ልጥፎች

ወጣቱ ለራሱ ሲል ለውጡን ይጠብቅ!

ምስል
ለውጡ ለኢትዮጵያ       ወጣቶች የልብ አድርስ ነው። „እጃችሁን ለእግዚአብሄር ስጡ፤ ለዘላለም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቁጣው ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሄርን አምልኩ።“ መጽሐፈ ዜና መዋል ምዕራፍ ፱፰ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ© ሥላሴ Sergute©Selassie   15.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        ጠ ብታ። ውዶቼ እንዴት ናችሁ ያቻላችሁ ፌስ ቡክ ያላችሁ ይህን መልዕክት ከፌስ ቡካችሁ ብትለጥፉልኝ ደስ ይለኛል። ምስጋናዬም ከንጹህ ልቤ እንሆ። ወጣቶች ከብክነት የማውጣት ትውልዳዊ ድርሻ አለብን። የእኛ ይበቃል። ወጣቶች የሚሸሹበት ምክንያት ሙሉ አቅም ስላላቸው ነው። ይህ ለውጥ የሚመራው የአብይ ካቢኔ ደግሞ በወጣቶች አቅም ለመጠቀም ስንዱ ነው። ስለምን? እርካቡን የያያዙት ወጣቶች ስለሆኑ። እነሱን የሚተካ ተከታይ ሃይል መፍጠርም ዋንኛ ዓላማቸው ስለሆነ። ጥቃቱ ደርሶባቸውም አይተውታል። https://www.youtube.com/watch?v=irRwk5vK7A8&t=17s Ethiopia - Dr Abiy ahmed Synergy የ " መደመር " እዉነት ሲገለጥ … ·        የወ ግ ገበታ። ወጣትነት ዕድለኝነት ነው። ወጣትነት ሃያልነት ነው። ወጣትነት አቅማዊነት ነው። ወጣትነት ጉጉታምነት ነው። ወጣትነት ፍጥነትነት ነው። ወጣትነት ግንባር ቀደምትነት ነው። ወጣትነት ምናባዊነትም ነው። ወጣትነት ድፍረትነት ነው። ወጣትነት ችኩልነትም ነው። ወጣትነት ግብታዊነትም ነው።  ወጣትነት ግንፍልተኝነትም ነው። ወ...

ስለምን ወጣቶች ቅንነትን ይፈሩታል?

ምስል
ወጣቶች ቅንነትን መፍራት የለባቸውም። የፃድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል።  አንደበቱም ፍርድ ይናገራል። መዝሙረ ዳዊት ፴፮ ቁጥር፮ ከሥርጉተ© ሥላሴ(Sergute©Selassie) ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።   ·        ስለምን ወጣቶች ቅንነትን ይፈሩታል?   እንዴት ናችሁ የጸሑፌ መደበኛ ታዳማዎች አክባሪዎቼ? ደህና ናችሁ ወይ?   ወጣቶች ስለምን ቅንነትን እንደሚፈሩት አይገባኝም። ምክንያቱ ወጣቶች ተስፋቸውን፤ ራዕያቸውን፤ ትልማቸውን፤ ግባቸውን ማግኘት የሚችሉ ቅን ከሆኑ ብቻ ነው። ምክንያቱም ልዑል እግዚአብሄር / አላህ ከቅኖች መንፈስ ጋር ስለማይለይ አቅም እና ሃይል ይለግሳቸዋል እና።   ብዙ ሰዎች በመማር ውስጥ፤ በዲታነት ውስጥ፤ በውበት ማሪኪነት ልክ ስኬት ይገኛል ብለው ያስባሉ። ቅንነት ከሌላ ላላቸው ሃብት ሁሉ ተጠቃሚ የመሆን አቅም ያንሳቸዋል። ስለምን? ቅንነት በጎደለ ቁጥር ራስን ከተፈጥሮ ስለሚቀንስ። ቅነንት ድርቅ በመታው ቁጥር ራስን ከተፈጥሮ ስለሚያጓድል የውስጥ ሰላም ይራቆታል።   ቅንነት የሌለው ሰው የህሊና ሰላም የለውም። ኑሮው ሁሉ ያደባ እና አሉታዊነትን የተጎናጸፈ ነው የሚሆነው። አሉታ ደግሞ ግራ ነው። ግራ ደግሞ ራስነትን ያሳጣል። ኪሳራ።   ቅንነት ከሁሉ በላይ ተጠቃሚ የሚያደርገው የሰውን አንጎል ነው። የሰው አንጎል ቅንነት ካላው ሃሳብ ለማፍለቅ፤ ለመፍጠር፤ ለመመራመር፤ አርቆ ለማሰብ፤ ምናባዊ የሆኑ ትልሞችን ለመተንበይ ይቻለዋል።   ለቅኖች ነገ ብሩካቸው ነው። ቅኖች ነገሮችን በቅንነት ስለሚዩት ለነርባቸው ሃኪሞች ናቸው። ለጨጓራቸው ዳሳሾች ናቸው...