ልጥፎች

Zenebe Kassie እሙኃይ እንኳን ደስ አለወት። እናት ዓለም በረከተወት ይድረሰኝ። አሜን። እሙኃዮዋን እናቴን ያስታወሰኝ እለት ነበር።

ምስል
  እሙኃይ እንኳን ደስ አለወት። እናት ዓለም በረከተወት ይድረሰኝ። አሜን። እሙኃዮዋን እናቴን ያስታወሰኝ እለት ነበር። እንደአከላተምኳት ፈቃዷን ሳልፈጽም መራራ ስንብት ሆነ።      ይህ መከራ የመጨረሻ ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው። ከውስጤ ስለ እናቶቼ አስባለሁ። አንገላትተናችኋል። አሰቃይተናችኋል። ሃዘን ስጦታ አቅርብነልቻኋል። ይቺ አገር ኢትዮጵያን ብለን ግን እራሳችን ረስተን ወጣትነታችን፤ ሐሴታችን ሁሉን ሰጥተን አሁንም እዛ ረግረግ ውስጥ መሆናችን ሳስበው ምጡ ምጥ ብቻ አይደለም። በሽታ ይገዛል። የሆነ ሆኖ ከእሱ አብራክ የተፈጠሩ ልጆቹ፤ እሱንብላ አብራ እምትከላተመው የትዳር አጋሩም ያሳዝኑኛል። እንኳን ደስ አላቸው። ብቻ ለመኖር ለወሰነው ቢያንስ ይህን አቃለናል ብዬ አስባለሁ። ለዘኔ ከእህት። "ላም እረኛ ምን አለን" እባክህ አዳምጥ። በጥዋቱ ጽፌልህ ነበር አልሰማህኝም። 1) በምግብ ሊበክሉህ ስለሚችሉ ብርቱ ጥንቃቄ አድርግ። 2) ቅንነትህን በቅጡ አስተዳድረው። ፖለቲከኛ ቅንነቱ ብቻ ለድል አያበቃውም። ጥበብ ያስፈልገዋል። 3) ገራገርነትህንም እንዲሁ ማኔጅ አድርገው። ዓላማን በራስ እጅ ለማበጀት መወሰን ጎዳናህ ይሁን። 4) ለአንተ ሲሉ 12993 ተማሪወች ቤተሰቦቻቸው ወደ 64 ሺህ ከተስፋ ውጪ መሆናቸው ግቡን እና ስኬቱን አጥናው። ለቀጣዩ እርምጃ ስለሚረዳህ። 5) የህዝባችን መሰዋት በሚቀንሱ በሚያመጣጥኑ መንገዶችብቻ ጥናት ውሰድ። ብዙውን በርደን ውጭ ያለው ይፈጽም። እናንተ ቋያ ውስጥ ናችሁ እና። 7) ለጥሞና አላማህም። ቆራጥ ነህ። ብቻህን ለአጅም ጊዜ የገደምክ ቆራጥ ወጣት ነህ። አገር ተደፈረችሲባል ነው የወጣህው። ያን ጊዜም ጽፌ ነበር። እዛው ሁን ብዬ። በቀለኛ ሥርዓት ስለሆነ ይቀሙናል በሚል። አሁንም #ጥሞና ውሰድ። እራስህ...

እግዚአብሄርን መዳፈር ይቁም። ስትትበሰበሱ፤ ስትዝረከረኩ አቅምን በአቅም ማስተዳደር ተስኗችሁ ከኋላዋ ዬተፈጠሩ አገሮችን እርዳታ ዬምትለምን አገር ተይዞ ፈጣሪን አሻቅቦ መናገር ልክን አለማወቅ ነው።

ምስል
እግዚአብሄርን መዳፈር ይቁም። ስትትበሰበሱ፤ ስትዝረከረኩ አቅምን በአቅም ማስተዳደር ተስኗችሁ ከኋላዋ ዬተፈጠሩ አገሮችን እርዳታ ዬምትለምን አገር ተይዞ ፈጣሪን አሻቅቦ መናገር ልክን አለማወቅ ነው። እያንዳንዱ አመክንዮ፤ እያንዳንዱ ሰብዕና ለተፈጠረበት ሰማያዊ ሚስጢር ህግም፦ ድንጋጌም አለው። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"   በህይወቴ የመጀመሪያው ረጅም እርእስ ነው። ዝም ብዬ አዳምጣለሁ። ከልክ ሲያልፍ ግን ለሃጣን የወረደ ለፃድቃን እንዳይሆን መናገር ግድ ይለኛል። ሁለት ጊዜ ስለ ጅንኑ ሂደት ጥፌያለሁ። አንድ ጊዜ አቶ ሂደት አፍንጫህን ላስ የሚል እርእስ ያለው ነበር። ደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው አውጥተውልኝ ነበር ብሎጌ ላይም አለ። ሁለተኛውን እርእሱን አላስታውሰውም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ አቅም የለውም። ኢትዮጵያን ለመምራትም ቅባዓ የለውም። ምክንያቱም ፈጣሪውን ተዳፍሮ ስለሚነሳ። ጥሞና ስለለው። ስለተደረገለት ጥሞና ሦስት ቀን ማድረግ የተሳነው ከአመት በላይ በካቴና ሲያባጀው ያለው ጨካኙ ፖለቲካዊ አመራር አያገናዝበውም። ሚስጢር ተላልፎ ይህ ስለመፈፀሙ። ከእስር ሲለቀቅም ጥሞና የለም። በእስር ወቅት የተፈጠሩ የኃይል አስላለፎች እና ተደሞወች የአረፍተ ነገር ድርድር ይመስለዋል። እዬተንደረደረ ሄዶ ዘው ነው። ይሉኝታ ስለመፈጠሩም ማስተዋል ዬለም። ዛሬ ሞልቶ በቅጽበት ለሚፈስ፤ ዛሬ ሰክኖ በድንገት ለሚታወክ፤ ዛሬ ተደራጅቶ ለታሪክ ሳይበቃ #በአንጃ ለሚዥጎረጎር፤ ዛሬ ዲል ባለ ድግሥ እና ድጋፍ ጉባኤ ተደምጦ በማግስቱ ሰብሳቢ አልባ ሲበተን ውሎ ለሚያድር የኢትዮጵያ የፖለቲካ አልፎ ተርፎ በፈጣሪ ሥራ፤ በፈጣሪ ጥበብ፤ በፈጣሪ ታምር ገብቶ ማነኮር ጎንደሮች ባለ ቅኔ ናቸው እና "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል" ይባላል። ልክ የለሽ ዝልኝጉዞ ...

#እያዬን የማይታዬን የዘመን የኦዳወገዳ ዘረፋ።

ምስል
#እያዬን የማይታዬን የዘመን የኦዳወገዳ ዘረፋ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ዕንባቆም ፲፮ ቁጥር ፫)   የኦዳ ሥርዕወ ሥርዓት እና የአድዋ ሥርዕው ሥርዓት ጦርነትን በሚመለከት ፍላጎቱ የአንድ ወገን ብቻ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ የታሪክ ዝበት ይመስለኛል። ነው አላልኩም። ኧረ ምን በወጣኝ። ይመስለኛል ነው። እራሱ አቶ ሰኩቶሬ የማን ናቸው? የአማራ እና የትግራይ ጦርነት ቀድሞ ታጭቷል ባይ ነኝ። ያ አልሳካ ሲል የሆነው ሆነ። በኦዳ ገዳ ሥርዕው ሥርዓት ጦርነት የተፈለገበት ምክንያት በሰላም ሥልጣኑ ስለተገኜ የጦርነት ድል ናፈቃቸው። ጫካው ቤተ - መንግሥታቸው መሬትን ደበደበ። ቀውስ አደራጅቶ ቀውስ አመረተ። ፍላጎታቸው ያለፋቸውን ታሪክ ሁሉ የእነሱ እንዲሆን ተመኙ። ፈፀሙትም። ከመካከለኛው ዘመን የቀደሙ ትሩፋቶችን በወረራ #በጭልፋም #በወጨፎሙ ተካኑበት። "ወደ አባቶቻችን የ3 ሺህ የታሪክ ዘመን ተመልሰን በጋሜ ሚዲያ ልጆቻችን ታሪካቸውን ያውቁ ዘንድ እያስተማርን ነው" ሲሉ አላፈሩም አቶ ሽመልስ አብዲሳ በ2014 የሬቻ ዋዜማ ላይ። ልብ ያለው፣ ያስተዋለው የለም። 2500 ዘመን በጠራራ ፀሐይ ሲዘርፋ እፍረት አልሰራላቸውም። የታሪክ ሙሁራን፣ የታሪክ ሊሂቃን ነጥቡን አንስቶ የሞገተ አላዬሁም። ከውስጤ የገባ አመክንዮ ስለነበር ያሉት ቢኖር ሊቃውንቱ አድኜ እከትበው ነበር። #ጦርነቱን ናፍቆታል ኦዳወገዳ? የአድዋ ሥርዖም። ለምን? የነበረውን ሠራዊት ማፍረስ ይፈልግ ስለነበር። ማለቁም ፕሮጀክታቸው ነው። ለኦነጋውያን ቦታ ይለቃላ። ይህ አንደኛው እና ሁለተኛው ነው። ሦስተኛው አጤወቹ፣ ደርግ ህወሃትም ጦርነት አስተናግደዋል። ዝልግልጉ ኦህዴድም በሌሎች መሰዋት ኪሳራ በዚህ ታሪክ #ማለፍን ፈለገ። አዲስ የገዳ ታሪክ እዬፃፋ ነው። ...

ሆዴን ባር ባር ቢለውም። ይህን ፍፅምና ትህትና ነው እያሰደደው ያለው የቤተ - መንግሥቱ ደራጎን።

ምስል
ሆዴን ባር ባር ቢለውም። ይህን ፍፅምና ትህትና ነው እያሰደደው ያለው የቤተ - መንግሥቱ ደራጎን። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" #ለምን ስለምን ሆዴን ባር ባር አለው? ብፁዓንን ሳይ፣ ይህን አውሬ ሥርዓት ሳስብ፣ ቅንጣት ስለማላምነው እንደ ሌላው ሁለመናችን እንዳያራግፈን እሰጋለሁኝ። እንዳያሳጣን እሰጋለሁ። እንደዚህ ዘመን ብፁዓን አቨው በሥጋ በብዛት የተለዩበት ጊዜ የለም። በአራት ዓመት ውስጥ ብዙ ነገር አጥተናል። አውሬ ዘመን ነውና። ስልቱን አናውቀውም። ይፈፀማል ዕንባችን አፍሰን ዝም እንላለን። ለማስተዋል፣ ለጥሞና ጊዜ ወስደን አናውቅም። እንጂ ለተዋህዶ ምፃዕት ዘመን ላይ ነን። አጥንተውናል። በአጠኑን ልክ በስውር እያጠቁን ነው። ዛሬ እምናዬው መልካም ነገር የነገ #ሃዘን እንዳይሆን እሰጋለሁኝ። ምነው በቀረብን እንዳንል። ብፁዑ አባታችን አቡነ አብርኃም አጽናኛችን፣ ጥጋችን፣ በከፋን ሰዓት ከጎናችን የማይለዩትን ሳይ ሆድ ይብሰኛል። ለሳቸውም ለእኛም የመኖር ዋስትና ባህርዳር ምርጫዬ ነበር። ይህን ሥርዓት አናውቀውም። ከአጠቃን በኋላ ነው የሚገባን። ስንቀደም እንጂ #ቀድመነው አናውቅም። እና መጪው ጊዜን ፈራሁት። ብፁዑ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ (ዶር) እሳቸውም ቢሆኑ በፈተና የፀደዩ፣ ርትፁ ናቸው። ልስሉስ። የእኛ፣ የውስጥ ናቸው። ቅርባችን ናቸው። የእሳቸውም ህይወት ያሳስበኛል። ይህን ሥርዓት አምኖ #ልብ #መጣል አይገባም ባይ ነኝ። ከፈጣሪ በታች። ይህ ድንቅ ሥራ የፈጣሪ ቢሆንም ዲያቢሎስ የሰፈነበት የቤተ - መንግሥቱ ዓውድን ግን አላምነውም። እርቅ እና ውጤቱ እኛ በቅንነት ብናዬውም የሆነው ነገር ዘለግ ብሎ ታስቦበት፣ ለአንድ ትርፍ ወዘተረፈ ኪሳራ ተደራጅቶ አይቻለሁኝ። እናም እንደ ተዋህዶ ልጅነቴ ውስጤ በስክነት፣ በአትኩሮት ከመከታተል ው...

#በራስ መተማመን ሚዛኑን ሲስት እና ጠኔው።

#በራስ መተማመን ሚዛኑን ሲስት እና ጠኔው። ዕለተ ሃሙስ ሰጋሪው በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) #ጠብታ ። በራስ መተማመን የሰብ ተክለ ሰውነት የግንባታ ሂደት ቀዳማይ ጉዳይ ነው። በራስ መተማመን ምንጩ ነፃነት ነው ብዬ አምናለሁ። ነፃነት የአገር፣ የሙያ፣ የቤተሰብ ወዘተ ሊሆን ይችላል። ግን አያያዝም፣ አፈፃፀምም፣ አስተዳደርም ይጠይቃል። #ዕፍታ ። አንድ ልጅ ከእናቱ ማህፀን ሲወጣ ራቁቱን ነው። እርግጥ ነው ለዬት ብለው የሚወለዱ ልጆች አሉ። ተክሊል ለብሰው ተወለዱ የሚባሉ። ተክሊሉ እንደ ሞራ ነገር ነው ይህ በጎንደር ይትበኃል የተለዬ አክብሮት አለው። ያ ሲቀደድ ያው ባዶ ገላ ነው። ልጆች ሲወለዱ አካላቸውን ብቻ ይዘው ነው የሚወለዱት። የሰብዕና ግንባታው መነሻ ሆነ መድረሻው ከተዉለዱ በኋላ ነው የሚታነፀው፣ ውኃ ልኩም የሚጀመረው እንደ ማለት። እያንዳንዱ ወላጅ ባሊህ ሊለው የሚገባ ቁምነገር ቢኖር እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መክሊትም #መልዕክትም ይዞ መወለዱን ነው። #አሳዳጊነት ። ……… ይህን በቅጡ ዕውቅና ሰጥተው ገርተው ያሳደጉ ወላጆች ወላጅ ሊባሉ ይገባቸዋል ብዬ አስባለሁ። ወላጅ ስል የወለደ ብቻ ሳይሆን ያሳደግም። በኢትዮጵያ ይትበኃል ጎረቤትም የወላጅ ያህል ነው፣ የማር ልጅነት፣ የክርስትና ልጅነት አብሮ የሚሄድ ሲሆን የትዳር አጋር ልጅም እንዲሁ። "እንጀራ እናት እንጀራ አባት" የሚለውን አልወደውም። ደወሉ አሉታዊ ነውና። #ተመክሮዬ ። ተፈቅዶም የሚሰጥ ልጅ አለ። እኔ እጅግ የምወዳቸው፣ የምሳሳላቸው ሁለት ጓደኞች ነበሩኝ ኦሮሞወች ናቸው። ሁለቱም የአንድ እናት አባት ልጆች...

የአማራ ፖለቲካ ቅንነት ማንፌስቶው ሊሆን ይገባል። ቅንነት አሻራው ነውና።

የአማራ ፖለቲካ ቅንነት ማንፌስቶው ሊሆን ይገባል። ቅንነት አሻራው ነውና። አንድ ተመስገን የምለው ጉዳይ አለኝ። በዘመነ 60ዎቹ የአማራ ፖለቲካ እንኳንም አልተጀመረ። መርዝ ይሆን ነበር። እናት አገሩን ኢትዮጵያን ከውስጡ የሚያወጣ ሳጥናኤላዊ መንፈስ ይውጠው ነበር። ተፈጥሯዊ እና ሰዋዊ መሆን ይሳነው ነበር። የሸር ባንድ ይኖረው ነበር። የሴራ ኦርኬስተር ይኖረው ነበር። የኢጎ ቁልል ይንጠው ነበር። መገዳደል መርኹ ይሆን ነበር። ስለዚህም እግዚአብሄር አምላክ ተማልዶት በ21 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነጥሮ ወጣ። ይህ ማለት ሰዋዊ እና ተፈጥሯዊ መንፈሱን ያጎላለታል። እኔ እንደ ሥርጉተ በህወሃት ተፈጥሮ እና ሰው ገዳይ ማንፌስቶ የተቀረፀው የተጋሩ ትውልድ ያሳዝነኛል። በኦነጉ የጭካኔ አውራ በማህበረ ሌንጮ የተፈጠረው የቁቤ ትውልድም ያሳዝነኛል። የሚገርመው፣ ግዙ፣ ንዱ ተብለው አሁንም ሰው አጥፊ ትል አስተሳሰብ ሲያመርቱ ውለው ያድራሉ። የለማወአብይወአባዱላ ዴሞግራፊን እሰቡት። የአቶ በቀለ ገርባን ጭራቃዊ ጨለማ የዘፍጥረትን ገዳይ ማንፌስቶ አስተውሉት። እንኳን የቁቤ ትውልድ ወጣቶችን ማንዴላ የተባሉት ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ጭካኔ ማርኳቸው ቀኝ ጌታ ሆነው ፀረ ሰው ራዕይን ወደውት፣ አቅፈውት በአውራነት እዬተመሩበት ነው። ሜዳው አልበቃቸውም ብሏል። ይህ አስቀንቶ ወደዚህ ሲኦላዊ መርዛማ መንፈስ የአማራ ፖለቲካ ዘንበል ማለት ለሰከንድ አያስፈልገው። ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር እንጂ በሽተኛ ትውልድ ለመፍጠር አቅም፣ ጊዜ፣ መንፈስ ሊዋጣም፣ ሊባክንም አይገባውም። ሰው ሆኖ ለሰው ልጆች የተረጋጋ የመኖር ዋስትና መትጋት ያስፈልጋል። ሰውነት ደንበር፣ ወሰን የለውም። ኢትዮጵያ የራባት ሰዋዊ፣ ተፈጥሯዊ ሥርዓት ነው። ለዚህ መትጋት የአማራ ፖለቲካ ሁነኛ መሥመሩ ሊሆን ይገባል። ይህን ለማድረ...

ፈጣሪ አምላክን ስለ ፍጥረቱ ሚስጢራት አትዳፈሩት።

ምስል

Unity Einheit አንድነት።

ምስል

No War

ምስል

ዬሞት ተማህጽኖ፣ የስቃይባለተስፋ።

ምስል
ዬሞት ተማህጽኖ፣ የስቃይባለተስፋ።     ምን እና ለምን ስለምንስ። ምን አድርገን ተገኜን??? ጭንቀት ያነሰን መሰለወትን? መሬት ደብድበው ማት አውርድ ብለው መና ለቤተ እግዚአብሄር ዬሚልኩ መሪ ነበሯት። ኢትዮጵያ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይም በድምጽ ያገኙትን በትረ ሥልጣን በደም ጎርፍ አጥለቀለቁት። እኛ ቋያ ላይ ያሉ ቅኔወቻችን ነገን እንዲዩ እንዴት ዞር ሊሉ ይችላሉ እያልን እንጨነቃለን ህግ በሌለበት አናርኪዝም በሰፈነበት ባዕት፣ ባረገረገ ዙፋን ልቀቀል ብሎ መፍቀድ ሥምዬለሽ ማት ነው።።።።።።። ውጭ አገር እንደሚሰለቻቸው አውቃለሁ። ግን ይህም መከራ መቀበል ነው። እናቴ አዘውትራ ፃድቅ ትለኝ ነበር። የቀረብኝን ነገር ሁሉ ኡስባ። ፆምም ሲመጣ የሁልግጤ ፆሚነሽ እኮ ትለኝ ነበር። ከሚወዱት ባተሌነት መለዬት መከራን ፈቅዶ መቀበልም ነበር። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" ዛሬ ምዕራፍ ዘጠኝን ልጀምር ሃሳብ አልነበረኝ። ሦስት ሃሳቦች ሲሞግቱኝ አድረዋል። አንዱ በቤተሰብ ጉዳይ ነው። ሁለተኛው ውሳኔ ነው። ባርች ሆይ ይቅርታ አድርጊልኝ። ሰላም ስጧቸው ቢያንስ አንቺ በመልካምም ቢሆን ሥማቸውን እንዳታነሺ ብለሽ የህማማት ዋዜማ ቃል አስገብተሽኝ ነበር። ይህም በመሆኑ ያዘጋጁት ዬሽግግር ሰነድ በማን እና በምን አመክንዮ እንደ ተጨናገፈ ስገልጽ ኢዴፓ እያልኩ ነበር። የሆነ ሆኖ አሁን ሞት ውሰደኝ፣ ጭንቀት እና ስቃይ ራዕዬ ይሁን ብለው ሲወስኑ ዝም ልል ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። ፈጽሞ። ላም እረኛ ምን አለ ዬእኛ ፖለቲከኞች ድርቅ ዬመታው አመክንዮ ነው። የብዙ ነገር ውድቀት፣ የብዙ ነገር ኪሳራ ዬሚነገረው ስለማይደመጥ ነው። ላደለው ንግግር ብቻ አይደለም ዬሚደመጠው። ፀሃይ አድማጭ ትሻለች። ንፋስ አድማጭ ይሻል። ተፈጥሯዊ ወጀብ አድማጭ ይሻል። የወፎች ዜማ አድማጭ ይሻል መ...