ ስፈጠር ለሌላ አጀንዳ አልተፈጠረኩም። ለአገሬ አጀንዳ ነው የተፈጠርኩት። የፈለገ ፈተና
ቢገጥመኝ እማላኮርፍበት፤ አንግቴን ደፍቼ እማልሰወረበት አመክንዮ ቢኖር የነገረ የኢትዮጵያ ሁለመና ነው። የደቡብ ሱዳንም ቅንጣት
ጥርጣሬ የለኝም ዶር አብይ አህመድ የአመራር እገዛ በማድረግ፤ ጥበብን በማጋራት፤ ብልህነትን በማካፈል፤ ሆደ ሰፊነትን በማቅናት፤ አመራሩን አንድ
ያደርጉታል ብዬ አስባለሁኝ። ስለምን? ቅዱስ ናቸው። ተመርቀዋልም፤ በቃሽ ብሏታል እማማ አፍሪካን።
„ዙረት“ ከሊቅ አስከ ደቂቅ በሚሄዱበት የሚነሳ ዲያስፖራውም ሲያብጠለጥለው የባጀው ዙረቱ እና
ዕድምታው በጥቅሉ በጥቂቱ ይህን ይመስላል። ርትህን በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቀጠናውም፤ በአህጉሩም ማማጥ ያስፈልግ ነበር። ስለዚህ
የጠ/ ሚር አሜኑ ጉዞ ርትሃዊ ነው
… በዓለም ሚደያ ኢትዮጵያ በስንት ወራት ውስጥ ነው ትነሳ የነበረው ለዛውም በአሉታ፤ አሁን እኮ ልክ እንደ ሃያላን መንግሥታት መሪዎች ነው እዬተነሳች ያለቸው። የእልልልልልልታ ዘመን ነው። ክብሯ፤ ልዕናዋ፤ የሰው ልጅ መገኛነቷ ጉመለናዋ እንደጸሐይ ብርሃን ፏ ፍንትው እያለ ነው። ተመስገን።
በሌላ በኩል በሰባአዊ መብት የአያያዝ ሂደትም የተከበረ ሪፖርት ነው የቀረበው። ከተጠበቀው በላይ የሆነ ንጹህ መንፈስ እንዳለ ነበር ሪፖርቱ በአድናቆት የዘገበው።
- · ውዶቼ።
የኔዎቹ ይቀጥላል … ተከታታይ እንዲሆንላችሁ አብረን አበረን ብያለሁኝ።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
እልፍ ነን እና እልፍነታችነን እልፍ እናድርገው!
ኑሩልኝ መልካሞቹ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ