የኦነግን ዓላማ ለመሸከም አቅም የለንም። አቅም ለማዋጣትም አንፈቅድም!

እንኳን ደህና መጣችሁልኝ
ምርመራ።
ክፍል አንድ።
„እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“
መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
                                                     
                          ይህ የኦሮማማ አይዲኦሎጂ ትርፍ ነው። 

ውዶቼ ክብረቶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? የበታችነት ባይረስ ፋሽታዊ ዕሳቤን እንደሚወልድ አሁን እያስተዋልኩኝ ነው። ፋሽታዊነት መንፈሱን የሚመራው መርህ ጥላቻ ነው። ጥላቻ ደግሞ የመንፈስ ሪህ ነው። ሥነ - ልቦናንም ያደቃል። ጠቡ ከሰውኛ ተፈጥሮ እና ስኬት ጋር ስለሆነ።
  
ይህ የመንፈስ ሪህ ለመፈወስ ደግሞ አላዛሯ ኢትዮጵያ መንገዱን ገና አልጀመረችውም። እርግጥ ነው ቀደም ባለው ዶር አብይ አህመድ የፈላስማው ዶር ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ከዶር ምህረት ደበበ ጋር ማይንድ ሴት ላይ አብረው ይሰሩ ነበር። እኔም የዶር አብይን መንፈስ የተዋወቅኩት በዚህ መስመር የፍቅራዊነት እንቡጢጣ ፕሮጀክቴን ስሰራ አፍሪካ ላይ ምን በመከናወን ላይ እንዳለ ሳስ ነው ያገኘኋቸው።

ዶር አብይ አህመድ በፖለቲካው መድረክ ጎላ ብለው ከመውጣታቸው በፊት ሲወገዙ ፊት ለፊት ወጥቼ ለመሞገት ያስቻለኝም ያ የቆዬ ጥሪት ስለነበረኝ ነው። ሰውኛ ጠረን ነበራቸው። ተፈጥሮኛ ጠረን ነበራቸው። የ አገር ፍጹም ተቆርቋሪነት እሸት ጠረን ነበራቸው።

ስለዚህም ነበር ደፍሬ እመመሰክረው የነበረው። ስለምን የህሊና ዕጠባ የሚጀምረው እውነትን በተፈጥሮው ልክ መቀበል ስለሆነ። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከእውነት ጋር ይዘልቃሉ ብዬ አስብም ነበር፤ እኔ ተስፈኛ ነኝና።

ከመስከረም ጀምሮ በማዬው ነገር ግን ያ የማይንድ ሴት ቤተኝነት በቁመናው ልክ በሳቸው ውስጥ ስለመስረጹ ዳገት ሆኗል።  የቆሞስ ስመኛው በቀል ህልፈት እና የቤተሰቦቹ መከራ ዕድምታው ለዜግነት ፖለቲካ ባይታዋር ሆኖ አግኝቻለሁኝ፤ በዚህ ፈተና የዜግንት ፖለቲካ የሚያራምዱትም ሆነ የ ኢትዮጵያዊነት አወራ ነን የሚሉት ከመንፈሳቸው ሊያስጠጉት አለመፍቀዳቸው የፈተናችን ጥልቀት የሚያሳይ ነበር። በመጎዳት ውስጥ እንኳን የክት እና የዘወትር የቤት እና የደጅ ዜግነት አለበት። እኛ ገና ነን።

ወደ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ስመለስ የቡራዩ ጭፍጫፋ እና ዕድምታው፤ የአዲስ አባባ ጭፍጨፋ እና ዕድምታው። የጌዲኦ ህዝብ ስውር ጭቆና እና ዕድምታው፤ የለገጣፎ ለገዳዲ የግርዲር ፍርሻ፤ የሰበታ መከራ እና የተሰፋው ዝቅዝቀት ጉድጓዱን ከሳቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ጋር ሳነጻጽረው እሳቸውም እውነት የሚያስፈራቸው ሆነው ነው ያገኘኋዋቸው። ወገንተኝነታቸው ለእውነት ሳይሆን ለሥጋዊ ሥልጣናቸው ልዕልና እና ለድርጅታቸው ለኦዴፓ ህልውና ግንባታ ስሰታምነት ሆነው ያገኘኋቸው።

„የጃኬታችን እናውልቅ ፍልስፍና“ አሁን ላይ አክብሩኝ፤ አወድሱኝ፤ ቀድሱኝ፤ የፈለገ ብሰራ አሞግሱኝ ብቻ ሳይሆን ድርጅቴም እንከን የለበትም ባይም ናቸው። በዚህ ሁሉ የሰብዕዊነት ቀውስ ውስጥ ቀውስ ፈጣሪዎች የራሳቸው ወገኖች ሆነው እሳቸው አንበሳ የሚሆኑት በዕውነት ፈላጊዎች ላይ ብቻ ሆኗል።

የጥላቻ ፈላስፋዎችን እነ ጃዋርውያን፤ በቀላውያን፤ ጋቢሳውያን በሚመለከት ደግሞ ከአንበሳነት የወረደ ሰብዕና ነው ያስተዋልኩት። እውነት በጠ/ሚር አብይ አህመድ ነፍስ ውስጥ መፈቅፈቋንም ተረድቻለሁኝ። ስረዳው ደግሞ እዬመረረኝ ነው። ስለምን በዚህ ውስጥ አሳቸውን አገኛቸዋለሁኝ የሚል እሳቦት ስላልነበረኝ።  

ይህ ሰብዕና ከሌሎች ከቀደሙ ንግግሮቻቸው ጋር ሳጣጥመው አልገጠም ብሏል። በዚህ የራስግጭት ጉዳይ የፈተናው ተራራ ያለው በጠ/ሚር አብይ አህመድ መንፈስ ውስጥ ይመሰልኛል። ከእኛው ጉዳት ከማግስት ሰቆቃ ከተስፋ ርቀት ይልቅ።

እና እሳቸው እራሳቸው ፈተና ውስጥ ያሉ ይመሰልኛል። አንድ ሰው ከጎረቤት ጋር ባይስማማ ቦታውን ጥሎ ይሄዳል፤ አገር ባይመችም መሰደድ አለ ከፋም ለማ፤ ትዳር ባይመችም መፍታት አለ በጀም አልበጀም፤ ህሊናን ግን ከዬት ይሸሹታል? ጌዴኦ ላይ አንድ ሰው ብቻ ነው የሞተ ብለው ለዛውም አትበሰበሱት።

/ / አብይ አህመድ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሰጡትን ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫ ይከታተሉ

 

ርህርሃናቸው፤ አዘኝነታቸው ሁሉ ብን ነው ያለው ተነነ ወይንም ተሰደደ። እንደ አገር ልጅነትም እንደ ወገናዊነትም እንደ ነገ አሳቢነትም ሰዋዊነት ለማዬት አልቻልኩም። ምቱ፤ ቃናው ሁሉ ድርቅ የመታው ነው። መልካም ስለተሠሩት ብቻ መቀደሱ ለ አንድ መሪ መለኪያ ሊሆን አይችልም፤ የዜግነት ሲሶ እና እርቦ ስለሌለው …

ስለሆነም የህሊና ግብግብ ወደ ሥነ - ልቦና ቀውስ ካደገ ከባድ ነው የሚሆነው። 
በዚህ ውስጥ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ጠ/ሚር አብይ አህመድን የፈለጓቸው 
ምክንያት ለውስጥ ፍላጎታቸው ማሳክያ ድልድይነት ነው። 

ስለሆነም የጠ/ሚር አብይ አህመድ መንፈስ ጠላፋ የተካሄደው በራሱ በፕሬዚዳንት
 ለማ መገርሳ ነው። ኢትዮጵያን አፍርሶ እንደገና በማደረጀት ሂደት አስቀደምው የሠሩት ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ የአብይን መንፈስ ውርስ ቅርስ አድርጎ እሳቸው ላለሙት ዓላማ ማንበርከክ ይምስለኛል። ደግሞም ተሳክቶላቸዋል። ጠ/ሚር አብይ አህመድም አዲስ ሰብዕናቸውን በመከረኛዋ አላዛር እዬተለማመዱባት ነው። አላዛሯ ኢትዮጵያ ዬዬዘመኑ እንደ ጥንቸል መሞከሪያ ጣቢያ ናትና።  
·       ዶቼ እስኪ ይህን ልብ ብላችሁ አዳምጡት …

Ethiopia - Dr Abiy ከላይ ስትሆኑ በዛ መነጽር ብቻ ታች አትመልከቱ

 

ይህን ርህርህና እናት አንጀት ነው ዶር ለማ መገርሳ ወደ ፈለጉት አቅጣጫ አስነጉደው አላዛሯ ኢትዮጵያ መከራዋን እያዬች ያለችው። በጠ/ሚር አብይ አህመድ ስለ ተጎዱ ኢትዮጵውያን የሚሰጡት መልስ እና የሚያደርጉት ንግግር የተላጠ ነው ፍግፍግ።  

 

ለዚህ ተልዕኮም ጠ/ሚር አብይ አህመድ ፈጣሪ ከሰጣቸው ምርቃት፤ መክሊት እና ረድኤት እጅግ ርቀው እዬሄዱ ነው። ራሱ ስለተፈጸመው ግፍ በደል እና ሰቆቃ ሲገልጹ ምንም እንዳልተፈጠረ ካውያ እንዳልጠፋበት ሰው ሆነው ሳያቸው እጅግ አዘንኩኝ። 

ሰው ፈርሶ የተሠራ ያህል ነው የተሰማኝ። ለነገሩ የፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ዓላማም ኢትዮጵያን አፍርሶ የመሥራት ነው በሳቸው ማንፌስቶ ልክ። ለዚህ ደግሞ ብአዴን አብሮ ይታትራል … ብአዴን አልገባውም ይመስለኛል። ለነገሩ አንድ አፍዝ አደንዝዝ ደግሞ ተሸከም ተብሏለኝ ጃዋርውያኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን …  

·        
አሳክተናል ስለሚሉት ማናቸውም ነገር በተረ ሥልጣኑን በመያዝ፤ ለዛም የሚመጥን ሰው በማቅረብ የሌላውን ልብ በፍቅር ሳይሆን በፌክ በማማለል ወደ የሚፈልጉት አቅጣጫ መውሰድ ነው … ይህ የፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ጥልቅ ስሪት ነው። እሳቸው ፊት ለፊት ሳይወጡ ነበር ትልሙን ለማሳካት ያሰቡት … ሥማቸው እንደተቀደሰ … መወደሱም እንደተኮፈሰ … ስለሳቸው ቀደምት ታሪክ ይህ ቃለ ምልልስ ላይ ምልክቶች ታገኛላችሁ … እግረ መንገዱን እኔ „ለማ ፊቱ ኦሮሞ ይመስላል“ የፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ፍልስፍናም ትንሽ ውልብልቢቱን አግኛቻለሁኝ።

ፍቺው እንደገባኝ ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ መንፈስ ተጠማኝ ነው ዓይነት ይመስላል … ይመስላል ነው ያልኩት … መምህር አቻምዬለህ ታምሩ ያገኘውን መራጃ ሲሰጥ እንዳደመትኩት። በዚህ ውይይት ላይ በጣም አውነታቸዎችን ብንጽጽር ያቀረበ ዝግጅት ነው … በጭልፋ ሳይሆን የነገረ ዕድማታውን መሰረት አስይዞ ማገናዘቢያ እያቀረበ በበሳል ሁኔታ የተብራራ ነው …

የሆነ ሆኖ የፕሬዚዳንት ለማ ራዕይ ችግሩ ይህ የአንድ ዓመት ጉዞ ጠቅላላ ኢትዮጵያን አወላልቆ የመሥራት ትልሙ በጥድፊያ እና ፋታ በማይሰጥ፤ በላይ በላይ በመጫን፤ ትንፋሽ ሰንጎ፤ የማገናዘቢያ ጊዜ ሳይሰጡ በማጫጫን ልባችን ሲያጠፉት የልብ አድረሱን ቀጣይ ተግባር ስለመከወን የታሰበው የረጅም ጊዜ ትልም በዓመቱ ስብራት መግጠሙ ነው … „የፈሩት ይደርሳል፤ የጠሉት ይወርሳል“ ሆኖ ታቦት ይቀርጽላቸው ዘንድ ስንሰብክ የባጀነውን ኩም አድረገው እረጅሙን ትልማቸውን ነገሩን …

ይህ በሰው ሰውኛ ልንተረጉመው የሚገባ አይመሰለኝም። ኢትዮጵያ አምላክ ስላላትም ጭምር ነው፤ ወደ ቀጣዩ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ከመሄዴ በፊት ግን …  

ለመሆኑ … ጠ/ሚር አብይ አህመድ አክቲቢስት? ካድሬ? መሪ? ገዢ? የሚዲያ ሞደራቶር? የፊስ ቡክ ጄኒራል? ወይንስ ዶር ብርሃነመሰቀል አበበ እንደነገሩን የኦነግ ወራሽ? ምን አሳኩ? ምን ቀረ በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ?  ምንችንስ ናቸው? ይቀጥላል … ለዬትኛው ዓላማ ነው የባተሉት? የሚባትሉት? 

ለኦሮማማ ወይንስ ለኢትዮጵያዊነት? 

·       ንድ እንዲያያዝልኝ የምሻው …

ሌላ አንድ ነገር ልከል … ስሜነኞች „ኢጓማ „ስለመሆናችን አዳመጥን …
Temesgen Desalegn: ጥብቅ መረጃ - ገዱ እና ጓዱ... | ADP | ODP | Gedu Andargachew | Dr Abiy Ahmed
Published on Mar 30, 2019

ዛሬ በስል ገብተን ለፍላጎታችን ስኬታማነት መተንፈሻ አግኝተናል ውጥረቱን አስታግሰነዋል ብለው የሚያስቡት የኢትዮ ኤርትራ ፍጥጫም እኮ ስሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመሆንስ አስበውበት ይሆን ጠ/ሚር አብይ አህመድ?

አሁን እኔ ከኤርትራ ከትግራይ ከጎንደር ሦስት ሴቶች የተሰናዳ ሽሮ፤ አብሽ፤ እልበት ጣዕሙን ለይተሽ፤ የምጥኑን አቅም ለክተሽ ዬትኛዋ ሴት ነው ብባል መለዬት አልችልም። ረቂቅ መንፈሳዊ ህብራዊነቱ ተትቶ ማለት ነው።

እና እንዱን ሲነኩ ሌላውም የእኔ ብሎ ማዳመጡ ግድ ይሆናል … አፋርም እኮ የወሎ ነው የነበረው። ይህ ማለት አፋርም ሥነ - ልቦናው የተሳሰረው በስሜነኛው ቅኝት ነው ማለት ነው። ይሄ ድንበር እዬጣሱ መሄድ አያሰነብትም ለማለት … ለክብሩ ጠ/ሚኒስተር አብይ አህመድ … ቢያስብቡት ማለት ነው … ደግሞስ ምን አጠፋ ስሜን አገር አበጅቶ፤ ፊደል ቀርፆ እውቀትን ሸለመ፤    

ከዚህ ጋር ተያይዞ ስለ ኢጎ ከተናሳ የጦር አዛዣቸውም አሁን ለወጥነው የሚሉት መከላከያ ሠራዊት የዛው መንፈስ ቤተኛ ስለመሆናቸውስ? የስሜን ፖለቲካ ዛሬ በበላይነት ተቆጣጥረን አፍረሰን እንሰራዋለን ለሚበላው ሥልጣን ያበቃ ነው። አገር ያበጀ። ስላማበጀቱ ደግሞ የሚጨበጥ፤ የሚዳሰሰ ቅርስና ውርስ ያለው ነው፤

… ራሱ የብአዴን ቁጥር ባይጨመር ብቻውን ኦህዴድ ይህን ሥልጣን ሊያገኝ አይችልም ነበር። አሉታዊ ኢጎ ቢኖርበት ይሳካ ነበርን? ማተበ ቢስነት ገና በጥዋቱ ለራስ ህሊና በሽታን ፈቅዶ መሸለም ነው። በሌላ በኩል ይህን የስሜና ፖለቲካ የመጸዬፍ መከራ ግንቦት 7 የተጸናወተው በሽታ ነው። ለዚህም ነው የያዘው፤ የተጠጋው ሁሉ የሚናደው።
አሁን በአማርኛ ቋንቋ ላይ መታመስም የዚኸው የበታችንት ስሜት ጉዳይ ነው … ለዚህ ሲባል ሙልጭ ያለ የፋሽስት መንገድ መከተል ግድ ሆኗል።

ሊዘህም ሊንክ ማስቀመጥ ስላለብኝ በዚህ ዝግጅት ላይ መንፈሱ ይገኛል … በሽታው ፈውስ አልባ ስለመሆኑ … …

LTV Show | Interview with Professor Ezekiel Gebissa - ፕሮፌሰር እዝቅኤል ጋቢሳ Part One (1
የኢትዮጵያ ቋንቋ መሆን ያለበት ኢትዮጵኛ ነው።ፕሮፌሰር እዝቅኤል ጋቢሳ (በአበበ ገላው)
March 31, 2019
ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙ – አቶ በቀለ ገርባ
March 23, 2019

ወደ ሰብዕዊ መብት ረገጣው ስንሄድ … ቁጥር ላይ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋዜጣዊ መግለጫ 3 ሚሊዮን የሚለው አንድ ሚሊዮን የቀደመ ስለመሆኑ፤ ከዚህ ቀደምም ጽፌ ነበር፤ ቀሪው ሁለት ሚሊዮን ደግሞ እሳቸው ወደ አንድ ሚሊዮን ነው የሚሉት ይህም በኢትዮጵያ የመረጃ ጥንቅር የብቃት ደረጃ ሲታይ አግባብነቱን ተቀብዬ ግን ህፃናትን፤ ድውያን፤ ነፍሰጡር አናቶችን መከራ ሳስበው ግን ከ3 ሚሊዮን በላይ ነው የችግሩ መጠን፤ ስፋት ጉዳይ … እራሱ የ5ቱ የኦሮሞ ድርጅቶች መግለጫ ስንቱ ሥነ - ልቦና ድቀት እንደተጫነው ማረጋጊያ ለመስጠት እንደ ሙሴ እንኳን መድፈር አልቻሉም ክብሩ ሙሴያችን? ክቡር የአሮን በትራችን?  
ክቡር ሆይ ማህሌት ቁመን ስንባጅ ሐሴት እንደነበረ ግድፈትን ስንገልጽ ደግሞ አይክፋዎት። አሁንም ወደ ቀደመው ሰውኛ ተፈጥሮኛ መንፈሰዎት ከተመለሱ ሁልጊዜም ከ አውነት ጎን ለመቆም አይታክተነም፤ የ ኦነግን ዓላማ ለመሸከም ግን አቅም የለንም።

·       ከቶ ይህ ፋሽስታዊ ፈለግ ሳይሆን ይቀር?
የአዲስ አበባ ወጣቶች በኦዴፓ የእስር ማጎሪያዎች - የአይን ምስክር | Ethiopia

ከምስራቅና ምዕራብ ጉጂ ዞን ተፈናቅለው በጌዲኦ ዞን ገደብ ከተማ የተጠለሉ በመንግሥት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገለፁ

#EBCበኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞንና በደቡብ ክልል ጌዲዮ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ

…“ፍርድ ቤቶቹ ገለልተኛ አይደሉም”… የቡራዮ ታሳሪ ወጣቶች ጠበቃ Ethiopia: Ethiopis

ብልት ላይ ሃይላንድ አንጠልጥሎ ቶርች ማድረግ አልቀረም”…Ethiopia: Ethiopis

Ethiopia:ይሄን ጉድ ስሙ እና ፍረዱ የለገጣፎው_መንግስታዊ_ሽብር ሴራ!


ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

የኦነግን ዓላማ ለመሸከም አቅም የለንም።
አቅም ለማዋጣትም አንፈቀድም!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።