" ሽመላዊ ትምህርት "

 

" ሽመላዊ ትምህርት "
 
"ሽመላ በመባል የሚታወቁት አዋፋት ወቅትን መሰረት ያደረግ ምቹ መኖሪያ ፍለጋ ከቦታ ቦታ ዝውውር ያደርጋሉ፡፡ በጉዟቸውም ልብ ብለን አስተውለናቸው እንደሆነ የ “V” ፊደልን ቅርጽ ሰርተው ነው የሚበሩት ፡፡ ሳይንስ የደረሰበት እውነታ ሽመላዎች በአንድነት ሲበሩ የሚኖረውን የአየር ግፊት ለብቻቸው ሲበሩ ከሚፈጥርባቸው የአየር ግፊት በእጅጉ ስለሚቀንስ ነው ፡፡ ብቻ ለብቻ ከሚበሩት ይልቅ የ “V” ፊደልን ቅርጽ ሰርተው በአንድነት ሁነው ሲበሩ የመብረር ፍጥነታቸውም በ71% ይጨምራል፡፡ ይህንን በመረዳታቸው ነው ሽመላዎች የ “V” ፊደልን ቅርጽ ሰርተው መብረራቸው፡፡
ሌላው ሊደንቀን የሚገባው ባሕሪያቸው በሆነ ምክንያት (በጉዳትም ሊሆንይችላል) አንድ ሽመላ ተነጥሎ ከዚህ ቅርጽ ከወጣ የተወሰኑት ተነጥለው በመቅረት በግራና በቀኝ በመሆን የሚደርስበትን የአየሩን ግፊት በማገዝ ወደ መንጋው እንዲቀላቀል ያግዙታል እንጂ ጥለውት አይሄዱም፡፡ እገዛቸውም የሚዘልቀው አገግሞ ከመንጋው እስኪቀላቀል ድረስ ወይም ደግሞ ለይቶለት እስኪሞት ድረስ የሚቀይ ነው፡፡ ሽመላዎች የሚያደርጉትን እረዥም ጉዞ ይመራ የነበረው ሽመላ በደከመው ጊዜ የመሪነት ሚናውን ለአንደኛው ያስረክብና ከኋላ በመሆን እረፍት ያደርጋል፡፡
ሽመላዎች በሚጓዙበት ወቅት ቋቅ… ቋቅ... የሚል ድምፅ ያስተጋባሉ፡፡ ይህም በገጠሩ የሀገራችን ክፍል እንደሚደረገው የደቦ ሥራ ሽለላ ጎዞውን ተበረታታው በነቃ መንፈስ እንዲጓዙት ለማድረግ የማነቃቂያ ስራ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ፊት ሆኖ መንጋውን ለሚመራው ግብረገባዊ ትምህርት ተፈጥሮ በራሷ ይንን ይረዱት ዘንድ ለሽመላዎች ጥበብ ሰጣቸዋለች፡፡ እኛም ከእነሱ ተምረን በአንድነት መስራት የሚያስገኘውን ጥቅም፣ በጋራ ሲሆኑ የሚፈጠረውን ተጨማሪ ጉልበት ማጤንና አንድነትን ማጠንከር እንዳለብን ያሳስበናል፡፡ አንድነት ኃይል ነው፡፡ በአንድነት በመሆናችን ለየብቻ ከነበረን የበለጠ ተደማሪ ኃይል ማግኘት እንችላለን፡፡
የጋራ መዳረሻን በእምነት ከያዝንና እንደ አንድ ልብ መካሪ ሁነን በአንድነት መስራት ከቻልን በፍጥነት ከአሰብንበት እንደርሳለን፡፡ የላቀ ውጤትም እናስመዘግባለን፡፡
የመሪነት ሚናን ለመጋራት በመካከላችን መከባበርና መተማመን ሊኖር ይገባል፡፡ ሥራዎችንና ችግሮችን ስንጋራ ያለንን ብቃት በአንድነት አስተባብረን ስንጠቀምበት በአጭር ጊዜና በትንሽ ጥረት ብዙ ውጤት ማስመዝገብ አንችላለን፡፡ የመሪነት ቦታ ዕርስት አደለም!
ወቅቱን የጠበቀ ማበረታቻ ስንለዋወጥ እርምጃችን ፈጣን ይሆናል፡፡
--
ልዩነታችንን አድንቀን ተቀብለን ለጋራ ችግራችን በጋራ እንነሳ በተለይም ደግሞ በአስቸጋሪና በፈታኝ ጊዜ አንድነታችንን እንጠብቅ፣ እናስጥብቅ፡፡
ምንጭ፡- #FLIGHT OF SWANS


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።