ስለ ሶቆቃው አማራ፤
የቱ ይቅደም ስለ ሶቆቃው አማራ? ክፍል አንድ። ከሥርጉተ © ሥላሴ 28.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) „አሌፍ። ህዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች“ (ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፪) · መነ ሻ። https://www.youtube.com/watch?v=EMCbOlzvr9A አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስለወልቃይት እና ቅማንት ጉዳይ መልስ ሰጡ Part 2 · እፍታ። ዛሬ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ውይይት አዳመጥኩት። የአማራ ቴሌቪዥን ችግሩ ቀንጨብ እያደረገ የሦስት እና የሁለት ደቂቃ ቅርጥምጣሚ መረጃዎችን ከመለጠፍ የሽወዳ ፖለቲካ ወጥቶ ሙሉውን ለቆታል። ስለሆነም ነው ዛሬ ጥዋት ሙሉን ለማድመጥ የፈቀድኩት። ቋረጥራጣውንማ ዞር ብዬም አይቼው አላውቅም። · ሂ ደት። በሁሉም ጉዳይ ነጥብ በነጥብ መሄድ አስፈለጊ አይመስለኝም ግን ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ማንሳት ግን ግድ ይለኛል። በጣም ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር የምስማማበት የፌድራሊዝም የተገነባንበት መንፈሱ ብክል ነው የሚለውን ነው። አዎን የፌድራሊዚም አወቃቀር መንፈሱ ብክልነቱ ሁሉም መሰጥሮ የያዘው አማራውን ከኢትዮጵያ መልክዕምድራዊ ገጸ ምድር በፍጹም ሁኔታ ያገለለ ነበር። ለዚህም ነው ፌድራዚሙ ችግር የለውም የሚለውን ሞጥረው ሲሞግቱ የሚሰሙት። አማራን ዜጋ አይደለህም ብሎ ቆራርጦ፤ ሽንሽኖ ከመንፈስ ሰርዞ የሚያስጠብቅ ማገር ስለሆነ። ይህ እንግዲህ ለ43 ዓመት በጠንካራ ሁኔታ የተሠራበት የሴራ...