ዕውነትን መወገን ትውልድን ያንጻል። ለእውነት ቀጠሮ አያስፍልጋትም!
ቋንጣ። „ምን እንኳን በለስም ባታፈራ፤ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፤ የወይራ ሥራ ቢጎድል፤ እርሾችም መብልን ባይሰጡ በጐችም ከበረት ቢጠፉ፤ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ እኔ ግን በእግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤ መዳድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።“ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ፲፯ እስከ ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 28.11.2018 ከገዳማዊቷ ሲወዘርላንድ። · እ ፍታ። ሴት ልጅ ሁነኛ ክንድ ሳይኖራት ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ መጀመር እኔ ባለኝ ተመክሮ እንደ እብደት ነው እማዬው። መከራ ብቻ ሳይሆን መኖርን የሚቃማ አሳር ነው። የማ ቆጨው በራስ ውሳኔ ስለሚሆን ብቻ ነው እንጂ ነገር ሴት የፈተና ተፈጥሮ ነው ያለው። እንዴት አደራችሁ ዋላችሁ አመሻችሁ ውዶቼ አዱኛዎቼ። መቼም ለኢትዮጵያ ሴቶች አዲስ ዘመን ቦግ ብሎ ብሩኽ ሆኖ ወጥቷል - ዛሬ ላይ። „ለእግዜር አይቀርበት ለሰው አይቀርበት ሰሌ ከሰራው ቤት እኛ ገባንበት“ ይላል የጎንደር ሰው ሲተርት። ገና ተወዳድራ ብታሸነፍ ተብሎ አንዲት ነፍስ ስንት ፍዳ ተከፈለ። ስንት መከራ ታዬ። ሥሟን የሚያነሳ የሚዋሳም አሳሩን ከፍሏል፤ ዕውቅናው ተቀባይነቷ እዬጎላ ሲመጣ ይህቺ ሽንብራ ከሰነበተች ዓይነት በሴራ ደቦ ከፖለቲካ ትግል የተገለለች ቅን ነፍስ እነሆ ዛሬ የኢትዮጵያ አሉ የሚባሉትን የፓለቲካ ድርጅቶች ሊቀ ሊቃውንታትን ጉባኤ ከጠ/ሚሩ ጀምሮ የስብሰባው መሪ ሆና ጉብ አለች። ቅብዐ ያለው ነፍስ እንዲህ ነው። የፈለገው ነገር ቢገደብ፤ አጥር ቢሰራ፤ ክትር ቢበጅ ቅብዕ ካለ አይቀሬ ነው። ቅኖችም እንዲህ ሲገኙ መገናኛውን በቅኔ ዘጉባኤ ይቃኙታል እንዲ...