ቆሞሳት እና ቅናዊ ምዕራፍት!
የቆመሱ ፈቃደ ተክለማርያም „ስንብት“ በፈቃዱ የሰላም ሐዋርያነት ነው። „የቀደሙት ነብያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፣ --- የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፣ --- ከክፉ መንገዳችሁ እና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤ እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ ይላል እግዚአብሄር።“ (ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ©ሥላሴ 02.08.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) v ልመና። እጅግ የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች ትንሽ ለዬት ያለ እድምታ ስለሆነ በጽሞና ትከታተሉት ዘንድ በዘንካት ትሁት መንፈስ እጠይቃችሁ አለሁኝ፤ እኔ ሎሌያችሁ ሥርጉተ ሥላሴ። v መካሄጃ። ዛሬ ደግሞ የቀብር ሥርዓት አለ። ማልቀስ ግን አይገባም። ማንባትም አይገባም። ይህን ሳለደርግ፤ ይህ ሳይሆን ሊባልም አይገባም። ይህ ሊሆን ግድ ያለበት እዮራዊ የሚስጢር ዕድምታ ስላለው። የመጨረሻም ቢሆን ስንብቱ ግን እዬራዊ ሥራ አለበት ስለሆነም እባካችሁን ሃዘኑን በልክ አድርጉት። ታላቅ መነኩሴ ነበር። ቆምሶ ኖሮ ነው፤ ቆምሶ ነውም ያለፈው። የኔዎቹ ግራ አይገባችሁ እገልጠዋለሁኝ የሚሰማኝን። ሰማዕትነትን ዘመኑ ፈቅዶታል። ሁለት ሰማዕታት ሰኔ 16 ቀን፤ በወሩ ሀምሌ 19 ሌላ ሰማዕት፤ የተክልዬ ጊዮርጊስ ለተክልዬ ሌላ የሰማዕትነት ዜና አዲስ አበባ አስተናገደች። ጸጥ ረጭ ብላ የባጀቸው አዲስ አበባ ሁሉንም በዓይነት እያስተናገደች ነው። ተደሞን ለተደሞ ጊዜ ከተሰጠው። v ትውስታ። ታስታውሱ ከሆነ ማን ጠ/ ሚር ይሁን በሚለው ላይ የዶ...