ስለ ፕሬዘዳንት ለማ መገረሳ ክፍል ሦስት።

እንኳን ደህና መጣችሁልኝ
ምርመራ።
ክፍል ሦስት።
„እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“
መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።

ዛሬ እኛ ብቻ ታግለን ነው የሚባለው!
የጎንደር እናቶች ታገድሎ!
                                            ይሉኝታ ይኑር ይህም ህዝብ ፍዳውን ከፍሏል!

·       ግቢያ  …

ውዶቼ አንድ በአንድ ነጣጥለን ማዬት ይኖርብናል። ለዚህ ለቀጣዩ አንቦ ኬኛ ማገዶ መንፈሳችን እንዳይሆን። "ኢትዮጵያዊ ሱስ ነው" አሁን ሲነግሩን ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ለእኔ እንደ አዳም እና ህይዋንን እንዳሳሰተው ዕጸ በለስ ነው እማዬው። ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ ሱሳቸው ከሆነች ኦሮምያ ከአዲስ አባባ ጥቅም ስለማግኘቷ አጀንዳቸው ሊሆን ባልተገባ ነበር ። ተራ ኮንዲሚኔዬም የጦርነት ቀጣና ባልሆነ ነበር። 

ኢትዮጵያ ሱሳቸው ከሆነ ከላይ እሰከታች በአንድ ብሄር ብቻ መዋቅር ማደረጃትን ባለለሙት ነበር። ዜጋ እንጂ ለሳቸው ነፍሳቸው ብሄራቸው ባልሆነ ነበር። ባንክ፤ አዬር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ፤ ብሮድ ካስት ባለስለጣን የቦርድ ሰብበሳቢ፤ መከለከያ፤ አዬር ሃይል አዛዥ፤ ገቢዎች ሚ/ር ከታች እስከላይ መዋቅር፤ የኢንደስትሪ ፓርክ ሃላፊ፤ ውጭ ጉዳይ ምን የቀረ ነገር ኖረና ...  

ኢትዮጵያዊነት ሱሳቸው ከሆነ ኢትዮጵያን ርዕሰ ከተማ አልባ ለማድረግ ባልሰሩ ነበር። ኢትዮጵያ ሱሳቸው ከሆነች ከህግ አግባብ ውጭ አዲስ ህግ ወጥቶ ከንቲባ ኦሮሞ ተፈልጎ ከሌላ ቦታ መጥቶ አዲስ አባባን ባልተጫናት ነበር።

ኢትዮጵያ በውስጣቸው አልነበረችም ዛሬም የለችም። ዜግነት እኮ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ አይደለም። ጽናት እና እምነትን ይጠይቃል።  ገድለኛዋ አገር በቀጣይ ህይወታቸውም በመታመናቸው ውስጥ ባለው ዕውነት ልክ ትቀጣቸዋለች። ይህን ይጠብቁት። 

·         ምንጭ

https://www.youtube.com/watch?v=ahQ9bPA1sVg&t=40s
የኢትዮጵያ ህዝብ ነገም ቢሆን ሊጠራጠረን አይገባምአቶ ለማ መገርሳ /OBN/
·         የነፃነት ማገዶነት በዬዘመኑ …

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች | -ሐበሻ

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም - ለማ መገርሳ


ይህ የፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ንግግር በአማርኛ ዶር አብርሃም አለሙ እንደተረጎሙት ነው። ለዛሬ ይህችን ብቻ ነጥለን እናያለን …  

„የኦሮሞ ጥያቄ ስንል መመለስና መታየት የሚገባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነዚህም መመለስና መታየት አለባቸው፡፡ ሆኖም ባንድ ጊዜ ተመልሰው የሚያበቁ አይደሉም፡፡ ህብረተሰቡ እስካለ ድረስ፣ በህብረተሰቡም ውስጥ ለውጥ እስካለ ድረስ፣ የህብረተሰቡ ፍላጎትም እየጨመረ እስከመጣ ድረስ፣ ጥያቄ በየትኛውም ጊዜ አያቆምም፤ ሁሌም ይኖራል፡፡ ይሁን እንጂ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ፍቱን የሆኑ ጉዳዮችን በቅደምተከትል እያዩ እየፈቱና እየመለሱ መሄድ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሁሉ ግን መመለስ ከባድ ነው፤ ጊዜ ሊሰጠቸው የሚያስፈልጉ፣ ጊዜ ሊገዛበቸው የሚያስፈልጉ ጥያቄዎች ስላሉ፡፡ ለምሳሌ፦ የኦሮሞ ጥያቄ ዋነኛውና ቀዳሚው ነው ልንለው ባንችልም፣ ባለፉት አራት ወይም አምስት ዓመታት ውስጥ ኦሮሞ በአንድ ድምጽ ሲያለቅስለት፣ ሲጮህለት የነበረው የኦሮሞ ቋንቋ የእስር ቤት ቋንቋ ሆኗል፡፡ የኦሮሞ ቋንቋ የእስር ቤት ቋንቋ ሆኗል ማለት የኦሮሞ ልጆች እስር ቤቶችን ሞልተውታል ማለት ነው፤ እስር ቤቶች ውስጥ ተኮርኩደው አሉ ማለት ነው፡፡ ይሄ ከስፍራ ስፍራ፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ ኦሮሞ ሲጠይቀው የነበረ ትልቅ ጥያቄ ነው፡፡“

እኛም እልል ያልነበት እኩል የታገልንበት ዓላማ መፍትሄ ሲያገኝ ነፍሳችን እርፍ ያለችበት የሐሴት ጊዜ ነበር። ወለሉ አልበቃን ብሎ እንደ አዲስ እንቦሳ የፈነጠዝንበት። መልሶ ጉም እንዲህ ይዳፋባታል ብለን አላሳበነም ነበር አላዛሯ ኢትዮጵያ። ዛሬ የ አንድ ዓመት መልካም ነገር አብሶ እኔ የደከምኩበት ስለነበር መዘከር የሚገባኝ ነበር። ግን ቆስያለሁኝ። ሰው መጀመሪያ ዋስትና ይኑረው። ዜግነታዊ ስሜት ይኑረው። ተስፋ ይኑረው።

የሚገርመው ውጭ አገር በነበረው የታገድሎ ዘመን እኛ እንጂ የኦነግ ባለመንፈሶች ለአንድ ኢትዮጵያዊ መንፈስ አበረው ከጎናችን ቆመው አያውቁም። እንዲያውም የሳውዲ እህቶቻችን እንባ ጊዜ „እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለንም“ ብለው ነበር አውሮፓ ውስጥ የተሰለፉት።

እኛ ግን ሰው በሚለው ተፈጥሯዊ ጸጋችን ደንበር ክልል ሳይገድበን የምንችለውን ሁሉ አድርገናል። ይህ ከሥር የተለጠፈው አጭር ፊልም ለብዙ ቁልፍ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተልኳል።  

Ungerecht (injustice) neue

 

የአዲስ አበባ ወጣቶች በኦዴፓ የእስር ማጎሪያዎች - የአይን ምስክር | Ethiopi
…“ፍርድ ቤቶቹ ገለልተኛ አይደሉም”… የቡራዮ ታሳሪ ወጣቶች ጠበቃ Ethiopia: Ethiopis

ብልት ላይ ሃይላንድ አንጠልጥሎ ቶርች ማድረግ አልቀረም”…Ethiopia: Ethiopis


በዚህ ውስጥ የጭካኔውን ዓይነት ሳስበው ይዘግንነኛል። ለውጭ ሚዲያ አንድም የታሰረ ጋዜጠኛ የለም፤ የፖለቲካ ድርጅት ውክል አካል የለም ነው የሚባለው።

የአዲስ አባባ ወጣቶች እኮ ፖለቲካቸው ኢትዮጵያዊነት ነው። ማንፌስቷቸውም ኢትዮጵያዊነት ነው። ዓላማ እና ግባቸውም ኢትዮጵያዊነት ነው። ይህ በምን ስሌት በምን ሁኔታ እንቅልፍ ይሰጣል …?  

የቀደመው ሲፈታ ሌላ የሚገባበት ከሆነ ከባድ ነው። መታሰሩ ብቻ ሳይሆን ከበረዶ ቤት በስተቀር ሁሉም መከራ እንዳለ ነው ቃለ ምልልሱ የሚነግረው። የሚገርመው መልካም ያደረጉትን ሰብዕዊ ተፈጥሮ ያላቸው የቡራዩ ነዋሪ ኦሮሞዎችም እስር ቤት እንደ ወንጀለኛ ስቃይ ውስጥ እንዳሉ ነው የሚደመጠው።

ወንጀል የፈጸሙትን አሰረናል የሚሉት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ደግ ያደረጉትን ቅኖችን የበታች አመራሮች የተበቀሏቸውን ጭምር እኮ ነው። እንደ ዘገባው ከሆነ። እና ይህም ሌላ ሽወዳ ነው።

የኦዴፓ ባለስልጣኖችን ያልተባበሩ ኦሮሞዎችም አሁን እስር እና እንግልት እዬደረሰባቸው ነው። እነሱስ ወገን አይደሉንም? ከላይ ቀረ ያሉን መቼ ቀረና አዲሶቹ ደግሞ ይሕው በተራ ገብተዋል በጉልበተኞች ይታሻሉ። መታመን በተግባር ይሁን! ሰው ሰው ለመሽተት ከራስ ጋር ታግሎ ራስን ማሸነፍ ይገባል። ከኦነግ ዓላማ በፊት ሰው ነው የተፈጠረው።


ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ ይቀጥላል …

መሸቢያ ጊዜ …

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።