ልጥፎች

አማራ ክልል:- ለወራት የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ዐውድ እና አሉታዊ የሰብአዊ መብቶች እንድምታው

አማራ ክልል :- ለወራት የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ዐውድ እና አሉታዊ የሰብአዊ መብቶች እንድምታው October 30, 2023 Press Release ተፋላሚ ኃይሎች ሲቪል ሰዎችንና ንብረቶችን፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን እና መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ከማድረግ ሊቆጠቡ፣ መንግሥት የማኅበራዊ አገልግሎቶች እዲቀጥሉ አስቻይ ሁኔታ ሊፈጥር ይገባል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ( ኢሰመኮ / ኮሚሽኑ ) በአማራ ክልል የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ላስከተለው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዘላቂ እልባት ለመስጠት ሰላማዊ መፍትሔ ማፈላለግን ጨምሮ፣ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል የሚያግዙ አፋጣኝ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በተለያየ ጊዜ ባወጣቸው መግለጫዎች ማሳሰቡ ይታወሳል። ኮሚሽኑ ግጭቱ በሰብአዊ መብቶች እና በማኅበራዊ እንቅስቃሴ ላይ ያስከተለውን አሉታዊ ውጤት በቅርበት መከታተሉን ቀጥሏል፡፡ በዚህም መሠረት በተለይም የሚመለከታቸውን መንግሥታዊ ኃላፊዎችን፣ በግጭቱ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን፣ የዐይን ምስክሮችን፣ተጎጂዎችንና የተጎጂዎች ቤተሰቦችን በማነጋገር መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ሲያሰባስብ ቆይቷል። ይህ መግለጫ ይፋ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ በክልሉ ብዙ ወረዳዎች ውስጥ የትጥቅ ግጭት የተከሰተ ሲሆን፣ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ . ም . ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ የአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በተለያየ ደረጃና ጊዜ የትጥቅ ግጭት ተካሂዶባቸዋል። በተጨማሪም እነዚህ አካባቢዎች ወይም ወረዳዎች በአንድ ወቅት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣ በሌላ ...