ህወሃት #ቤርሙዳ ትርያንግል ነው። ቀደምት ከተማዋ ናፍቆቴ ደብረታቦር #ጠቀራ መልበሱ ሐሤቱ ለማን ይሆን?
ቀደምት ከተማዋ ናፍቆቴ ደብረታቦር #ጠቀራ መልበሱ ሐሤቱ ለማን ይሆን? ህወሃት #ቤርሙዳ ትርያንግል ነው። "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።" #ምዕራፍ ፲፰። እንዴት አረፈዳችሁ ውዶቹ ውቦቹ። የሚናፍቀኝ፤ የምሳሳለት የደብረታቦር ከተማ መንደዱን ሳደምጥ በሃዘን ውስጥ ሆኜ ነው። በብልጽግና እና በህወሃት መካከል የተደረገውን ጦርነት በሠላም ሲቋጭ ተረፋልኝ ብዬ ከደብረብርሃን ጀምሮ ያሉ ከተሞችን ስዘረዝር #ደብረታቦር ከተማ አንዱ ነበር። ሙሉ ለሙሉ በህወሃት ወረራ እና የበቀል እርምጃ ህወሃታውያን ሳያሳኩት ከቀሩ ከተሞች የደቡብ ጎንደር ርዕሰ መዲና የታሪክም #ቀንዲል ደብረታቦር አንዱ ነበር። ይህ የሰሞኑ መጥፎ አጋጣሚ የታሪክ #ጠቀራን ሳደምጥ ውስጤ አዘነ። ደብረታቦር አልባሌ ከተማ አይደለም። በጣም ነው የማውቀው። ቀበሌ መንደሮችን ሁሉ። ዝክረ ታሪኩ ዘለግ ብሎ ከሚጠቀስባቸው ከተሞች አንዱ ደብረታቦር ነው። የታሪክ ድርሳንነቱ በክብር ጥበቃ ሊደረግለት ሲገባ እንዲህ አመድ ሆኖ ማዬት ውርዴት ብቻ ሳይሆን #ውርዴም ነው። ማን ይፈጽመው ማን አላውቅም። እኔ ከቦታው ስለለሁኝ፤ ማንንም ስለማላገኝ ትክክለኛውን መረጃ ለማግኜት አልችልም፤ ማን ምን ፈጸመ የሚለውን። በስማ በለው ደግሞ ለህሊና ዳኝነት ይቸግራል። ግን ከአመድ፤ ከጭስ፤ ከውድመት የሚታፈስ ቅርስ እና ውርስ እንደሌለ ጠንቅቄ አውቃለሁኝ። ያሳዘነኝ ይህ ነው። ወረታም መቀጠሉን ሰምቻለሁኝ። ወረታ ወሳኝ ከተማ ነው። ይህ ለህወሃት ለተስፋው ጥሩ መደሊድል የሚፈቅድ ስትራቴጂያዊ የድል ብሥራትም ነው። ወደ አዲስ ዘመን፤ እንፍራንዝ፤ ጸዳ፤ ጎንደር ከተማ ለማቅናት፤ የአዲስ አበባ ጎንደር መንገድን ለመዝጋት፤ የ...