የባልደራሱ ባላደራው የፖለቲካ ድርጅት ምሥረታ ጉዞ ጥንቃቄ ስለማስፈለጉ።
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። የባልደራሱ ባላደራው የፖለቲካ ድርጅት ምሥረታው ላይ ሆነ ጉዞው ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል። የትውልድ አድዮ ለመሆን ከተለመ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ {መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 16 ቁጥር 9 } ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 11.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ይድረስ ለባልደራስ የባለ አደራው ምክር ቤት አዲስ አበባ። ግልባጭ ለሁሉም የባልደራስ የባለ አደራው የድጋፍ ሰጪ ትጉኃን አካላት፤ በያሉበት። 11.01.2020 · ትህትናዊ መሳሰቢያ። ክብረቶቼ በስብሰባ ሥርዓት ከአስተያዬት ማሳሰቢያ ይቀድማል እና ሦስት ማሳሰቢያዎቼን እንሆ። 1. ባለ አደራ ወይንም ባልደራስ እያልኩ ስለምጽፍ ግር እንዳይላችሁ። ሁለቱም ሥያሜዎቹ ቢሆኑ ዕይታዬን የመሸከም አቅማቸው እኩል ነው። በቀለለኝ መንገድ ነው የምጸፈው። በሌላ በኩል ግን የባልደራስ ባለ አደራው ወይንም ባልደራስ በአደራው ጥሩም አማራጭ ይመስለኛል። 2. አብን በተደጋጋሚ ለምሳሌነት አነሳዋለሁኝ። ያው ልጅ ድርጅት ስለሆነ ቀለል ይለኛል። እንዲጠነክርም ስለምሻ። 3. ሌላው ጋዜጠኛ፤ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች፤ የዴሞክራሲ ታጋይ እና የባለ አደራው ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ እስክንድር ነጋ እያልኩ መጻፍም በጥበብ ውስጥ እንዳለ ሰው እሱንም ስለማስበው በአጭሩ አቶ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ብለው „አንተም“ ብለው አቶ እስክ...