ልጥፎች

ዛሬ አብያዊ መንፈስ ከሱባኤ ማግስት በመነኩሲት ባዕት!

ምስል
ትርጉም ገብ ማዕልት። „እግዚአብሄርን መፍራት ውደ ህይወት ይመራል፤ የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፤ ክፉ ነገርም አያገኘውም።“ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፳፫    ከሥርጉተ ©ሥላሴ 26.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ይህ የዶር አብይ አህመድ ፍላጎት የዛሬ አይደለም የቀደመ ነው።  እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ። ትናንትና ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በርከት ላሉ አገር ውስጥ ለሚገኙ ጋዜጠኞች የመጀመሪያውን የጋዜጠኞች እና የጠ/ሚሩን የመጠይቅ እና የመልስ ሂደት ሁላችንም ተከታትለናል።  በጤናቸው ዙሪያ ለተነሳው ጥያቄ ምንም አልደረሰብኝም፤ ታምሜም አላውቅም ሲሉ ቅልብጭ ያለ መልስ ሰጥተዋል።  ያም ቢሆን እንደ እኔ መሰል የቀደመውን አብይ ፍለጋ ለነበርን ሰዎች ብዙም አጥጋቢ አልነበረም።  ይህ ሲባል ደህንነታቸውን መስማት አያስደስትም ማለት ግን አይደለም። የአብይ መንፈስን ባወቅነው ልክ አለመግኘታችን ነበር ጭንቀታችን። በሌላ በኩል ተራ ወሬ ብቻ ተደርጎ መወሰዱም ብዙም ያልተመቸኝ ነበር። ሰዉ ልዩ ፍቅር፤ ልዩ አክብሮት፤ ልዩ ተስፋ ስላለው ነው ጭንቁ መጠበቡ የነበረው። ዕንባ አልቃሽ በገንዘብ የተገዛበትም ታሪክ እኮ እናውቃለን። ከሚዲያ መጥፋት ብቻ ሳይሆን የሚዲያዎች ሂደት እና አቀራረባቸው፤ ምስል ቀረጻው እና ሁኔታው በፍጹም ወደ ውስጥ ሊገባ የሚቸል አልነበረም። ዛሬ ሳይሆን ቀደም ባለው ጊዜም ጭምር በጥልቀት ጉዳያችን ብለን አብያዊ መንፈስን ለምንከታተለው ሰዎች ወሬው ከመወራቱ ቀድሞም ያሉትን ክንዋኔዎች በባለቤትን ስንከታተል መቆዬታችን ለኢትዮጵያ ተስፋ ካለን ቀናዕይነት ነበር።  ልብ አምላክ ዳዊት „የቤትህ ቅናት በላኝ“ እንዳለው ማለት...

የመቀሌ የፖለቲካ ትኩሳት ደግሞ ወደዬት?

ምስል
በዕለ አሸንዳ በትግራይ።   „ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም። “   የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልዕከት ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፲፪ ከሥርጉተ© ሥላሴ 25.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። መቀሌ እንደለመደባት ሞቅ ደመቅ ብላለች። በሁለተኛው ስታዲዮዋ ላይ ደግሞ ሁለተኛውን ባዕሏን እያከበረች ነው። የትግራይ ባልሥልጣናት በሙሉ በተገኙበት በዚሐው ባዕል ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በባህላዊ ቀሚሱ ተውበው ተገኝተዋል።  በዚህ ባዕል ላይ ከትግራይ ደም ያላቸው ተዋናዮችን እና ታዋቂ ሰዎችም አንደተገኙ መረጃው ይጠቁማል። ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤልም አብያዊ ለመሆን በተሸለ አቀራረብ በሚመሯቸው ወገኖች ማህል ሰላምታ በመለዋወጥ እና በማከበር ቀረቤት እንዳላቸው አንድ ያልተለመደ ነገር ሲሳዩ ተመልክቻለሁኝ። ይህም መልካም የሆነው ያልተለመደው ነገር በወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥር የወደቁ ነፍሶችን ከእሥር በባዶ 6 ያሉትን ግፉዕና በማስለቀለቅ እና የወረሩትን መሬት በክብር በመመለስ አብነቱን ወደ ስልጣኔ ቢያሻግሩት ምንኛ ይህ ድርጊታቸው ከልባችን በገባ በነበረ። በዚህ የአሽነድዬ ባዕል ባህላዊ ውዝዋዜውንም ሲያኬዱት ተመልከተናል። ከውስጣቸው ይሁን አይሁን አይታወቅም ብቻ ደስ ብሏቸው ሲወዛወዙ አይቻለሁኝ። በዚህ ዓመት በነበረው የትግራይ ህዝባዊ ኮንፈረንስም ላይ እንዲሁ ልባቸው ጥፍት እሲክል ድርስ ሲጨፍሩ አይቻለሁኝ። ይህ መቼም ሰውኛ ነው። እንደ ሰውኛ ጭፈራው ደግሞ ሌሎችን የሸር ገመዶችን እና የሴራ ድሮችን ተወት ቢያደርጉት መልካም ...