ልጥፎች

!ዳግማዊ አባ ኮስትር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የማን ናቸው?

ምስል
!ዳግማዊ አባ ኮስትር አቶ ንጉሡ ጥላሁን   የማን ናቸው? ! „አንተ በህይወት ሳለህ አእምሮህም  ሳለች ግብርህን አትለወጥ።“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴ ቁጥር ፳፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 05.01.2019  Sergute©Selassie ፍቅር በፍቅር! ·        ከእመ ዝምታ ከእናቱ ሲዊዝ ዋው ሻሾ ፍጥነቱን ጨምሯል ዛሬ የታደለ ቀን ነው። ሻሾን እወደዋለሁኝ እንደ አድዮ ነው የማዬው። በቃ በዚህ ከቀጠል ነገ ነጭ ስጋጃ ለሰንበት ሙሽራ አንጥፎ ይጠብቃል ማለት ነው። ግን ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ·        ወግ ቢጤ …. ሰሞኑን አንድንድ ዜናዎች ከዚህም ከዚያም ሲወርቡ ደፍሬ መጻፍ አልቻልኩም። የጠራ መረጃ በግራ በቀኝ ማግኘት ስለነበረብኝ። አቶ ንጉሡ ጥላሁን የጠ/ሚኒስተር ጽ/ቤት የፕሬስ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው እርግጥ መሆኑን ዛሬ የበለጠ አረጋግጫለሁኝ። ስለሆነም በዚህ ዙሪያ የምለው ይኖረኛል። ·        አቶ ንጉሡ ጥላሁን የማን ናቸው? ለመሆኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የኢትዮጵያ? - የአማራ? - የጉራጌ? - የኦሮሞ? - የዜግነት? - የዞግነት? ከቶ - የማን ናቸው። እንደ ሥርጉ ሥላሴ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የራሳቸው  ብቻ ናቸው። እድግመዋለሁኝ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የራሳቸው ብቻ ናቸው። ለሁሉም መስመር ደግሞ ሊንክ አገናኝ ድልድይ ናቸው። ለውጩም ለአገር ውስጡም። ዘለግ አድርገን ስንሄድበትም ከዚህም ያለፈ ይሆናል። ወደ ሌላ ዓለም ይዶለናል። ለጊዜው በቁጠባ ይያዝ ...  እንዲህ ዓይነት...

ሳተናው ወጣት አቶ ምግባሩ ከበደ ሳንጠግባቸው የት ገቡ?

ምስል
ሳተናው ወጣት   አቶ ምግባሩ ከበደ ሳንጠግባቸው የት ገቡ? „ለሞት እስከ ደርስ ድረስ ሁልገዜ መከራ ተቀብያለሁ  እና ስለዚህ ነገር እግዚአብሔር ከመከራ ያድነኛል“ መጽሐፈ ሲራክ ፴፩ ምዕራፍ ፲፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ  Sergute©Selassie 05.01.2019  ከእመ ዝምታ ሲዊዝ ·        ጠብታ። ዛሬ ክረምቱ ከገባ ለመጀመሪያ ጊዜ አያ ሻሾ መጣሁ ብሎ ብንብን እያለ ነው። ትናንት ሃይለኛ ብርድ ነበር። ከሃይለኛ ብርድ ቀጥሎ አያው ሻሾ እንደሚከተል ልብ ልክ ቢሆንም ከመኝታዬ ስነሳ ሙሉ ለሙሉ አያዋ ሻሾ ከነመጎናጸፊያው ስጋጃውን ዘርግቶ ኑልኝ ይላል ብዬ ነበር። አሁን ግን በስሱ ይዞታል።  ሌላው የሲዊዝሻ መለያ አያ ሻሾ ሲኖርም ልክ እንደ አውድ ዓመቱ የእማ ዝምታ ነገር ጸጥ ረጭ ነው። እና ሥርጉትሻ ወደ ባዕቷ ገባ ብላ ታጣጥመዋለች። ግርግር የሌለበት፤ ህውከት የሌለበት፤ ኳኳቴ የሌለበት ረጋ ያለ ዓለም ይናፍቃል አይደል? እኔ ለዚህኛው ዓለም የተፈጠርኩ ነኝ። ረጭ ላላው ...  እንደዛ …  ስለሆነም ዛሬም ምንም እንኳን ዕለተ ቅዳሜ ቢሆንም ጸጥታ አንጻራዊ ይኖራል አይዋ ሻሾ ሳይደክም ወይንም ሳይሰለች ገፋ አድርጎ ከሄደበት ነገ ዳግሚያ ባይናከተን ሆኖ እርፍ እንደሚል ነው። እንጠባበቃለን … ·        የስጋት እንቁላል። የብአዴን የስሜን አሜሪካ ጉዞ ብዙም ስላልተመቸኝ ጥፌ ነበር። ምክንያቱም እኔ ፈሪ ስለሆንኩኝ። ያልኩትም አልቀረም እነሱ ስሜን አሜሪካ እያሉ ነው በቅማንት ጉዳይ ያደቡ ሃይሎች ስንጥቅ ፈጥረው ጥፋት ያስከተሉት።  ...

የራስነገር።

ምስል
የራስ ነገር ። „አንተ በህይወት ሳለህ አእምሮህም  ሳለች ግብርህን አትለወጥ።“  መጽሐፈ ሲራክ ፴፳ ቁጥር፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 04.01.2019 ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ። መቅድም። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? የራስነገር። የራስነገር ብዙ ነው። የራስነገር ሁለመና ነው። የራስነገር ሁለንትና ነው። የራስነገር መስታውት ነው። የራስነገር ሰውኛ ነው። የራስነገር ተፈጥሮኛ ነው። የራስነገር መ ሆን ኛ ነው። የራስነገር ቢሆንም ባይሆንም ቢያምርም ቢከፋም ብቻ የራስነገር የራስ ነው። አፍንጫው ደፍጠጥ ከንፈሩ ነፋ፤ ፊቱ ከስከሰከስ ቁመቱ አጠረ፤ ሰውነቱ ደንበል ትክሻው ጠበብ ያለው የራስነገር ከሆን ደስ ይላል ይወደዳል። የመቻል ትሁቷ እህቴ አጭር ወንድሟን እሰከ ነፍሷ ነው የምትወደው። የትዳር አጋር ግን ምርጫዋ ረጅም ነው። እሷ እራሷ አጭር ናት። በዛ ላይ ባርቾ ናት። አጠር ያለ የትዳር አጋርነት ጥያቄ ቢያቀርብ ሁለ ነገሩ ቢስማማት ግን ላትፈቅድ ትችላለች ዘለግ ያለ ስለምትሻ።  ለወንድሟ ግን ቅድመ ሁኔታ መስፈርት አይወጣለትም የራስነገር ስለሆነ ጌትዬ አባትዬ ትለዋለች። እሱን ሳታይ፤ ትንፋሹን ሳታዳምጥ ውላ ማደር ጭንቋ ነው። እህቴ ወንድሟን እንዲህ ነው  የምትጠራው አብዬ ጌታዬ አባትዬ ቁልምጫው እንክብካቤው ልክ የለውም።  ሌሎቻችን ትርፍ ነን። እሱን የመሰለ ሰው በምድር የተፈጠረ አይመስላትም። ጋብቻ ላይ ሲመጣ ደግሞ ቆንጆ ወንድ ነው ምርጫዋ። ወንድሟ ደግሞ አሜሪካዊውን ስሚዝ ነው የሚመስለው በቁመት እንዲያውም ከስሚዝ አጠር ይላል። ስለምን ወንድሟን መረጠችው ሲባል የራስነገር ስለሆነ። የራስነገር ተወዳጅ፤ ተፈቃሪ ነው። ...