Adaptable ተስማሚ፤ Visibility ተጎብኝነት።
ስለምን ይሆን ዶር አብይ አህመድ መከላከያውን የተፎካካሪ ፓርቲ አካላት እንዲጎበኙት ይደረጋል ያሉት? ከሥርጉተ ሥላሴ 19.06.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ „መባህን አግባ አስበህ፤ ስንዴህን አግባ የተቻለህን ያህል መሥዋዕትህን አብዝተህ አቅርብ።" (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፲፩) · የመነ ሻ ሃሳብ። በትናንትናው ውሎ የፓርላማ ጉባኤ ውሎ የክቡር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ መከላከያን በሚመለከት ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ክፍት ይሆናል ያሉበት መሰረታዊ ምክንያት በግርግር የፖለቲካ ትርምስ እንዲታይ ስለማልሻ እራሱን አስችዬ መግለጽ ፈለግኩኝ። · ሰ ውኛው መሪ! የዶር አብይ አህመድ ሰብዕና ሰውኛ ነው። ሰውኛ መሆን ደግሞ ከሰውኛ መንፈስ ጋር የተዋህደ ነው። ከሰውኛ ፍላጎት ጋር የተስተገባረ ነው። ከሰውኛ ጠርን ጋር ደማዊ፤ ደማማዊም ነው። ጥምረት አይደለም ውህደት ነው። ውህደቱ የፖለቲካ ሊሂቃን የቀደሙት እንደሚሉን በማስመስል የሚለበጥ አይደለም። ሰው ለመሆን የፈቀደ ሰው ሰው ነው። ለሰው ልጅ ትልቅ አክብሮት ያለው። ለሰው ልጅ አለው አክብሮት የሚመነጨው ደግሞ "ቃል" ሰው ስለመሆኑ ስለሚያምንበት ነው። "ቃል" ስለፍቅር የቀደመ ነው። "ቃል" ነው ...