የፕሬዚዳንት ለማ ማንፌስቶ ዲል ያለ መከራ ክፍል ሁለት ...


እንኳን ደህና መጣችሁልኝ
ምርመራ።
ክፍል ሁለት።
„እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“
መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
የኦሮማማ ሃዲድ የተዘረጋው በዚህ መልክ አህዱነት ነው። 

·       በቀዳማይ ላዬው እምሻው፤

ምርመራ ሁለትን የኢትዮጵያ እውነተኛው ጠ/ሚር በሆኑት በፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ንግግር ዙሪያ ላይ የሆናል አትኩሮቴ። ትንሽ በትንሽ ጥቂት ነገሮችን ማዬት ግድ ይላል። ሳናበዛ አንድ በ አንድ በማስተዋል ምርመራ ማድረግ ግድ ይላል። 

አማርኛ በመላ ኢትዮጵያ መናገር የሚታገድበት ዘመን ይመጣል አሁን ጠንከረን መትጋት ካልቻልን። ይህን ነው በቅንጅት እዬሠሩበት ያለው ... ለኦነግ መንፈስ ጠላቴ አማርኛ ቋንቋ ነው ብሎ ነው ሳንጃውን የሳለው። የምለውን ጠብቁት ... የቡራዩ የጌዲኦ መከራ ምንጩ ይኸው ነው ... አዲስበባም ነገ ወዮልሽ ነው! መሪሽ ነኝ ብለዋል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ... 

ውዶቼ ስለስሜን ፓርክ ዝም አልሽ ላላችሁኝ ምን ያልተቃጠ ነገር ኑሮ ነውና? ሥነ - ልቦና እራሱ ሰደድ እሳት ተለቆበት የለም ውይ? 5ቱ የኦሮሞ ድርጅቶች እኮ መናህሪያ አልባ ያደረጉን ዕለት ነገሩ ሁሉ አብቅቷል።

በሌላ ባኩል የደን ቃጠሎ… ባሌ ላይም መሰሉ ተፈጽሟል። ገናም ይቀጥላል። ቅርስ እና ውርስ በሚባሉ በላሊበላም፤ በፋሲል ግንብም መሰሉን እጠብቃለሁኝ ያው የመፍረስ ዘመን ስለሆነ… ኢትዮጵያ እራሷ ከባዕቷ እኮ እዬተፈናቀለች ነው …

ኦነጋውያን ለመደገፍ አቅም እናዋጣ ሲባል ነገን አስቦ መሆን ይኖርብናል። ዶር ብርሃነመሰቀል አበበ „የአነግ ወራሽ አብይ ነው“ ሲሉን ከመሬት ተነስተው አልነበረም። ደረጃ በደረጃ በዛ ጉዳይ ላይ በትጋት እዬተሰራበት ስለመሆኑ አስተውለው ነው።

እና አቅም እና መንፈስን ራስን ለማፈረስ ከሆነ ከልካይ የለበትም። እንደ ግርባው ብአዴን ማለት ነው። በዘመነ ህወሃት የሆነው አልበቃ ብሎ አሁን በቀጥታ በአማራ አንደበት ላይ ልዩ ዘመቻ ተክፍቶ ለሽ ብሏል፤

ራሱ ጠ/ሚር አብይ አህመድም ልባቸውን እንደገጠሙለት ነገረውናል ለግርባው ብአዴን። በድርጅት ደረጃ እኔ የኦዴፓ፤ የብአዴንም ሊቀመንበር ነኝ ብለውናል። ያው የግንባሩ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። ይህ ማለት አማራ ድርጅት ተብዬው እውነተኛው ሊቀመንበሩ ዶር አብይ አህመድ መሆናቸው ነው። ቀደም ባለው ጊዜ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ እንደነበሩት ማለት ነው።

/ / አብይ አህመድ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሰጡትን ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫ ይከታተሉ


በሰሞናቱ የፕሬዚዳንት ለማ መገርሰ ማስተባበያ የፌክ ገለጣ ላይ ኢትዮጵያ ስትደገም አዳምጠናል። እሱን ማሰተማር ያለባቸው ለራሳቸው ህሊና እና እመራዋለሁ ለሚሉት ህዝብ ነው … መንፈሱ እንዳይጠጋ ብርቱ ጥንቃቄ ነው የሚያደርጉት በኦሮምኛ ቋንቋ በሚያደርጉት ንግግር … ሌላው ከማንም ጋር ውል አልገባሁም ለሚሉት ደግሞ እሱ ረቂቅ ነው በዬቤቱ ካለው መንፈስ ጋር ውል ፈጽመዋል። እኛ ውላችን ህጋችን ድንጋጌያችን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች | -ሐበሻ
በዚህ ንግግር ውስጥ አንድ ቦታ ኢትዮጵያ የለችም። በዚህኛው ደግሞ በአምርኛ ቋንቋ በተገለጠው ማስተባበያ ኢትዮጵያ አለች … ጨዋታው እንዲህ ነው የሚከወነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ነገም ቢሆን ሊጠራጠረን አይገባምአቶ ለማ መገርሳ /OBN/

 

የኢትዮጵያ ህዝብ ሊጠራጠረን አይገባም ነው የሚሉት ጠ/ሚርወፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ። መጠራጠር አይደለም ፈርተናቸዋል

እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ምን ይሰማሻል በዚህ አብይወለማ ሌጋሲ ወይንም አመራር ብባል ከህወሃት በላይ ፍርሃት ይሰማኛል። ሙያቸው የደህንነት ሰዎች ስለሆኑ የግራቀኙ እጅግ ከባድ ዘመን ይሆናል ብዬ ነው እማስበው። በቀደመው የኢትዮጵያኒዝም ፖፕሊስት ናቸው ብዬ ስለማምን ጎጂ አልነበረም፤ እንዲያውም ወርቃማ ዕደል ሁሉ ብዬ ጽፌያለሁኝ፤ የአሁኑ እኮ  የኦሮምያ ፖፕሊዝም ነው። ይህ ደግሞ እጅግ አሰፈሪ ነው።

ህፃናትን በት/ቤት አሶሳ ላይ ተዝገተው የታቀጠሉት፤ ነፍሰጡር በቁም በሳንጃ የተዘለዘለችበት ሂደት በምለስት ሳስብ እና አሁን ቤተ መንግሥት መንፈሱ ከገባ ወዲህ በዬአዋሳኙ የሚፈጸሙት ጉዳዮች የመከራ ሌሊቶች ናቸው …  

መፈራት ደግሞ ግድ ነው አገዳደሉ ጭካኔው የተለዬ ስለሆነ። የዘር ምንጠራው እና የማክሰል ስልቱ በተጠና ጥብብ እና ስልት የተለዬ ስለሆነ ነው። መረዳዳት እንኳን የማይፈቅድ። የደከመን፤ የራበን መርዳት ወንጀል ነው። ያስከስሳል ያስጠቃልም። ያስገድላልም።  

ኦሮማማ፤ ገዳ፤ ሞጋሳን በዘመናዊ ሁኔታ እያዬን እዬሰማን ስለሆነ ተግባር ላይ እጅግ ልንፈራ ግድ ይለናል ከተፈጥሯዊነት እና ከሰዋዊነት ጋር ከተጣለ ሰብዕና ጋር ተማምኖ ለመቀጠል እጅግ አስጊ ነው። ባሰቡት መልክ በፌኩ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ጋሬ አብሮ መሳፈር ካልተቻለ ቁልጭ ያለ ፈርኦናዊነት ቀጣይ ነው …

·       በቀጣይ።

ወደ ቀጣዩ ሃሳብ ስንሄድ ደግሞ እንዲህ ይሉናል ኦሮማማን ማንፌስቶ ለማሳካት በምን ሁኔታ የተቀናጀ ተግባር እዬተከወነ እንዳለ … መንገዱ እዬተጠረገበት ያለውን ምህንድስና  …  
„የኦሮሞ ጥያቄ አልተመለሰም የሚለውን ሃሳብ በተመለከተ፣ እውነት ነው እኛም የኦሮሞ ጥያቄ ተመልሷል፣ እኛም መልሰነዋል የሚል እምነት የለንም፡፡ እንዲያውም ኦሮሞ ገና ከጅምሩ አንስቶ ሲጮህላቸው፣ መስዋእትነት ሲከፍልባቸው የነበሩ ጥያቄዎችን ገና አልነካንም ብንል ነው ትክክለኛ መልስ ሊሆን የሚችለው፡፡ ሆኖም እኛ እየሄድንበት ያለነው ወይም ልንሄድበት እየጠረግነው ያለነው መንገድ፣ እነዚያን ጥያቄዎች ለመመለስ መልካም መንገድ ጀምረናል፣ የሚያዋጣ ስልትም ይዘናል ብለን እንድናምን ያስችለናል፡፡

·       መንገድ ጀምረናል፤ መንገድ ጠርገናል፤ የሚአዋጣ ስልትንም ይዘናል ያሉን ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ይሄ ይሆን? ነገስ ነገን እራሱ ከነተፈጥሮው ምን ይጠበቀው ይሆን? ብልህነት ሳይሆን ያዬሁት ብልጠትን ነው።

https://www.youtube.com/watch?v=bcRFG-LMcI8

"ስመለስ ወላጆቼን አጣቸዋለሁ ብዬ ስለምፈራ ትምህርት ቤት አልሄድም።በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ያለ ህፃን

ለማ መገርሳ በልዩ ሃይሉ ታግዞ፣ በጌድዮ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው፣ ዘግናኝ ግድያና ማፈናቀል አልጀዚራ አንደዘገበው።

Ethiopia: ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማሳካት ቀን ከሌት እየሰሩ መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በአንደበታቸው አረጋግጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶች በኦዴፓ የእስር ማጎሪያዎች - የአይን ምስክር | Ethiopia

ከምስራቅና ምዕራብ ጉጂ ዞን ተፈናቅለው በጌዲኦ ዞን ገደብ ከተማ የተጠለሉ በመንግሥት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገለፁ

#EBCበኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞንና በደቡብ ክልል ጌዲዮ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ

…“ፍርድ ቤቶቹ ገለልተኛ አይደሉም”… የቡራዮ ታሳሪ ወጣቶች ጠበቃ Ethiopia: Ethiopis

ብልት ላይ ሃይላንድ አንጠልጥሎ ቶርች ማድረግ አልቀረም”…Ethiopia: Ethiopis

Ethiopia:ይሄን ጉድ ስሙ እና ፍረዱ የለገጣፎው_መንግስታዊ_ሽብር ሴራ!

#EBC 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ጐበኙ፡፡

 https://www.youtube.com/watch?v=cHXaU9BLVyk

Ethiopia: የሱሉልታ ነዋሪዎች የድረሱልን ጥሪ ...

https://www.youtube.com/watch?v=b8JfkxjZ_zA

Ethiopia: ቤታቸው ምልክት የተደረገባቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች ለኢትዮታይምስ | Residents of Sululta | Addis Ababa

https://www.youtube.com/watch?v=wjZ0PzEKxec

Ethiopia: አረብ ሀገር ለፍታ ሱሉልታ የሰራችው ቤት ሊፈርስባት | Sululta Houses

 

እንግዲህ ጥቅም ከተባለ „ለኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ይሄ ነው የተሸለመው። ለተሰለፉበት ኦሮማማ ማንፌስቶ ደግሞ ድልም በረከትም ሊሆን ይችላል … ምን አልባት ምርቃትም የሚያሰጥ … ለኢትዮጵያዊነት ግን የከፋ የርግማን ዘመን ነው።፡ላይ ላዩን ሳይሆን በጥልቀት ስናስበው … ይህን ሥሙን የወረሰው ብአዴን ራሱ ሊሰቀጥጠውም ሊያፍርበትም ይገባል።

·       ለቅኖች።

በዚህ ውስጥ ግን አሁን በቡራዩ ተከሰው ፍዳቸውን እዬከፈሉ ያሉት ለጋሞ ወገኖቻችን መንገድ የመሩ፤ ሲቆስሉ ለደገፉ፤ ከቤታቸው ደብቀው ላቆዩ፤ ለሰው ጠል እርምጃ ለ ኦዴፓ አመራሮች ያልተባባሩ ንጹሃን የኦሮሞ ወገኖቻችን ስለመሆናቸው መረጃ ቃለ ምልልስ አድርጎበታል።

ስለዚህም እነዚያ በቡራዩ እንደ ወንጀለኛ ታይተው ከሚሰቃዩት ውስጥ የ አቡነ ጵጥሮስን ሰማዕትነት የሚቀበሉ የ ኦሮሞ ወገኖቻችን እንዳለበት ነው። ስለዚህ አሁን ኢትዮጵያን እዬመራት ያለው መንፈስ የጭካኔ፤ የ አረመኔነት ደዌ የተጸናወተው የ ኦነግ ክንፍ ስለመሆኑ አውቀን በማስተዋል መራመድ ይኖርብናል። ዋና ነፍሰ ገዳዮች አልተያዙም። ዋና ጨካኞች አልታሰሩም።

በዚህ ውስጥ የምናዬው ከሰብዕባዊነት ጋር የቆሙ ንዑዳን መከራ አሁንም እንደቀጠለ ስለመሆኑ ነው። መጪው ጊዜ እጅግ አስፈሪ ነው። እንበራታ … ይህ ሁሉንም የኦሮሞ ተወላጅ በአንድ ዓይን የማዬት ጉዳይ ቅጥ መያዝ አለበት።

በዛ አውሮፕላን አደጋም እነዛን ንጹሃን ሳልስት አስራ ሁለት እያሉ የሚባዝኑ ወገኖቻችን ከልባችን ሆነን እናቅርባቸው። አደራ። እኔ አርሲ ክ/ አገር ጢቾ ስለሰራሁኝ ህዝቡን አውቀዋለሁኝ። ሊሂቃኑ ነው እያመሱት የሚገኙት … ህዝቡ ወተት ነው። ሊሂቃኑ ግን ለሥልጣናቸው ለድርጅታቸው ማንፌስቶ ሲሉ … ነው ይህን በደል የሚፈጽሙት። ይህን ለይቶ አንጠርጥሮ አበጥሮ ማዬት ያስፈልጋል።

ኦዴፓ በኦሮምያ ክልል ስለ ኢትዮጵዊያነት እንዲሰበክ አይፈቅድም። ፈጽሞ። ራሱም አያምንበትም ድርጅቱ እንደ ድርጅት መሪዎችም እንደግለሰብ።

ኢትዮጵያዊነት ቃሉ እንደ መላሹ ለሌላው ነው የሚነገረው አብሶ ለአማራው። ከብት ነው በአሞሌ የሚደለለው የሰው ልጅ ህሊናውን ማሰራት ይኖርበታል …

ኢትዮጵያን ከእውነት ቢቀበሉት ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ „ከኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ ማግስት አንድ ነፍስ ስጋት እንዲፈጠርበት አያስደርጉም ነበር። የሳቸው ጨዋታ የሥነ - ልቦና ነው ….

ከእኛ የሚጠበቀው … አንድ ቦታ ላይ ከእውነት ጋር ታርቆ አቋምን ማስተካካል፤ ህሊናን መግራት ይገባል።

የትኛው መንፈስ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደቆመ ማሰብ ይገባል … የቆመው ከኦነግ ዓላማ ልብ ውስጥ ነው የአብይወለማ ካቢኔ። ለዚህ ደግሞ አቅም ማዋጣት፤ አቅም ማፈሰስ የተጋባ አይመስለኝም። ነገር ግን ለተከፈለው መስዋዕትነት ሆነ ለተገኘው ወላዊ ሁነት እውቅና መስጠት የታሪክ አካል አድርጎ ማዬት ይገባል። ታሪክ በ አንድ ወቅት በግልም በወልም የሚከወን አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ ክስተቶች ዕድሜ ጠገብ ሲሆን ማለት ነው …

·       ውድቀታችን።

ይህን ሁሉ ዘመን የታገለነው ለኦነግ ዓላማ አልነበረም። ቲም ለማ ለዛ አሳልፎ ሰጥቶናል … ኢትዮጵያን ለዛ ለጨካኙ ኦነግ ዓላማ ተላልፋ ተሽጣለች 

… ስለዚህ ከዝለት፤ ትጥቅ ከመፍታት፤ ተስፋ ከመቁረጥ ወጥቶ አንድ አዲስ መንገድ ከዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ሎሌነት ያለጎበደደ ጠንካራ መንፈስ መፍጠር ግድ ይላል … የቀደሙትን የፖለቲካ ሊሂቃን አሽኮኮ ማድረግ አስፈላጊ አይመስለኝም። እነሱንማ ቀበቷቸውን አስፈትተው እንዳሻቸው እያደረጓቸው ነው አነ በቀላውያን፤ ጃዋርውያን፤ አራራስውያን፤ ጃዋርውያን።

ንጹህ መንገድ መፈልግ ያስፈልጋል። ከሴራ ጋር የተፋታ፤ የፊት እና የጎን ሸጎሬ ያላሰናዳ ግን ለኢትዮጵያ የህልውና ማንነት የሚተጋ … ዘመኑ ይህን አጥርተን እንፈለግ ዘንድ ነው ሁሉ ነገር የሆነው። ሁሉም ወደቀ፤ ከወደቀ ጋር አብሮ መውደቅ ሳይሆን ያን ጥሶ ወጥቶ የጠራውን መስመር ፈልጎ፤ አጥንቶ፤ አስቦበት መነሳት ግድ ይላል … ፈጣሪ አላዛሯን ኢትዮጵያ ይርዳ … አሜን!

አሁን ከሆነ በትእዛዝ „ፊንፊኔ“ በል ስለተባሉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ አጋቾቻቸውን ለማስደስት ካለቦታው ሲደግሙ ሲሰልሱ ይስተዋላል። አሁንም ቅድምም ሲሉ እያዳመጥ ነው … የአማራ ሚዲያ ይህን ሲል ሰምተናል ዶር አብባቸው መኮነን በጀርባው ቀልሃ ስለመፍቀዱ ደግሞ ጊዜ ይመለስው።
 
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ ይቀጥላል …

መሸቢያ ጊዜ …    

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።