ልጥፎች

ጉበትዎ እንደተጎዳ የሚነግሩዎት 10 ምልክቶች

ጉበትዎ እንደተጎዳ የሚነግሩዎት 10 ምልክቶች ጉበት በአካላችን ትልቁ ኬሚካል አመንጪ አካል ነው። ጥቅሞቹ ብዙ ናቸው። 3 ዋና ጥቅሞች አሉት። ባይል የሚባል ምግብን ለመፍጨት የሚያግዝ አረንጓዴ ኬሚካል ያመነጫል። በሰውነታችን ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያጸዳል። የሰውነታችንን ሃይል ፍላጎት ላማሟላት ግሉኮስ ያመነጫል። ከጉበት አስፈላጊ ጥቅሞች አንጻር ጤናውን መከታተል ለሰውነታችን ጤና አስፈልጊ ነው። ጥሩ አመጋገብ፣ አካል ብቃት እንቅስቅሴ እና በቂ እንቅልፍ ማግኘት ለጉበት ጤና አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። አልኮል እና ቡና ማብዛት የጉበታችንን ጤና አደጋ ላይ ይጥሉታል። ጉበታችን ሲታመም ህመሙ በብዙ ሰውነት አካላታችን ላይ ይንጸባረቃል። የተለያዩ የጉበት በሽታዎች አሉ። የተለመዱት ሲሮሲስ፣ ሲስቲክ ህመም፣ የጉበት ፋቲ ህመም፣ የሃሞት ጠጠር እና ሄፕታይተስ ናቸው። ጉበትዎን ሁሌ የሚንከባከቡ ከሆነ ጤናዎ ላይ ለውጡን ያዩታል። የጉበት ጉዳት ካለዎ አስቀድሞ በመታከም የመዳን እድልዎን ያሰፋሉ። የጉበት ጉዳት ምልክቶች 1) ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ derneuemann / Pixabay ብዙ ሰው የማቅለሽለሽ ስሜት እና ማስመለስን እንደ አደገኛ የበሽታ ምልክት አይቆጥራቸውም። ያለምንም ምክንያት የማቅለሽለሽ ስሜት ወይም ማስመለስ ካጋጠመዎ የእኩላሊት ወይም የጉበት ህመም ያመላክታል። ስሜቱ የተሰማዎ ግን በምግብ መመረዝ ወይንም በሌላ የተያያዘ ህመም ከሆነ የጉበት ጉዳት የመሆን እድሉ ትንሽ ነው። የጉበት ጉዳት ያጋጠማቸው ሰዎች የማይለቅ የማቅለሽለሽ ስሜት ይሰማቸዋል። ይህ ስሜት የሚመጣው የጉበታችን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን የማስወገድ ሃይል ስለተዳከመ ነው። የምግብ አፈጫጭ ለውጥም ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ያስከትላል። በየግዜው የማቅለሽለሽ እና የማስታወክ ስሜት ጤናችንን በከፍተ...

"በነቀምቴ ለኦሮሞ ህዝብ ያስተላለፈው መልዕክት የአብይ ጭንቀት

ምስል
ዬማህበረ ኦነግ ውሎ አዳር። አንደበቱ ኦነግ ማይኩም ኦነግ ቅላፄውም ኦነግ። አማራን እንስበር ነው ተጀምሮ እስኪ ጠናቀቅ። "ከእንግዲህ አማራ ሁነህ ከአብይ ጋር በአንድ ቂጥ ካላራሁ ብለህ የምትጋጋጥ በግለሰብም ይሁን ቡድን ካለህ እርምህን አውጣ " "በነቀምቴ ለኦሮሞ ህዝብ ያስተላለፈው መልዕክት የአብይ ጭንቀት ሸኔን እንዴት መመለስ እንዳለበት ብቻ ነው የተጨነቀውጂ በፍጹም ለህዝቡ ሰላም፣ ልማት እና ብልጽግና አለመሆኑን በግልጽ አሳይቷል። ከተናገረው፥ እናንተ ወደኛ ኑ እንጂ ለሌላው በጭራሽ አታስቡ። ሌላው ያወራሉ፤ እኛ ግን ለኦሮሞ ነው የምንሰራው። እየሰራን ነው። ይሔ ብልጽግና የኦሮሞ መንግስት ነው። በዚህ ወቅት ስልጣኑ ከእጃችን ከወጣ በመቶ አመት ውስጥ አናገኘውም። በሰሜን በኩል ያሉት እያንገራገሩ ነው። እኛ ተደራጅተን እነሱን ማንበርከክ ካልቻልን እኛ ስልጣን ላይ ያለነው ብቻ ሳይሆን የምንጎዳው ኦሮሞ የሆነው ሁሉ ነው። በወለጋ በርካታ የተፈናቀሉ አሉ። እነዛ የተፈናቀሉት ለኛ የሚተኙልን ይመስላችኋል!? ሲልም በነቀምት ከተማ ከአራቱም ዞን ለተውጣጡ ለኦሮሞ ህዝብ ጥሪ አቅርበዋል። እናም ብዙ ጥያቄ በወለጋ ህዝብ ይነሳሉ። ለምሳሌ፦ በ1971ዓ.ም የትግራይ ህዝብ በዘመነ ደርግ በረሐብ፣ በጥይት እና በመከራ ውስጥ ሳለ፤ ወያኔ ነበር። አሁንም በወለጋ ያለው ችግር ይሔው አይነት ችግር ነው!? ኦሮሞ ሞተ!? ተሰቃየ!? ተራበ!? መንገድ አጣ!? ማብራት፣ ኔቶርክ፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት እና ጤና አጥቷል? መንግስት ይድረስልን ትላላችሁ!? መንገዱን ለማሰራት ኮንትራክተሮች፣ ባጀት፣ ማቴሪያል እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ስንልክ ይዘረፋል፣ ይቃጠላል፣ ሰዎች ይታገታሉ፣ ይገደላሉ። ይህን ሁሉ ታድያ እየሆነ ያለው በደርግ ዘመን እንደወያኔ አይነት የ...

#ለአማራ ህዝብ 40 ዓመት ሙሉ #ህማማቱ ነው።

#ለአማራ ህዝብ 40 ዓመት ሙሉ #ህማማቱ ነው። 27 ዓመቱ #ሥነ - ሥቅለቱ። #ዓራት ዓመቱ መቃብሩ! "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፫) የተገለለ የገደለ የተሳደደ የተወገዘ የተሰቃዬ የተገፋ የተጨቆነ የታሠረ የመከነ የተሰደደ የተወጋ የታፈነ የተሠወረ የታገደ የተወገዘ ሰቆቃው አማራ! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 21/04/2022 ተስፋችን አምላካችን ብቻ!  

በዚህ የጭንቅ ጊዜ እንዴት ሰው ጥል ያምረዋል?

የሚገርመኝ። በዚህ የጭንቅ ጊዜ እንዴት ሰው ጥል ያምረዋል? በዚህ የጭንቅ ጊዜ እንዴት ሰው ምቀኝነት ትዝ ይለዋል? በዚህ አስደንጋጭ ጊዜ እንዴት ዝና ሰው ትዝ ይለዋል? በዚህ የጭንቅ ጊዜ ፕሮፖጋንዲስትነት እንደምን ያምራል? በዚህ ጨለማ ጊዜ የሰው ልጅ ከበቀል ጋር እንደምን ጋብቻ ይፈፅማል? በዚህ ግራጫማ ዘመን ስለምን ሰውን ለማስከፋት ይጣራል? በዚህ ቀኑም ቀን፣ ፀሐይም ፀሐይ በማትመስልበት የሞት ዘመን ወገኑን ወገኑ እንደምን ያሳደዋል? እንደምንስ ያስረዋል? ስለምንስ ይገድለዋል ያስገድለዋል? የሰው ልጅ ጠላቱን ኮሮናን ወይንስ አምሳያውን የሰውን ፋጡር ይዋጋ? ሚዛኑን ሳስተውል የዕውነት ይጨልምብኛል። እማያስፈራ ነገር እኮ ዛሬ የለም። የኖራችሁበት ቤት ያስፈራችኋል። የኖራችሁበት ግቢ ያስፈራችኋል። የኖራችሁበት እቃ እራሱ ያስፈራል። መንገዱ ያስፈራል። መስኮት ከፍታችሁ ስታዩ አዬሩ ያስፈራል። የምታነሱት፣ የምትጥሉት ነገር ያስፈራል። ፖስታ ለመክፈት ትፈራላችሁ። ደብዳቤውን መክፈት አትደፍሩትም። እንዳታጥቡት ወረቀት ነው። እንዳትተውት ትሰጋላችሁ። ስለዚህም የፀጉር ማሞቂያችሁን ከፈት አድርጋችሁ በሙቀት አገላብጣችሁ ትገርፋታላችሁ። ፖስታው ሳይከፈት እኮ ነው ይህ ሁሉ ጉድ፣ ከተከፈተ በኋላ ደግሞ ደብዳቤውንም እያገላበጣችሁ በወከባ በወላፈን ታላጉታላችሁ። የምጥ ጊዜ ፈተና። እና በዚህ ወቅት ቂም፣ በቀል፣ ሸፍጥ፣ ሴራ፣ ትርምስምስ ሲል ስታዩት ይገርማችኋል። አጠገባችሁ ሞት እያጫወታችሁ፣ እዬኮለኮላችሁ እኮ ነው ይህ ሁሉ ክፋ መንፈስ ተሰንቆ ደግሞ ጉግስ የሚገጠመው። የሚገርመው ሰባራ ገል ይዘው እሳት የሚያጫጭሩት ናቸው። ብቻ ይገርመኛል። ሞት እና ሰው፣ ሞት እና ተፈጥሮ ተፋጠው የሸፍጥ አደንጓሬ ሲኮን እግዚኦ ነው ተሳህለነ። ልብ ይስጠን ስንደግፍም ዕውነትን ከማዳን፣...

ማህበራዊ ንቃተ ህሊና እና ማህበራዊ ንቅናቄ ሰቆቃው እንጂ ፕሮፖጋንዳ አላመረተውም።

  ማህበራዊ ንቃተ ህሊና እና ማህበራዊ ንቅናቄ ሰቆቃው እንጂ ፕሮፖጋንዳ አላመረተውም። ዕለተ ሮቡ ማዕዶተ ተናኜ በከበበሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ዛሬ ማዕዶተ ተናኜ ስለሆነ የሃሳብ ቀን ነው። እምጽፈውም ትዕግሥቱ ኑሯቸው ለሚያነቡ ቅኖች ነው። • ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ምንድን ነው? በጭልፋ ... ማህበራዊ ንቃተ ህሊና የህሊና ማቹሪቲ ነው። ህሊና የነቃ እና ያልነቃ ተብሎም ይከፈላል። ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደረግ የግለሰብ ንቃተ ህሊና ሲደረጅ እና ይህ የግለሰብ የንቃተ ህሊና አቅም ወላዊ ወደ መሆን ሲሸጋገር ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ይባላል። ማህበረወዊ ንቃተ ህሊናው ማህበራዊ ንቅናቄ ሊፈጥር ከቻለ አብዬት ነው የሚሆነው። አብዮት በሳቢያ ሳይሆን ምክንያታዊ በሆነ አምክንዮ የሚፈጠር ነው። በሳቢያ እና በምክንያት መሃከል ሰፊ የፍልስፍና ልዩነት አለ። በቀላሉ ሳቢያ ጫሪ ሆኖ ግን ጫፍ ቀሪ ነው። የሳብያ ውጤት ተላላ ነው። ለጥገናዊ ለውጥ ብቻ የሚሆን ነው። ምክንያታዊ ግን ከሥር ተነስቶ ቁንጮ ፍላጎት አቀንቃኝ ነው። ነገር ግን መሪ ይሻል። እንደ እና ፊደል ካስትሮ፤ ቼጎቢራ አይነት ማለት ነው። የዓለምን ሚዛን ያስጠበቀውም ያ ዝልቅ ተጋድሎ ነው። • መከራ የወለደው የበቃን አብዮት! ወደ ቀደመው ስመለስ ይህ ያዬነው የቆረጠ ትዕይንተ ህዝብ በፕሮፖጋንዳ የመጣ አይደለም። ፕሮፖጋንዳው ቢሆን ቅቤ አቅልጡ፤ የሞድ መኮንኑ፤ የፓርክ ሚኒስትሩ፤ አጤ ዝናቡ የሄሮድስ ዶር አብይ አህምድ ፕሮፖጋንዳ ኾሽታም አያስነሳም ነበር። በአማራ ክልል እሳቸው ከመጡ ወዲህ 5 ታላላቅ ገድለኛ ህዝባዊ ንቅናቄ ተፈጥሯል። ምኞቶኞች አርቲስት አልማዝ ...

በቃ! በቃን ሱባኤም ነው። በሱባኤ ወቅት በድዋ እና በፆም የተወለደ።

  በቃ! በቃን ሱባኤም ነው። በሱባኤ ወቅት በድዋ እና በፆም የተወለደ። • በቃን! ህዝባዊ አብዮትም ነው። ለህዝባዊ አብዬት የሥርዓት ለውጥ! ዕለተ ሮቡ ማዕዶተ ተናኜ በከበበሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) በቃ! ተደሞው በቃ ዕድምታው ለድርርድር የሚሆን አይደለም። ድርድር ውል ለበቃ! ግርግር ነው። በቃን! ለማድመጥ ጆሮ የሌለው ፖለቲከኛ ዓይን ያለው ጆሮ ከቤተ - እስራኤሎች ቢያፈላልግ ይሻለዋል። በቃ! ማለት በቀላል ቋንቋ ብርጭቆ ውሃ ቢሞላ ከዛ ላይ ጠብታ መጨመር አይቻልም። እንደዛ ማለት ነው። በቃ ተርጓሚ አስተርጓሚ አያስፈልገውም። በይቅርታ፤ ብምንትሶ፤ በቅብርጥሶ፤ በጓዳ ድርድር የሚሆን አይደለም። በቃ! ለዛውም የህዝብ በቃን! የሚጨመር የሚቀነስ ቦታ የለንም ነው። የምናደምጠው - የምንዋዋለው - ውል የለም ነው። ይህን የበቃን! ንቅናቄ ለመመራት የህልውና የተጋድሎውን ዲስፕሊን ለመሸከም ዲስፕሊኑን ምን እና ምን ነበሩ ብሎ ማጠዬቅ ይገባል። የህልውና ተጋድሎ የጫጉላ ሽርሽር አልነበረም እና። የህልውና ታገድሎ የግጥግጥ ዳንኪራ አይደለም እና። ድንቁ ነገር ረመዳን በገባ ማግሥት ፤ ሁዳዴ ሳይጠናቀቅ ነው ይህ ሞገድ የተነሳው። ሞገዱ ከሰማይ ነው ብዬ ነው እማምነው። ግልገል በለስ ላይ ነው የተጀመረው። የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ቀጠሉት፤ ፍኖተ ሰላም ተከተለ ከዛ ሙሉ ጎጃም እና ሙሉ ወሎ በአኃቲ መንፈስ እራሱን አደራጅቶ ቀጠለበት። ተጋድሎው የህዝብ ነውና የኮፒ ራይቱ ነገር ላይ ከማተኮር የወለቀ፤ የሾለከ፤ የተነደለውን የኃላፊነት ልክ ቁጭ ብሎ መመርምር ያስፈልጋል። በቃን! ምንም ነገር አናስተናግድም ነው። ቅ...

Abiy Ahmed’s Vengeful Actions towards Amhara: Biting the Hand that Feeds Him By Henok Abebe Human Rights Advocate

ምስል
  April 17, 2023   Updated:  2 hours ago ·    Abiy Ahmed’s Vengeful Actions towards Amhara: Biting the Hand that Feeds Him April 17, 2023 By   Henok Abebe Human Rights Advocate ·        Introduction  In his book entitled “War and Conflict in Africa”, Paul Williams points out that African leaders tend to instrumentalize disorder and use violence to assert authority as a survival strategy whenever they feel their legitimacy is challenged. Abiy Ahmed’s leadership in Ethiopia is no different from the well-worn path of African despots who govern impoverished societies from the comfort of opulent palaces bulwarked by merciless soldiers from their own citizens. When he felt that Tigray Peopel’s Liberation Front(TPLF) has challenged his authority and questioned his legitimacy and even ability to lead Ethiopia, he completely forgot the fact that he said he is “his brothers’ keeper and his sisters’ protector” on th...

መደራጀት ሊፈራ አይገባውም።

ምስል
  ይህ ግርባው ብአዴን ዬወጣቱን መንፈስ ሲያደነዝዝ በነበረበት በ2011 ዬጻፍኩት ነው። መደራጀት ሊፈራ አይገባውም።   • እፍታ። መደራጀት ኃይል ነው። መደራጀት አቅም ነው። መደራጀት ስንዱነት ነው። መደራጀት ፍቅር ነው። መደራጀት አብነት ነው። መደራጀት የታማኝነት ማስፈጸሚያ ነው። መደራጀት የህሊና መቅኖ ነው። መደራጀት ዓላማና ግብ ያለው ሰብዕና ማለት ነው።መደራጀት የአብሮነትም አንባ ነው። መደራጀት የሥን - ልቦና ቅዬሳ ተቋም ነው ለአዎንታዊ ከተጠቀምንበት። ይህችን ለመግቢያ ከከሽንኳት በኋላ እምጠቅሰው በመደራጀት ዙሪያ ያሉ ጥቂት ነገሮችን ነው። በጽንሰ ሃሳቡ ዙሪያ ሌላ ጊዜ ብመለስበትም ትንሽ የአማራ ወጣቶች በገጠማው አንኳር ችግር የምለው ይኖረኛል። • ወግ። የአማራ ወጣቶች እዬተደራጁ ነው። ማህበራቸው ነፃ እና ገለልተኛ ነው። ማህበራቸው ዓላማ እና ግብ አለው። ዓለማ እና ግብ ደግሞ የአንድ ድርጅት መሰረታዊ ጉዳይ ነው። የአማራ ወጣቶች መደራጀት የአዳማን ሥርዕዎ መንግሥት አላስደሰተም። ስለሆነም እውቅና እንዲነፈገው ተደርጓል። ከሰኔ 15 በፊት በነበረው ሰንበት የደብረታቦር ወጣቶች ኢንጂነር ይልቃልን ጌትነትን ጋብዘው ነበር ነገር ግን ታግደዋል። ይህ መቼም እኔ እብደት ነው የምለው። ሰው ያበደ ዕለት ጋብቻን ያግዳል። ልክ እንደ ባቢሎን ግንብ ቀያሹ እንደ አቶ በቀለ ገርባ ማለት ነው። ነፍሳቸውን ይማረውና ዶር አንባቸው መኮነን በመሩት ጉባኤ ደብረታቦር ላይ የወጣቶች ጉባኤ ነበር። አቶ ዮኋንስ ቧያለውም ተገኘተው ነበር። ሁለተኛ የወጣት ድርጅት አስፈላጊ አለመሆኑ በአጽህኖት ሲገልጹ ሰምቻለሁኝ። በፖለቲካ በሳል ከሆኑ አንድ የፖለቲካ ሊሂቅ የማልጠብቀው ገለጻ ነበር። በተፎካካሪያቸው በአብን ላይም የነበራቸው ምልከታ ጤናማ አልነበረም። ፖለቲካ በ...