ቆሞሳት እና ቅናዊ ምዕራፍት!

የቆመሱ ፈቃደ ተክለማርያም „ስንብት“ በፈቃዱ 
የሰላም ሐዋርያነት ነው።


„የቀደሙት ነብያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፣
--- የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፣
--- ከክፉ መንገዳችሁ እና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤
እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤
እንደ እነርሱ አትሁኑ ይላል እግዚአብሄር።“
(ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፩)

ከሥርጉተ©ሥላሴ
02.08.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)

   v   ልመና።
እጅግ የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች ትንሽ ለዬት ያለ እድምታ ስለሆነ በጽሞና ትከታተሉት ዘንድ በዘንካት ትሁት መንፈስ እጠይቃችሁ አለሁኝ፤ እኔ ሎሌያችሁ ሥርጉተ ሥላሴ።

  v   መካሄጃ።
ዛሬ ደግሞ የቀብር ሥርዓት አለ። ማልቀስ ግን አይገባም። ማንባትም አይገባም። ይህን ሳለደርግ፤ ይህ ሳይሆን ሊባልም አይገባም። ይህ ሊሆን ግድ ያለበት እዮራዊ የሚስጢር ዕድምታ ስላለው። የመጨረሻም ቢሆን ስንብቱ ግን እዬራዊ ሥራ አለበት ስለሆነም እባካችሁን ሃዘኑን በልክ አድርጉት። ታላቅ መነኩሴ ነበር። ቆምሶ ኖሮ ነው፤ ቆምሶ ነውም ያለፈው። 

የኔዎቹ ግራ አይገባችሁ እገልጠዋለሁኝ የሚሰማኝን። ሰማዕትነትን ዘመኑ ፈቅዶታል። ሁለት ሰማዕታት ሰኔ 16 ቀን፤ በወሩ ሀምሌ 19 ሌላ ሰማዕት፤ የተክልዬ ጊዮርጊስ ለተክልዬ ሌላ የሰማዕትነት ዜና አዲስ አበባ አስተናገደች። ጸጥ ረጭ ብላ የባጀቸው አዲስ አበባ ሁሉንም በዓይነት እያስተናገደች ነው። ተደሞን ለተደሞ ጊዜ ከተሰጠው።

  v   ትውስታ።
ታስታውሱ ከሆነ ማን ጠ/ ሚር ይሁን በሚለው ላይ የዶር አብይ አህመድ ወደ ፊት መምጣት አስመልከቶ ሰፊ ጫና ነበር። ቀድመው ዶር ለማ መገርሳን የማይደግፉት የነበሩት፤ "ኢትዮጵያዊነት ሱስ፡ ምናቸው ያልነበረ፤ ለነገሩ "ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው" የእኔ አጀንዳ ብቻ ሆኖ የቀረም ይመስለኛል እራሳቸው ዶር ለማ መገርሳም ሲያነሱት ሰምቼ አላውቅም። ታላቅ እቀም የነበረው የተጋድሎ ምዕራፍ የከፈተ ዋዜማ ነበር። ግን ስለምን ተውት? 

... ግን የታማሩ ሞገድ ያስነሳው ይሄው ነበር። "ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው።" እርግጥ ነው "መደመር" የነገሰው በ አዋሳው ጉባኤ ነበር ኢትዮጵአዊነት ሱስ ነው የተጸነሰውም በዚኽው መንፈስ ወስጥ ነው። ጽንሱ የተወለደው ደግሞ ግዮን ላይ ነበር። ያ "ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው" የተጠለፈበት ሞገዱ ልብ ያለው የለም እንጂ፤ ልሙጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማን መንፈስ ያነገበ ነበር፤ አገር ልጠትጣፋ ነውና ተነሱላት ነበር አውጃው። በዛ ውስጥ ነበር እድምታው። ያ ያለውን መንፈስ ያህል ማንም የለውም። በነገራችን ላይ ባድመ ደንበር ላይ ተውለብልቦ ያየሁት ይህ ሰንደቅዓላማ ነው።  አሸናፊ መንፈስ ሰው ሰራሽ ጉድብን ጥሶ መውጣቱ ደግሞ ነገ አይቀሬ ነው።

የሆነ ሆኖ ያን ጊዜ የዶር ለማ መገርሳ ወደ ፊት መምጣት ያልተማቻቸው በተቃውሞ ሰምጠው የቆዩት፤ ዶር አብይ አህመድ ወደ ፊት ሲመጡ ግልብጥ ብለው ደግሞ የዶር ለማ መገርሳ ደጋፊ ሆነው አረፉና በመከረኛው የዶር አብይ አህመድ መንፈስ ላይ እጅግ የተጠናከረ፤ እጅግም የተደራጀ ዘመቻ ከፈቱ። ከለማ መንፈስ ሊነጥሉት ተጉለት። ያም በራሱ የራሱ የሆነ መንፈስ ነበረው።  

ለዛ መንፈስ ዕውነት ለመናገር የተጋው፤ ሞጥሮ የታገለው አማራ ብቻ ነበር ነጥሮ ወጥቶ ሎቢ ላይ ሲሰራ የነበረው። ውግዝ ከአርዮስ የተባለው የአብዩ መንፈስን በለወጥ ፈላጊው መንፈስ ውስጥ እጅግና በፍጹም ሁኔታ የተገለለ ነበር። የዶር አብይ አህመድ ወደ ፊት መምጣቸው ያሰጋቸው ወገኖች ጥቅልል ብለው የዶር ለማ መገርሳ ደጋፊ ሆኑ እስከሚገርመን ድረስ፤ ግን ይህም የእብለት ነበር። ዶር አብይ አህመድ  "አስመሳይ" ነው፤ ዶር ለማ መገርሳ ደግሞ "ታማኝ እውነተኛ" ነው በማለት ፊት ለፊት ወጥተው ሲታገሉ  ሙግት ላይ ነበርኩኝ። 

ያን ጊዜ ብቸኛ ተሟጋቹ የእኔ ብዕር፤ የሳተናው ብራና ብቻ ነበር። ሳተናው የዶር አብይ አህመድን ሰብዕና የሚገልጹ የቀደሙ ንግግሮችን በመለጠፍ ያሳዬው ቅንነት ወደር አልነበረውም። እኔ የሚገርመኝ ፍጥነቱ እና ቅንነቱ ነበር። ምንአልባትም በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ እንዲህ ከስሜት ርቆ ለእውነት የወገነ የእውነት ታማኝ የሆነ ብቸኛ ሚዲያ ብለው አላፍርበትም። እንዲያውም ደጋፊው ሲሳሳ እጅግ ያዝን ነበር። "እኔ በእርምጃቸው እዬተደስትኩ ነው ግን ቁጥራችን እዬቀነሰ ነው፡ ይለኝም ነበር። አብሶ ትግራይ ላይ በነበረው ሁኔታ የተፈጠረው ህውከት እጅግ ፈታኝ ነበር። እኔም አይዞህ እለው ነበር።

እስታውሳለሁኝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ውስኔ ላይ ዶር አብይ አህመድ አልተገኙም ነበር። ያም ትልቅ አጀንዳ ነበር። የሚገርመው ከዛ በፊት የብሮድካስት ስብሰባ ላይ በሳቸው ደረጃ የነበሩት ሳጅን አለምነህ መኮነን ሲገኙ ዶር አብይ አህመድ ግን አልተገኙም ነበር፤ ያ አጀንዳ አልነበረም። ዳግማዊ አባ ኮስተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተገኝተው ኦቦ አዲሱ ረገሳም ስለምን አልተገኙም አጀንዳ አልነበረም። ይህን የማነሳው የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሴራ መረቡን በምን መልክ ለማያያዝ እንደሚታሰብ ለማሳዬት ነው። ወደፊትም ገና ያልሰከኑ ጉዳዮች አሉና ጥራት የትጋት እና የጥራት ብቻ ሳይሆን የጊዜም ጉዳይ ነው። ይህን ፈተና ብንሻገረውም ሌላ ደግሞ ይገጥመናል ... 

የሆነ ሆኖ ለሴራዊ አጀንዳችን አጋዥ ካልሆነ ወሳኝ አማክንዮ ለማመሳከሪያነት ለሙግት አይቀርብበትም። ለሙግት ፊት ለፊት የሚቀርበው ለማጥቆር የተነሳነው ሃሳብ ደጋፊ ጭራ ከተገኜ ብቻ ነው። ለእኔ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውሳኔ ላይ ዶር አብይ አህመድ አለመገኘታቸውን ከብሮድ ካስት ስብሰባ አለመገኘት ጋር አገነዛብኩት። ስለዚህም አቅም አላፈሰስኩበትም። 

ስለዚህ አጀንዳዬ አልነበረም። ለማጮኽ ሲሆን አፍራሽ አምክንዮ የሚለቀምበት ለማብረድ ሲሆን ገንቢ አመክንዮ የሚወረወርበት ዘይቤውን አሳምሬ ስለማውቀው። መጋለብ አልተመርኩትም በፖለቲካ ህይወቴ። አንድ ሌላ ተጨማሪም ልከል፤ ከዛም በፊት መቀሌ ላይ ቅልጥ ያለ ኮንፈረንስ ነበር የገዱም የለማም መንፈስ ውክል አካል ትውር አላለም ነበር። 

እነኝህ ሁሉ ጭብጣቸው ፍሬ ነገር ነበራቸው፤ ግን አቅል ስሌለ፤ በንፋስ ሞገድ በሚራው  ኢትዮጵያ ፖለቲካ  ሁሉንም  በአንድ ሙቀጫ ሲሰለቅ አቅም ባልተገባው መንገድ ባከነ፤ ትውልዱም መንፈሱ ተበተነ። ያ ሞገድ ኢትዮጵያ ወደ አልታወቀ አቅጣጫ እንድትሄድ እጅግ ሰፊ ጫናም ነበር፤ የለማ ገዱ መንፈስ ከሚያሸነፍ ሁሉም ገደል ይግባ ዓይነት ነበር። ይሄ የፖለቲካ አስተሳሰብ ፍሬ ነገር የሚባል ቦታ የለውም፤ ለነገሩ አመጣጥ ይወስናል … ደንገቴ ነው ሰውን ሁሉ አክቲቢስት እና ጋዜጠኛ ያደረገው፤ ካልሆነም …

  v   ካልሆነም፤
በዛው የጠ/ ሚር እጩነት ውድድር ጊዜ የተፈለገው ደካማ ሰው ተመርጦ በዛው ስሞታ ተቀጥሎ በጫና ወደ አደራ መንግሥት የማምራት ዝንባሌ ነበር በነፃነት ፈላጊው ሲቀነቀን የነበረው። ለውጥ ተፈልጎ ለውጥ ተፈርቶ ማለት ነው።
 በሌላ በኩል ደግሞ የወያኔ ሃርነት የማንፌስቶ ማህበርተኞች ደግሞ ከተሳካ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፤ ካልሆነ ደግሞ አቶ ደመቀ መኮነን እንዲሆኑ ምርኩዛቸውን ሁሉ ይዘው ጉባኤው ላይ ታድመው ነበር። 

በዚህ ሁኔታ ላይ ነበር ሞያሌ ላይ ወደ 50 ሺህ ህዝብ መፈናቀል የተከሰተው። ሰፊ የሆነ የስደት ፍስት ወደ ኬንያም የነበረው። ያ ትልቅ ፋሲካ ነበር አዲሱን መንፈስ በሽታሽቶ አጋልጦ ለመጣል። በዚህ ውስጥ ኦህዴድ ከዓላማው ላይ ቸክሎ ንቅንቅ ሊል አልተቻለውም። የፖለቲካ አቅም ማለት ይሄው ነው። አውሎ በተናሳ ቁጥር ሸሽጉኝ የማይል … ወንዳታ!

ከዚህ ቀደም ብሎ የተዋቂው የጥብብ አባወራ የቆሞስ ፈቃዱ ተክለማርያም ህምም እና የእርዳታ እጅ ተጠይቆ ነበር። በውጪም፤ በአገር ውስጥም ያለው ወገን በአንድ መንፈስ በቅጽበት ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ፤ ካለምንም ሲናርዮና፤ ካለምንም ፖለቲካዊ ድርድር፤ ካለምንም የልዩነት መንፈስ ራሳቸውን ለመስጠት የፈቀዱ ቅኖች በአንድ መንፈስ ሊደረግለት የሚጋባውን የፍቅር ታማኝነት በገፍ  ለቆሞሱ አበረከቱለት። ይህ ዘመን ቅንነት እንደገና የተወለደበት ዘመን ነው። 


ይህን እንዲይ ነበር ለቅኑ ቆመስ ያን ሁኔታ የተፈጠረለት። ያ ልብ ያለው ሰው ስላልነበረ እንጂ ቅንነት ምን ያህል በኢትዮጵያ መሬት ጥማት እንዳለበት የታዬበት አጋጣሚ ነበር። አሁን ኢትዮጵያ የቅንነት ሥነ - ምግባር  እንደገና የመወለድ ዘመኗ ነው።

በሦስት በታመቁ ስሜቶች ፖለቲካው ይናጥ የነበረው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ረግጦ የመግዛት ፍላጎት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለፈስፋሳ ሰው ተመርጦ ያን በማሳጣት ስሞታዊ አብዮት እንዲካሄድ የዶር አብይ አህመድ መንፈስ ወደፊት እንዳይመጣ ሰፊ የሆኑ የፖለቲካ ውዝግቦች አደባባይ ላይ የወሉበት ጊዜ ነበር። በዚህ ማህል ነው መቀሌ አቅርቢያ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ የተደመጠው። ሌላ ቦታም የተደገመው ውጥሩት በማዬሉ ነበር።

እኔ ምልክቱን አንስቼ ፃፍኩኝ። ፈቃዱ ጸጋዬ መብራቴ በአንድ ላይ ሲሆኑ መጪው ጊዜ ጥሩ እንዲሆን እዬተነገረን ነበር። የኖረ ኖሮ ቆመስ ፈቃዴ ተክለማርያም ህመም እና የህዝብ ፍቅራዊ ምላሽ በሌላ በኩል የተኖረ ተኑሮ መቀሌ አቅርቢያ የመሬት መራድ አገጣጥሜ ከእግዚአብሄር የሆነ ነገር ነበረው። ስለዚህ ግራቀኙ አደብ ግዙ ብዬ ጻፍኩኝ። ሰሚ አልነበረም።

https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_25.html
ምልክት

የጠ/ ሚስተሩ የስሜን አሜሪካ ስፖርት ፌስተባል ላይ ለቀረበው ጥያቄ  በመላጣ ዕቅድ ነበር። መንፈስ ቅዱስ አልጎበኘውም። ከፈቀደው ይሆን የማይጠቀማቸው ከሆነም ይቅር ብዬም ጽፌለሁኝ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን የለመደበትን የተቃውሞ ጹሁፍ ሲጽፍ፤ ግብዣ ሊደረግላቸው አይገባም ብሎ ሲሞግት። ያን ጊዜ ሰላማቸውን ባጡት ሁለቱ አንጋፋ ሃይማኖቶች በእስልም እና በኦርቶደክስ ሃይማኖት እና በቤተ መንግሥቱ ምንም የመንፈስ ቅድመ መሰናዶ አልነበረም። ያላተሰካውም ለዚህ ነበር። 

ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን እና መሰሎቹ ያስነሳውም ለዚህ ነበር ልዑል እግዚአብሄር ሚስጢራትን ሊያሳያቸው ስላልፈቀደላቸው። ስለምን? የራሱ ንጹህ ጊዜ ስለነበር። ንጹህ ጊዜው ሲመጣም አሁንም ጋዜጠኛ መሳይ ተነሳ እንዴት ከእነሱ ጋር ብሎ? ግን አቅም አልነበረውም መልዕከቱ? ስለምን? ያቀዱት ዲያቢሎስን የሰበሩ ቅኖች ስለነበሩ። ስለዚህ አሸንፎ ወጣ።

አሁን ይህ የአሜሪካን ጉዞ የጠ/ ሚሩ በገሃዱ ዓለም ትርጓሜ ማህበረሰባቸውን ለማገኘት ነው። የጋሼ ፈቃዱ ተክለማርያም የህመም ዕወጃም ገንዘብ ለማሰባሰብ ነበር። እኛ ፈጣሪ የሚለውን ረስተነዋል። ለገሃዱ ዓለም ተልዕኮ ቢሆንማ ቆሞሱ ፈቃዱ ተክለማርያም ውጪ አገር ሄዶ ታክሞ ድኖ ቁሞ እናዬው ነበር። ያ ሞገድ የሰጠው ምልክት ነበር ቅንነት መሪ ከሆነ እርቦንም ራሳችን ለመስጠት የሚያስችል አቅም እንዳለን ለማመላካት ነበር። ደወሉ ያ ነበር።

አሁንም ብዙ ነገሮች በዚህ የአሜሪካ ጉዞ ሲባል አዳምጣለሁኝ። የልዑል እግዚአብሄርን ታማራታዊ ትንግርት እዬተሳተ። የሆነው ግን በሁለቱ ሃይማኖቶችን ለማቀረራብ ቅንነት እንደገና የተወለደበት የልዑል እግዚአብሄር ጥሪ ነበር። ሁለታችሁም የቤተመንግሥቴ አጀንዳ ናችሁ በማለት ጥረት ተጀመረ ቀድሞ አገር ቤት። እዛው መሬት ላይ መለምለም ተበጀ። 

የቀረው አያያዥ የተግባር መቅኖ ነበር። ስለዚህ ቅንነት አሜሪካ ገባ። አስቡት ከልብ ሆናችሁ ውዶቼ፤ ፈጣሪም ሚስጢር እንዲገልጽላችሁ ተማጸኑት። ብዙ ነገሮችን በመንፈስ እንድትኖሩበት እማጸናለሁኝ። በሰውኛ የሚታዩ ነገሮች ካቢኔው ውስጥ የሉም ማለቴ አይደለም፤ ይህ በቀጣይነት እምሞገትበት ነው። ይሄኛው ግን በፍጹም የተለዬ ነው፤፡

የሰላም ፋውንዴሽን ጉባኤ ላይ ያ ቅን መንፈስ ተገኜ። በምን ስሌት? በምን ቀምር? ካቴናን ያሸነፈ ነፍስ የተገኘበት ጉባኤ ይህን ቀን አስቀድሞ አቀደው። ሚስጢር አለበት። የተቋረጠው መቅኖ ውህድ ሆነ አገር ቤት እና ውጪ አገር። የተበተነው መንፈስ ተያያዘ። ከዚህ ላይ በጥርጣሬ ውስጥ የነበሩ የሁለቱ አንጋፋ ሃይማኖቶች ኢትዮጵያዊ ቀለም ህብርነት ሰማያዊ ስለመሆኑ መስካሪ አያስፈልገውም።

ሌላው የቅድስት ተዋህዶ ነው። ቅንነት ማረፍ አልፈለገም። ሄደ እና የቅድሚያ የለሞችን ግንኙት በውህድነት በአክብሮት በአንክሮ አመሰገነ። እንዲያውም የተባባሩት መንግሥታት ድርጅትን በድፍረት ወቀሰ። የሰላም መሠረት የሆነችው ቅድስት ተዋህዶ ታምሳ አጀንዳ በዓለም ዘንድ አለመሆን እጅግ ውስጥ ያቆሰለ ስለመሆኑ ሁላችንም እራሳችን እንድንጠይቅ በሚያደርግ መልኩ ውስጣችን ቅንነት እንዲያበቅል አደረገ። „ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገር ናት“ አለን። "ሰላም" ናት አለን።

 የጥል ግድግዳ የማፍርስ አቅሟን በድፍረት ገለጸ። ይህ በሰውኛ የሚተረጉሙት አይጠፉም። እራሱ ቃለ ምህዳኑ በዬቦታው ካልተበተነ ሰላም የማያገኙ፤ ያልታዳሉ ነፍሶች አሉ። ቃል እኮ ካለቦታው ከሆነ አያምርበትም። እስኪ መስጊድ ሄዶ "ቅደስት ተዋህዶ አገር ናት" ይበል ያሉትን እያዘንኩኝ አዳመጥኩኝ፤፡ ካለቦታው፤ ከለልኩ፤ ከላክብሩ ከሆነ ገበርዲኑም፤ ከረባታውም አያምርም። ከመንፈስ የተላከ መንፈስ በፈቀደለት ቦታ ብቻ ነው አደንደበቱ የሚከፈተው። ቃናው እራሱ ልዩ ነው። እስኪ የባዕለ ሹመቱን ንግግር እና ከዛ በሆዋላ የተደረጉትን እጅግ በርካታ ንግግሮችን ሁሉ መርምሯቸው ድምጹን በፍጹም አይገናኝም። የቅርቡን የሎሳንጅለሱን አዳምጡት ... በጹሁፍ ነበር።  

„ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገር ናትን“ ሰላም ፋውንዴሽን ጉባኤ ላይ ስለምን አልተነገረም የሚሉ ነፍሶችንም አዳምጫለሁኝ። አብይ ፈርቶ ነው? እኔ እንዲያውም ይገርመኛል ድፈረቱ እና በራስ የመተማመን አቅሙ። ልቡ ያሰበውን ሳንሱርድ ሳያደርግ ነው የሚናገረው። ፕሮቴስታንትም አማኝ እንደሆኑ ነው የሚነገረው እና ይህ አንደበትን ከፍቶ ያናገረ መንፈስ እንደ ሰውኛ ባንተረጉመው መልካም ነው። ሊቃውንተ ቤተክርስትያን እኛ እንኳን አልደፈረነውም ነው ያሉት በቅደስት ስላሴ ካቴድራል ትናንት በ አደባባይ። ቅድስተ ተዋህዶ መሪዬ ሙሴዬ ብላዋለች ይህን መንፈስ። … ካለ መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የማይደፈሩ ተደሞዎች አሉ።

  v   ሰንበት ሲያምርበት።

ለነገሩ አሜሪካም ቅድስት አገር ናት። ልዑል እግዚአብሄር የፈቀደላት ነገር አለ። መድህን የሆኑ ታላቅ ሉላዊ ተግባራት ነበር ሰሞናቱን ያሰተናገደቸው። እንደ እግዚአብሄርኛው። ለምሳሌ ዘመኑን „አስላምን እያጠፋው ያለው እስላም ነው“ ታላቅ መርኸዊ ጉዳይ ነው። 

ይህን የዓለም ሰላም ወዳድ ህዝቦች ቢተረጎምላቸው ይህን መንፈስ እጬጌ ለማድረግ ደቂቃ አይፈጅባቸውም። እኔ „ህሊና“ በሚለው ጹሑፌ ላይ  ለኢትዮጵያ የክርስትና አማንያን ስጋት ከእንግዲህ እንደማይኖር ማጠቃለያዬ ላይ ጽፌው ነበር። አብይ የብዙ ሉላዊ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ ነው። ከውስጥ ከተቀበልነው። የማከብራችሁ ጊዜ ሲኖራችሁ ያነሰሁዋቸውን ነጥቦች መርምሯቸው። 

ግንቦት 1 ጀምሮ ስበስቡን ሰርቼ ቀንበጥ ላይ አስቀምጬላችሁአለሁኝ። አንድ ደሃ ትቢያ ላይ ያለ ነፍስ፤ ለዛውም ሴት ማን ያዳምጠዋልና … ያ ቢሰማ አሁን መሬት ላይ የሚያስነጥፍ ነገር ባልኖረ ነበር … ሰው ለሚዛን ነው የተሠራው። ግን ሚዛኑን ስቶ ወጀብ ሲመራው ደግሞ ይከብዳል። በ አሉታዊ ውስጥ ሊዘልቁ የሚፈልጉት የራሳቸው ሰብዕና ስለሆነ መጋፋት አልሻም ... ዛሬ ገብቶናል ስለሚሉት ነው እኔ የምናገረው ... ጥቁር እና ነጭ መለዬት እንዴት ያቅታል? ትግሉ ለነፃነት ከነበረ። በ እጅ ያለው አቅም ደግሞ ይታወቃል ... ዛሬ ዛሬማ እኮ የአዲስ ነገር መበርከት እሳቸው ሳይደክሙ እኛው ደከመን ...

ትንግርት።

የሰንበቱ ጥዋት ትንግርት ነበር። ሱባኤ ያደከማቸው፤ መታዬቱን የማይፈቅዱት፤ ውዳሴውን የማይሹት፤ ስለ ብፁዕነታቸው የሚዘጋጁትን ልዩ የልደት ቀናት አልሻም የሚሉት፤ በዝምታቸው ውስጥ 27 ዓመት ሙሉ ገድመው የኖሩ ታላቅ ቅዱስ ሰማዕት አባት ብጽዕና እና እና እዬራዊ ልጃቸው ተገናኙ። ረቂቅ ነው።

 ሊመረመር የማይችል። ቅንነት እንዲህ ነው። ዕውነት ለመናገር ቅን መሆን የተመለከትኩት የማከብራቸው ዶር. ካሳ ከበደ አብረው ነበሩ በዛ ጉባኤ ላይ ነበሩ፤ ሁለቱም የተሰደዱበት ሥርዓተ መንግሥት አንድ ነበር።  

ያ  የትውውቅ ሁኔታ መንፈስ ቅዱስ አብዝቶ በረበበት መቅደሳዊ እዮላዊነትን የታደለ ቦታ ነበር። ስኬታማው ጠ/ ሚር ጉንብስ ብለው ብፁዕነታቸውን ሲያናግሯቸው የረበበው የማላዕክታን መንፈስ ግርማው ሌላ ነበር። ፍጹም ሌላ። መንፈሱ ሁለመናው ክልፍልፍ አልነበረም፤ የፖለቲካ ሸቀጥ በቦንዳ የተቸበቸበት አልነበርም። አላስጠጉትም፤ ስለምን ሱባኤ ድሉ ይሄው ነውና።

እርግጥ ነው ዲያቢሎስ ሥራው ማመስ ስለሆነ ቀድሞ የተዘጋጀው ወሳኔው ለዛ ቅዱስ መንፈሳዊ የዕድምታ ጉባኤ የሚመጥን፤ ደረጃውን የጠበቀ አልነበረም። ከልብ የሚገባ አልነበረም ለእኔ ማለት ነው። እንደ ድሮው ቢሆን ሙግት ስለሆነ ሥራዬ ስለሁሉም ነጥብ አምክንዮ መርምሬ እማስበውን ማቅረብ እችል ነበር። ቀድሜ እኮ የቆሞስ ኢንጂነር ስመኛው በቀለን ህልፈት አስመልከቶ ስጋቴን ጽፌ ነበር ብፁ ዕአባታችን እና ፕ/ ብርሃኑ ነጋ አገር መግባታቸው ስጋቴ ነው ብዬ።

 ያቺ መንፈስ ግን ቀረበችኝ፤ ሁሉን ጥርጣሬየን ሁሉ እርግፍ አደርጌ የአባ ቅንዬን አብዩን መንፈስ ዝግጁነት ስንዱነት ውስጤ አጸደቀው። ያን ግርማ ኢትዮጰያ በፍጥነት ማግኘት አለባት ብዬ ወሰንኩኝ። እኔ እያንዳንዷን ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ከገሃዱ ዓለም በፍጹም ሁኔታ ወጥቼ ነው የማስተናገድው። ልክ ስለልጆች ሳስብ ስጽፍ እንደምሆነው ማለት ነው። ስለ እናቶች ሳስብ ስጽፍ እንደምሆነው ማለት ነው። ስለ እናቶች ስጽፍ በዳይ የሚለውን አስቤው አላውቅም። የበዳይም የተባዳይም እናት እናት ናት እና።

እና ውሳኔው የገህዱ ዓለም ውሳኔ ነበር። „ዋስተና፤ የሥራ ድልድል፤ የአቀባባል ሴሪሞኒ፤  ስለ መስከረም 8ቱ ጉዞ“ በዛች ቅጽበት የቅንነት ገጽ እና መንፈስ ከመጥቆሩ በፊት ነበር እኔ ወስጤ የመገለው። የሆነው ሁሉ ከልዑል እግዚአብሄር ስለነበር ለምርቃት፤ ለቅድስና፤ ለክብር፤ ለሰማያዊ ልዕልና ቅደመ ሁኔታ አያስፈልገውም ነበር። ሞተ መነኮሰ ማለት በዬትኛውም ሁኔታ ተሰናድቶ መጠበቅ ማለት ነው። ስለዚህም ከፋኝ። ጊዜም አላጠፋሁም ለመፋለም … ሞት ቢመጣ ኑሮስ? አልሄድም መቼም አይባልምና ... 

ከዛ በኋዋላ የሆነው ደግሞ በሰው ሃይል፤ በሰው ጥበብ አይደለም የሆነው። በኬንያ ክልትምትም ብለው የተቀጡ አባ ቅንዬ እዮራዊ ቅንዬን ልጅ ሲያገኙ አውሮፕላን ልክ እንደ ታክሲ እቤታቸው ድረስ ሄዶ፤ አስተውሉ የለማ መንፈስም እንዳይቀርባቸው አክሎ፤ መንግስታዊ አካላትም እንዳይቅርባቸው አክሎ፤ በዛ ሥርዓት አብሮ የተሰደደውን መንግሥታዊ ውክል አካል አክሎ ዶር ካሳ ከበደን ጉባኤዎችን አብዛኞቹን የመራው፤ የፕሮቶኮል ሹሙን ሙግት ውስጥ የከረመውን ዲያቆን ዳንኤል ክብረትንም መንፈሱን አካቶ ታምር በምድር ተከወነ። 

ስለ ቀደመው የስደት ዘመን ማሰቡ በራሱ ከንቱነት ነው። ቅድዱስ ልዑል እግዚአብሄርም፤ ሰማይታትም፤ ነብያትም ተሰደዋል። ስለ እምነት መሰደደ ክብር፤ ሽልማት፤ ሥጦታ ነው። በመከራው ውስጥ ስለተገኘው ትሩፋት ነው መመስከር የሚያስፈልገው። አሜሪካም ቅድስናውን ሰማያዊ መሆኗን መሰከረ መንፈስ ቅዱስ። ገድል ነው።

የሚገርመው እነሱ ጉዞ ላይ እያሉ ተልዕኮውን የፈጸመው፤ መክሊቱን መንበር ላይ ያዋለው፤ በሱባኤ የባጀው ቆሙሱ ፈቃዱ መንፈስ አሸለበ። በእለተ መርቅርዮስ አባ ቅንዬ ብጹዑ አቡነ መርቀርዮስ ወደ ባዕታቸው በሰላም፤ በእልልታ ገቡ። ከሚስጥርም በላይ ነው። 

ያ ታላቅ የአገር ዋርካ ተሰናበት ማለት አልችልም፤ ለዚህ ነው በቅንፍ ውስጥ „ስንብት“ የሚለውን ቃል ያስገባሁት፤ በእሱ ውስጥ የነበረው የቅንነት መንፈስ ሱባኤ የባጀበት የመንፈስ እርሻ አስብሎ አባቶቹን አዋህዶ ነው የተከወነው። ገዳም እኮ ነው የባጀው። ስለምን ህክምናው ተተጓጉለ ቢባል ያ ሳቢያ ነበር። ቅንነት የመንፈስ ሃብትነቱን ለማዘከር ሱባኤ ያስፈልገው ስለነበር ነው … የሚሊዮኖችን ሃላፊነት ወስዶ ነበር ሱባኤ የባጀው። 

በዚህ ሚስጢር ውስጥ ዕንባ ማፈስስ አይገባም። በዚህ ሚሰጢር ውስጥ ማዘን አይገባም። ሳናውቀው ግን ፍጹም ንዑድ የሆነ መንፈስ ቆሞስ ፈቃዱ ተክለማርያም ውስጥ ነበር፤ ስለ ቅድስት ተዋህዶ እንጂ ስለ እሱ የጤና መዳን ጉዳይ አልነበረም ያ ሁሉ ድካም፤ ለዛም ጥሪ የደረሳቸው በራሱ ፈቃድ በመንፈስ አንድ አድርጓቸው ባታን ጣና ዘገሊላ አድርገዋታል መብረትና ጸጋ መቅደስ ተመሰረተ፤ እሱም ሳያወቀው እኛም ሳናውቀው ኖረን እንጂ በክህነት ዓለም ሊኖር የተጋባው፤ በውስጡ ቅድስና የተሰጠው ንዑድ ሰው ነበር ማለት ይቻላል ቆሞስ ፈቃዱ ተ/ ማርያም። አባቱን አስገባ ተልዕኮውን ከወነ።

  v   ማሰብ።
እሰቡት በዛን ጊዜ የነበረውን ከትግራይ የተፈጠረው የወያኔ ሃርነት መታመስ እና የሰሞኑ ያገረሸ ሁኔታ፤ የአደባባይ ሰልፉን ዕድምታ፤ የአዲስ አባባው ቦሌ ቅድስናን ሲያስተናግድ የመቀሌው የአሉላ አባነጋ አዬር ማረፊያ ደግሞ አንቶኖብ በጠመንጃ የደነደኑ ሰዎችን አስተግዷል። ምን አልባት ቦሌ ያሰተናገደው ቅዱስ መንፈስ ተረካቢዎች ቁጥር እና በአንቶኖብ እንደ ዘሃበሻ ዘገባዎች 40 ታጣቂዎች በመቀሌው የአሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ እንደተያዙ ተዘግቦል።

ለመሆኑ ከጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጋር ጉዞ ወደ አሜሪካ ያደረጉ ስንት ነፍሶች ነበሩ? አሁን ደምረው ሲመለሱ ምን ያህል ብጹዕን ነበሩ? ተቆጥሮ ቢነገረኝ ደስ ይለኝ ነበር። ምክንያቱም አንድምታ ሚስጢር ተርጓሚዎች የመነሻ መሠረት ሊሆን ስለሚችል። በጠ/ ሚር አብይ አህመድ ባረፉበት ቦታ የነበሩት የሰንበት ታዳሚዎችስ ምን ያህል ነበሩ አባት እና ልጁ ሲገናኙ? በመጀመሪያው ቀን የደስታ መግለጫ ጊዜስ ምን ያህል ንጹሃን ነበሩ 318 ይሆን? 

አሁን አሁን ሳስበው እኛ የምናውቃቸው እና የማናውቃቸው ተደምረው ጉልሆቹ 12 የለውጥ ሐዋርያት ይሆኑን እላለሁኝ? ልዑል አስፋው ወሰን አስራተ ካሳ አራቱ የአዲስ ኪዳን ወንጌላውያን ብለውናል፤ ቃለ ህይወት ያሰማልን፤ እነኛ የ108 ይሁንልን ያለቱም አሉን፤ ይደረግልን ያሉትስ፤ ከዬትኛው የዕድምታ ሚሲጥር ጋር ይቀራራብ ይሆን ቁጥራቸው? ምንም ያለተነገራላቸው ትንፋሻቸው አሜሪካን አገር የቀረው የአቶ ተስፋዬ ጌታቸው ህልፈትስ በምን መልክ እንዘክረው? እሳቸውም በቆመስነት ውስጥ እንዘክራቸውን?አያንሳቸውም ባይ ነኝ። 

ሞት እና ደስታ፤ ተስፋና ቅንነት፤ ጭካኔና ርህርህና፤ ሳቅ አና እንባ፤ ሲቃና ፈገግታ ሁሉንም አላዛሯ ኢትዮጵያ እያስተናገደች ነው? መሪው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ነው እና አሸንፍን እንወጣለን ብዬ አስባለሁኝ - እኔው።

  v   ምዕራፍ በቅኔ ዘጉባኤ።
ዘመነ ሚስጢር፤ ዘመነ ቅንነት፤ ዘመነ ትውፊት፤ ዘመነ ትሩፋት፤ ዘመነ ማድመጥ፤ ዘመነ የማናውቀው ግን እዬሆነ ያለ ረቂቅ ነገር።  እንድ ስብሰባ ላይ እጅግ የማከብራቸው ዶር ምህረት ደበበ እና ረ/ ፕ ምህረት ሻንቆ ስብሰባ ላይ አንድ ወገኔ "ፈጠነብኝ ለውጡ እና ከአብይ ውጪ ሳስበው ጨነቀኝ" የሚል ሃሳብ አቅርበዋል። "እሱን በ100 ቀን ስንገመግም እኛስ በ100 ቀን ምን እዬሠራን ነው" የሚልም ሌላ ትንታግ ወጣት ያቀረበው የእድምታ ባለጉዳይ ነበር። 

"ይህ ጥረት እና ህዝቡ መስመር ሠርተዋል ማህል ላይ ግን አስፈጻሚ አካሉ እኩል መራመድ አልቻለም እና እንዴት ማገናኝት ይቻላል፡ የሚሉ ሞጋች ፍሬ ሃሳብም ያነሱ ብልህነት አስተውያለሁኝ፤ የሚገርመው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው ውይይቱ ስለመደመር ፖለቲካ ክፍል አንድ እና ሁለት ይህ የሚደመጠው። ፈቃዱ ሲሆን የፈቃዱን ያህል ተመጥኖም ሆነ ተቆንኖ፤ ተንሰራፍቶም ለምቶ ይከወናል። ሁሉም ነገር ለበጎ ነው።

በጠ/ሚር ምርጫ ዋዜማው ላይ ነበር የመቀሌው መሬት መንቀጥቀጥ፤ የምርጫው ውጤት የተደመጠው እንደ ትንሳኤ ቀን በሌሊት ነበር፤ በዛው ሰሞናት ነበር የቆመስ ፈቃዱ ተክለማርያም አጀንዳ ጎልቶ የወጣው፤ የምርጫው ውጤት እንደ ትንሳኤ ቀን በሌሊት ፈጽሞ በታሪካችን ተደምጦ የማያውቅ አዲስ ክስተት ነበር። እራሱ ዶር አብይ አህመድ እጩነት ፈጽሞ ያልተጠበቀም ነበር። ድንገቴ ነበር። 

በዚህ ሰሞን ደግሞ አሜሪካ መምጣት የለባቸው የሚሉ ወገኖች ሙጉቶች ነበሩ። የጠ/ ሚሩ መንፈስ በአካል አሜሪካ እንዳይታይ ሞጋቾቹ ዛሬ ደግሞ አትራፊ የሆኑት እነሱ ናቸው። እዬት የፈጣሪን ጥበብ፤ አሁን እዛው ላይ ነኝ ሌሊት ጉዞ ላይ እያለ ነበር መንፈስ ቅዱስ የቆሞስ ፈቃዱ ተክለማርያም በሥጋ መለዬት የተገለጸው።  በሌሊት ማለት ነው። 

በሁለቱም ዘርፍ ስትመለከቱት የሚገፋው የአብይ ቅዱስ መንፈስ ነበር፤ ግን ግድ ነው ጸላዬ ሰናይ ሥራው ምን ይሁንና? ነገር ግን ከእግዚአብሄር የሆነውን ማንም ገድቦ ሊያስቀርው ስለማይችል የሆነው በፈቃዱ ነው። አሁን ሁሉም ረብ አለ የቤተ መንግሥቱ ጉግሥ እና የዝና አሽኮኮም ታወጀለት። የአደባባይነት፤ የሥም ግነት የሚፈለገውን ያህል ውሃ አገኜ በቃኝ እስኪል ድረስ እንደጠጣው፤ አዋኪ ሃሳቦችም የአደባባይ ሙገሳ፤ የአደባባይ ልቅና፤ የአደባባይ እጬጌነት ተሰጣቸው የፈለጉት ይህን ነው ሰለዚህ አዬሩ ረብ አለ።  

የቀድሞው ፕ/ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሲሞግቷቸው የነበሩትን ክብርት ወ/ሮ ክሊንትን አብረን ነው ቤተ መንግሥት የምንገባው በማለት የከወኑት ምግባር ነው አሁን ዲሲ ላይ ሲከወን የተመለከትነው። 

ቤተ መንግሥቱ የህዝብ ነው ብለው የጥበብ ሰዎች እንዲጎበኙት ሲያደርጉ፤ ደህነንቱ የህዝብ ነው ብለው ተፎካካሪ ፓርቲዎችን እንዲጉበኙት ሲደረግ፤ በቤተ መንግሥት ውስጥ እጅ በርካታ የህዝብ ግንኙነቶች ሲደረጉ አማኝ አልተገኘም ነበር። እበራችን መጥተህ ስታነጋግረን፤ በተግባር ዓወድ ልካችን ሚዛን ላይ የገጠመውን ፈተና ስታስተካክልልን፤  በእንደበትህ ሥማችን እስከ ሊጋባችን አደባባይ ላይ ስተውለው ነው የእኛ ክብር ላሉት የፈቀዱት ሆኑላቸው። 

የራባቸው፤ የጠማቸው አዲስ የለውጥ ሃሳብ ቢሆን ይህ ሁሉ ሽር ጉድ አያስፈልግም ነበር። ለውጥ ተፈላጊ ከነበረ፤ ነፃነት ተፈላጊ ከነበረ የተባባሩት መንግሥተት ኮሚሸነር በአደባባይ መስከረውታል። የዓለም ሚዲያ በሚገርም ሁኔታ ለውጡን ቀድሰዎታል፤ የ አሜሪካ እኒባሲ ጋዜጣዊ መግለጫ ስጠተውበታል። 5 ሚሊዮን ህዝብ ራሱን ለመገበር ተሟል በመዲናዋ ብቻ ሌላው ትንግርት ነበር ባህርደር ሆነ በዬ አካባቢው የሆነው፡  ማንበብ ማድመጥ እስኪደክመን ድረስ። ግን የሚፈለገው ያ አልነበረም … ሚዲያ ላይ እኩል መከፈስ ነበር ... መሻቱ ... 

 ለዚህ ነው አባ ቅንዬ ይህ ከሆነ የሚረብሻቹህ አፌ ባንቡራ እስኪያወጣ ድረስ እደግማችሁ፤ እሰልሳችሁ አለሁኝ፤ ቢያስፍልግም ሥማችሁን አሽኮኮ አደርግላችሁ አለሁኝ ያሏቸው። ክታብም አድርገን ቢሉ ያደርጋቸዋል። ነገ ደግሞ ቀይ ምንጣፉን እንጠብቃለን። ቀይ ምንጣፍ ቀዩ ዶሮ ነውና። 

እንግዲህ መሬት ላይ ሲያውክ የከረመው የነጭ ተደራዳሪ ናፍቆተኛም አቤቱ ሰማያዊም አብሮ ቤተመንግሥተኛ መሆኑ ታውጆለታል። ያው በጥቁር ቀለም ስለሆነ ቢከፋውም … ነገ ደግሞ ክብርት ወ/ሮ አና ጉምዝ ባለቀይ ምንጣፍ ይሆኑላቸዋል … ይመሰገናሉም በአደባባይ። የቀረው ይህ ክፍል ብቻ ስለሆነ።፡ ማሸነፍ ማለት ይሄው ነው … ያሸነፈው ግን የተገፋው፤ የተዳጠው፤ አቀመ ቢስ የተባለው፤ ከሌሎች በይሻላል ታች የተወረወረው፤ ጉልቻ ቢለዋወጥ የተባለው… ነው ድል ላይ ያለው። በአቋሙ ውስጥ ግን ሌሎችን ወደ ራሱ አምጥቶ።  

የአብይ መንፈስ ነው በራሳቸው ሜዳ አሸንፎ ስኬቱን መንበር ላይ ያዋለው። እሱ የማይደፈር ረቀቅ የማድርግ የመቻል አቅሙን ነው ያሳዬን። ይህ የእሱ አቅም ነውን? አይደለም። የሚስጢር አቅም ነው።

አሁን ያሉት ፈንገጥ ያሉት መንፈሶች ደግሞ ህልውናዬ ይጠበቅልኝ የሚል መንፈስ ነው ያላቸው። አጀንዳም አይደሉም። ዕወቅናም የላቸውም። ግን ጥያቄው የመንፈስ ስለሆነ መንፈስ ቅዱስ በራሱ ጊዜ ሥራውን ይሰራል።

  v   የሚኒያ ምልዓተ ጉባኤ ዕድምታ።

ክፉ መንፈሶች ከዚህ በኋዋላ አጀንዳ የላቸውም። ጹሁፌን በቋሚነት ለታደማችሁት፤ ታስታውሳላችሁ ኦቦ ሊበን በለንደኑ ጉባኤ ላይ „ኢትዮጵያ ካልፈረሰች ኦሮምያ ሰላም አታገኝም፡ ሲሉ፤ በዚህ ርብሽብሽ ያለው መረብ እና ህብር ራዲዮ ሌት እና ቀን የኦሮሞ ሊሂቃን ሲያናግር ግልምት ብሎኝ፤ ከዚህ በኋዋላ አጀንዳ አይኖራቸውም። እድሉን አገኝተው መናገራቸው ታላቅ ነገር ነው መልካም ነገር ነው ብዬም ነበር። ልክ አቶ ሞላ አስገዶምን ደግመን ሚዲያ ላይ አናያቸውም እንዳልኩት ሁሉ።

በቀን 600 ነፍስ፤ በሳምንት 700 ሺህ በላይ ህዝብ የሚፈናቀልበት ወገን አማራ ጠላቴ ነው ብሎ ተነሳ። ይህ በአደባባይ ነው። ከዚህ በኋዋላ ይሄ መንፈስም ሌላ አጀንዳን አይኖረውም። የታመቀው ፈነዳ፤ በቅንነት የነበሩ ሰዎች አሸነፉ። በቅንነት የነበረው አማራዊ መንፈስም አሸነፈ። በቅንነት የነበረው ኦሮማዊ መንፈስም አሸነፈ። ስለምን ፈቃዱ ስለሆነ።

ስለዚህ በፍጹም ሁኔታ ተገሎ የነበረው የአብይ መንፈስ ይጸጽታችኋዋል፤ ይቆረቁራችኋዋል እንዳልኩት ሆነ። መሬት ተነጠፍን። በምክንያት መደገፍ፤ በምክንያት መቃወም መርህ ቢሆን ይህ ሁሉ ድራማ ባልታዬ ነበር።
ዛሬ የአብይ መንፈስ አክቲቢስት ተሆነ። ተመስገን! አገር ልንገባ ወሰን። ተመስገን! የክብር አቀባባል እንደሚኖረልን አዳመጥን፤ ተመስገን! በቃ ዲያቢሎስ የት ይጠጋ?

  v   የታመቀ ፍቅር።  
ትግራይ ውስጥ ኢንጂነር ስመኛው ገዳይ የታወቀ ቀን አብዮት ይፈናዳል? አገር የሚያደባልቅ። ለትግራይ ህዝብ የስመኛው ቅንነት ተገልጦለታል ከማንም በላይ። ለትግራይ ህዝብ የስመኘው ሚሰጢርነት ተገልጦለታል ከማንም በላይ። በውነቱ ቅንነቱ ነው በዚህ ወቅት ህይወቱን ያሳጣው፤ ከኖረው በላይ ዛሬ ስመኛው የውስጥ ታቦት ሆኗል ለትግራይ ህዝብ - ረመጡ ነው። 

የኤርትራን ሰላማዊ ሰምምነት ተቀብለናል ብለው የሙታን መንፈስ አደባባዩን ሲያስወርሩት፤ የሰማዕታትን ቀን አከባባር እስኪመስል ድርስ ለሴራ መደበቂያ ስላደረጉት ዝግጅት አይደለም እኔ እምመሰከረው። ያ ለማድመቂያ የሆነውን አይደለም ንጹሃን እንዴት ግብግብ እንዳደረጋቸው በግል ቃለ ምልልስ የተደረገላቸውን ስለ አዳመጥኩኝ ብቻ ነው። ለትግራይ ስመኛውን ጥሉት ቢባሉ አይቻልም። ስመኘው ውስጣቸው መሆኑን መንፈሱ ነግሮኛል። 

ለቋሚዎች በመድርክ ሺህ ሚሊዮን ጊዜ ስለተጠሩ ሊመስላቸው ይችላል፤ የስመኘውን ያህል በሞት ውስጥ ያሸነፈ ጽኑ፤ በማተቡ እንደ ቆመ፤ ታማኝነቱን ሳያብል ያጸደቀ፤ ከዓላማው ንቅንቅ ሳይል እንደ አባቶቹ፤ እንደ አያት ቅድመ አያቶቹ መውደድም፤ መፍቀርም፤ መሆንም ምን ማለት እንደሆን ተቋም ከፍቷል ስመኘው። ስመኛው ውስጣችን ገልፆል። አስከብሮናልም። ስመኛው ከመይሳው መቀዳቱን በጸጥታው ወስጥ አመሳጥሯል። ስመኘው ወጀብ አልነበረም ስመኘው የማተብ ሙሉ ድምጽ እንጂ!

   v  የቁምነገር ፈርጥ በጣምራ ድል ጎዳና።

ዶር አብይ አህመድ እጩ የጠ/ ሚር አባል ሲሆን አሜሪካ ላይ የነበረው የሎቢ ሥራ ደግሞ ኦህዴድ ለእስልምና ዘመም ስለሆነ ዓለም እያሰጋት ላመከራ ተጨማሪ አቅም መስጠት ነው የሚልም ሌላ ጠንከር ያለ አሟጋች ጉዳይም ተነስቶ ነበር በወያኔ ሃርነት ትግራይ መኳንታት።

በዚህም መንፈስ ዙሪያ ቀደመው የተሠሩ ጉዳዮች ቢኖሩም መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ታምራቱን ገልጦ ጉልላቷን ቅድስት ተዋህዶብ በመንበሯ አሃቲነት ለማስቀመጥ ቀደማዊ አክቲቢሰት ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሆነው ሲገኙ ያን በሎቢ ደረጃ ሲሰሩ የነበሩት ያን ጊዜ ከከሰሩት በላይ፤ አሁን በእጥፍ ድርብ ከስራዋል ተቀናቃኞቻቸው። መንፈስ ቅዱስ እንደዚህ ነው።

ሌሎችም የተፎካካሪ ፓርቲዎች ሊሂቃንም ቢሆነ በፖለቲካ ሥራቸው ላይ አጀንዳ አድርገውት የማያውቁት የኢትዮጵያ የሚስጢር ዕድምታ በእውን እንዲህ ሲገለጥ ኢትዮጵያን የመምራት ብቁነት ሌላ ተጨማሪ አቅም ተገኝቷል። የአሜረካኑ ሴኔትም ይህን ልብ ሊለው እንደሚችል አልጠራጠረም። ብፁአን ባቶቻችን እቅፍ ድግፍ አድርጎ ይዞልን አሁን በ እልልታ ወደ ባዕታቸው ሲመለሱ ምን ያህል ኦህዴድ ለአገሩ ሰላም እንደሚተጋ ተጨማሪ ጉልበት ይሆንለታል። 

እጅግ ያሰደሰተኝ ልዩ የአመክንዮ ምስባክ ደግሞ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ብፁዕን አባቶቻቸውን እያቆላመጡ፤ በአውሮፕላናቸው ይዘው መሄዳቸው ሌላው የዘመናች የታሪካችን ፈርጥ ነው። ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን በአብዩ አቅም ነው ለማለት አያስችለኝም። ሁሉ የሆነው በፈቃዱ ሁሉ በሚቻለው በአዶናይ ነው ብዬ ነው የማምነው። 

ዋልድባ አብረንታት ገዳም ለመሄድ ሃሳቡ እንዳላቸው አዳምጫለሁኝ። ስለዋልድባ እና ስለቦረና የጠረፍ የምርምር ድንቅነት ከዚህ ቀደም "ከርምጃ ወደ ሩጫ ሞቶ" የሊሂቃን ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ አውስተውት ነበር። እኔም በሆነ አብይ ኬኛ ላይ ገልጬው ነበር ለሙግቴ። እንዲያውም በጥቂቱ ታሪኩን የተረኩትም ለዚህ ነበር። 

ስለዋልድባ ገዳም በመጠኑ ታሪክ ቀመስ የሆኑ ጉዳዮች ለማወቅ የምትፈልጉ ወገኖቼ ሃብትነቱ የሁላችንም ስለሆነ ከክፍል አንድ እስከ ስድስት የተሰራውን ትረካ መከታታል ትችላላችሁ። ዋልድባ የሁላችንም ነው። ግዕዝም እንዲሁ።

https://www.youtube.com/channel/UCJEQXw86u_NG4A1FVC1j2qg?view_as=subscriber

  v    ግራቀኙ ሲቃነት!

የሰሞናቱ የተደሞ ሂደት ከቦሌ እስከ ቦሌ፤ አብዮት አደባባይ ዲሲ፤ ሎሳንጅለስ፤ ሚኒያ ቅደስት ሥላሴ፤ አዬር መንገዳችን አክሎ በተደሞ ሲመረመር ይህ ስለምን ሆነ? በፈቃዱ የተከናወነ ነው። 

በዚህ ውስጥ የተገፋ፤ የተገለለ፤ የተረሳ መንፈስ አለ በዬትኛውም ዘመን። ይህ እንዲሆን ግድ አለ እና ግራ ቀኝ የመንፈስ ድል በድል ላይ ሲቃነት ሆነ። ግን ርቁቅ ነው። ሁሉንም አዬነው በእውነት ውስጥ ባዕትነት እና በድፍን ውስጥ ባዕትነት።

ተግባር ላይ የሰከኑ ነፍሶች ሞታቸውም ጌጥ ነው። ሰንበታቸውም ታሪክ ነው ቆሞስ ፈቃደ፤ ቆመስ ስመኘው፤ ቆሞስ ተስፋዬ ኢትዮጵያን እንደ አከበሩ ተከበረው አለፉ። አዲስ አበባም የኖረች ኑራ ሰሞናቱ በወር ውስጥ በተደጋጋሚ ማቅ ለበሰች፤ የሲቃነትም ቤተኛ ሆነች። ተነሺ ስትባል ሳትነሳ ለአብይ መንፈስ መነሳትን ፈቀደች፤ ለስመኛው መንፈስ ስንበት፤ ለፈቃዱ ትንፋሽ ማብቃት ዐነባች በሲቃነት።

  v   ገና ብዙ ገናዎች አሉ።

ቅዱሳኑ ቆሞሳውያን ማለፉን ቢያልፉትም ግን ገና ብዙ ገናዎች አሉ። እድሉም፤ ዕድሜውም ከተሰጠን …

ቆሞሰች ለሥም፤ ለዝና የተንበረከኩ ሳይሆኑ ለዛች ንጹህ ሰንደቅ ዓላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሳይነተከተኩ፤ ሳይብተከተኩ፤ መናጆም ሳይሆኑ፤ ሳይገለባበጡ ባመኑበት፤ በጽናት በመንፈስ ቅዱስ ልዕልና ከብረው ለዘለዓለም ይኖራሉ ….
ታቦት እኮ የሚቀረጸው በዚህ መንፈስ ውስጥ ነው …

እጅግ ለማከበረው ለምውደው ለቆሞስ ፈቃዱ ተክለማርያም የሰላም እረፍት እመኛለሁኝ። ቅድስናህ ያልታዬቸው የበለጠ ያከብሩህ ዘንድ እማጸናቸዋለሁኝ። ሱባኤ የያዝክበት ሚስጢር ከሚስጢርነቱ ጋር በተገናኘበት በተዋህድበት ሰሞናት ነበር ትንፋሽህ ከእኛ የራቀው፤ ግን የዘራኸው መንፈስ ቅዱስ ሙሉው በባዕትህ ረቦባታል እና እንኳን ደስ አለህ። የተካሃት መንፈስ ቅዱስ በስፋት የረበባት ነፍስ ደግሞ ነገ የምን ታምር ተቀባይ እንደምትሆን „ጊዜ ለኩሉ“ ነው።  ለደረክልን መልካም ነገር ሁሉ፤ ለሰጠህን የመንፈስ ሐሤት ሁሉ እግዚአብሄር አክብሮሃል። ሱባኤህም አፍርቷል። 

ማንነታቸው ያልታወቀ 40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ

  v   ክወና።

ገራሚው ነገረ ያን ያህል ሌሊቱን በሙሉ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ 4ኛው ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ ሙሉ ቀን ሳይደክሙ በዛ ግርማቸው ልክ ቅደስተ ሥላሴ ካሬድራል ላይ የነበራቸው ንቃት ሰውኛ አልነበረም። ሰንበት ላይ እዮር የሰጣቸውን ልጅ ጋር ሲገናኙም አቅማቸው አሜሪካ ያሉ ቤተሰቦቼ ድንቅ ብሏቸው ነበር። ያ ሁሉ አቅም የት መጣ ነበር ያሉኝ። የመንፈስ ቅዱስ ነው ብያለሁኝ። 

መንፈስ ቅዱስ አምሳዬውን ሲያገኝ ሃይለ አውዱ እዬራዊ ነው። ግን ቅኖቹ የኔዎቹ ክብረቶቼ፣ ---- ይህንስ አስተውላችሁታልን? እውነት ብነግራችሁ በምድር ሎሬት እና እሳቸውን እጅግ አደርጌ ነው የምወዳቸው። ጸጥታቸውን በፍጹም ሁኔታ ነፍሴን ይገዛዋል። እርጋታቸው በፍጹም ሁኔታ መንፈሴን ያስደገድገዋል። እንደ ሳሳሁዋቸው፤ እንደ ናፈቁኝ ሳለገኛቸው ባዕታቸው ገቡ። 

አሜሪካም ሲገቡ በሌላ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ሆኜ ሂደቱን እንድከተታል አዶናይ ፈቀደለኝ፤ ዛሬ ደግሞ በገደሙከበት ባዕቴ ውሰጥ ሆኜ ለማዬት አበቃኝ። እሞታለሁ ብዬ የተሰናዳሁት ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ነበር። ግን ያሰነበተኝ ለካንስ ስለዚህ ነበር። ሃይማኖታዊ መንፈሴ አንድ ሆነልኝ። ተመስገን! 
  
የኔዎቹ ለነበረን ተደሟዊ ጊዜ እጅግ አድርጌ አከብራችሁ አለሁኝ። እውዳችሁ አሉሁኝ ስል የለበጣ አይደለም፤ የለበጣ ክብር፤ የለበጣ ፍቅር ነፍሴን ጎብኝቷት አያውቅም። ስለዚህም የምር ነው። እኔን ፈቅዳችሁ ጊዜ ለመስጠት መወሰናችሁ በራሱ ሚስጢር ነውና ላከበረው ግድ ይለኛል። አቅሙ ከኖረኝ ልመለስ እችላላሁኝ ዛሬም አንድ ተደሞ አካፍላችሁ አለሁኝ። ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
መንፈስ ቅዱስ የፈቀደውን ነገር ከማድረግ የሚያግደው አንዳችም ሃይል የለም።


ወስብሃት ለእግዚአብሄር። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።