ቅኝቴ ነሽ!
„እኔ ብናገር ህመሜ አይቀንስም፤ ዝም ብል ከእኔ አይወገድም።“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፮) ሥርጉተ© ሥላሴ 28.07.2018 (ከዝምተኛዋ ሲዊዝ) ይህ ፎቶው ያነሳችኝ መምህሬ ናት - የሥነ ጹሁፍ ክፍለ ጊዜ ላይ፤ ለሦስት ተከታታይ ዓመት በሳምንት አንድ ቀን አንድ የስደተኛ መጋዝን ዝግጅት ውስጥ ከነበረው ቡድን ጋር እሰራ ነበርኩኝ፤ ያው በነፃ ማገልገል እግረ መንገድም መማር ስለሆነ። ለመጽሄቱ የመጀመሪያውን የሥነ - ግጥም አምድ ያስጀመርኩት እኔ ነበርኩኝ። ከዛ በኋ ዋላ ነበር መምህሬ እና አለቃዬ የዓለምን ዕውቅ የሥነ ግጥም ባለቅኔዎች ማሰስ የጀመረቸው። ሌላው አለቃዬ ሁልጊዜ ስትናገር ሥርጉተ ተማሪ ብቻም አይደለችም ባልደረባዬም ናት ትል ነበር። ብዙ ጌዜ መጋዝኑን እርእስ እኔ እረዳት ነበር፤ ለይ አውቱንም፤ በተጨማሪም ኬኒያ ለሰባዕዊ መብት ጉባኤ የሄደችው ዋና አለቃችን እኔን የሚያውቅ ሰው አግኝታ ዝርዝር መረጃውን በኢሜል ስትልክላት የነበራት ደስታ ይህ ነው አይባልም። አልናገረም ነበር እኔ ምን እንደነበርኩኝ። መረጃ የሰጣት ወንድሜ ሙሉ ስብዕናዬን እና ተመክሮዬን ነበር። የቅርብ አለቃዬ እና መምህሬ የልጆች ጋዜጠኛ ነበረች። አሁን ሌላ ፕሮጀክት ውስጥ ነው የምትሰራው። እኔን ወደ ልጆች ራዲዮ አዘጋጅነት እንዳተኩር ያደረገኝም የእሷ ተመክሮም ጭምር ሲሆን ለኢትዮጵያ የነፃነት ትግል ብዙ ደክማለች። መረጃ በማሰባሰብ እረግድ ብቻ ሳይሆን በመሰጠት እረገድም። አብሶ በስብዕዊ መብት ረገጣዎች ጉዳዮች ላይ ሰፊ አትኩሮት አላት። እኔም በብዙ ሁኔታ አግዛኛለች። ቤቷ ስሄድ እንደኛው ባህል አልጋዋን ለቃ እሷ ከታጣፊ አልጋ ተኝታ ታስተናግደኝ ነበር። እሩቅ ግን በሽኝት ሄጄ...