ፍቅር፤ ምህረት፤ ይቀርታ ታማኝነትን ይጠይቃል።
ፖለቲካም ታማኝነት ይርበዋል፤ ይጠማዋል፤ ይናፍቀዋልም። „ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሄር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።“ የዮሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 06.10.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። ክብር ናችሁ! ኑሩልን! · መቅድም። እንኳን ደስ አላችሁ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ፤ እና አቶ ደመቀ መኮነን። እንኳን ደስ አላችሁ ቅድስት ኦርኦቶዶክስ ተዋህዶ እና ድምጻችን ይሰማ። እንኳን ደስ አለህ የ ኢትዮጵያ ቅን እና ቻይ ህዝብ። ወግ። ክብርት ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚል የእቴጌ ጣይቱን ዘመን ጠገብ የብርሃን ውቅር መክሊት ሥጦታ አስጠብቀዋል። ቀደም ባሉት ጹሑፎቼ የቀደመው ዓላማ ዲዛይን ይኸው መሆኑን አስቤ የኢትዮጵያን ሴቶች የፖለቲካ ብልህነትን አነገት እንዳያስደፉ ማሳሰቢያ ጽፌ ነበር። አሁን እሳቸው ያደረጉት ይህን ነው። የኢትዮጵያ ሴቶችን ታማኝነት ልቅና አሳይተዋል። ለፖለቲካ ፍጹም የሚያስፈልገው የአቅም ምንጭ ታማኝነት ነው። የ አገር ፍቅር ብሄራዊ ስሜትም እንዲህ ይገለጣል። ከኢጎ በላይ አገርን ማዬት ይኸው ነው አብነቱ። በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ በህልሙም የማይገኘው ግን አፍቅሮተ ግራ ፖለቲካ ነው። ታማኝነት በግራ ፖለቲካ አሞራ በረረ ቅሉ ተሰበረ ነው። ቀን ሲገነ...