" ሽመላዊ ትምህርት "
" ሽመላዊ ትምህርት " Yidnekachew Kebede "ሽመላ በመባል የሚታወቁት አዋፋት ወቅትን መሰረት ያደረግ ምቹ መኖሪያ ፍለጋ ከቦታ ቦታ ዝውውር ያደርጋሉ፡፡ በጉዟቸውም ልብ ብለን አስተውለናቸው እንደሆነ የ “V” ፊደልን ቅርጽ ሰርተው ነው የሚበሩት ፡፡ ሳይንስ የደረሰበት እውነታ ሽመላዎች በአንድነት ሲበሩ የሚኖረውን የአየር ግፊት ለብቻቸው ሲበሩ ከሚፈጥርባቸው የአየር ግፊት በእጅጉ ስለሚቀንስ ነው ፡፡ ብቻ ለብቻ ከሚበሩት ይልቅ የ “V” ፊደልን ቅርጽ ሰርተው በአንድነት ሁነው ሲበሩ የመብረር ፍጥነታቸውም በ71% ይጨምራል፡፡ ይህንን በመረዳታቸው ነው ሽመላዎች የ “V” ፊደልን ቅርጽ ሰርተው መብረራቸው፡፡ ሌላው ሊደንቀን የሚገባው ባሕሪያቸው በሆነ ምክንያት (በጉዳትም ሊሆንይችላል) አንድ ሽመላ ተነጥሎ ከዚህ ቅርጽ ከወጣ የተወሰኑት ተነጥለው በመቅረት በግራና በቀኝ በመሆን የሚደርስበትን የአየሩን ግፊት በማገዝ ወደ መንጋው እንዲቀላቀል ያግዙታል እንጂ ጥለውት አይሄዱም፡፡ እገዛቸውም የሚዘልቀው አገግሞ ከመንጋው እስኪቀላቀል ድረስ ወይም ደግሞ ለይቶለት እስኪሞት ድረስ የሚቀይ ነው፡፡ ሽመላዎች የሚያደርጉትን እረዥም ጉዞ ይመራ የነበረው ሽመላ በደከመው ጊዜ የመሪነት ሚናውን ለአንደኛው ያስረክብና ከኋላ በመሆን እረፍት ያደርጋል፡፡ ሽመላዎች በሚጓዙበት ወቅት ቋቅ… ቋቅ... የሚል ድምፅ ያስተጋባሉ፡፡ ይህም በገጠሩ የሀገራችን ክፍል እንደሚደረገው የደቦ ሥራ ሽለላ ጎዞውን ተበረታታው በነቃ መንፈስ እንዲጓዙት ለማድረግ የማነቃቂያ ስራ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ፊት ሆኖ መንጋውን ለሚመራው ግብረገባዊ ትምህርት ተፈጥሮ በራሷ ይንን ይረዱት ዘንድ ለሽመላዎች ጥበብ ሰጣቸዋለች፡፡ እኛም ከእነሱ ተምረን በአንድነት መስራት...