የጤና ባለሙያወች #የራሳቸው #ጉዳይ ነው በህብረት ያስነሳቸው። ሌላ ገፊ ኃይል ያላቸው አይመስለኝም።
የጤና ባለሙያወች #የራሳቸው #ጉዳይ ነው በህብረት ያስነሳቸው። ሌላ ገፊ ኃይል ያላቸው አይመስለኝም። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" በዘመነ አብይዝም የ፯ ዓመታት የአገዛዝ ሂደት ኢትዮጵያ ውስጥ ያልታዬ የፈተና፤ ያልተሞከረ የቀውስ፤ ያልተመለከትነው የሴራ ድንኳን የለም። 100 ቀናት ሳይሞላ ገና በልጅነት ዕድሜው ከሰኔ 16 ጀመሮ በመላ ኢትዮጵያ ያልታዬ የፈተና ቡፌ የለም። ደቡብ ምን ያህል ህዝብ ነው የተፈናቀለው። የገዴወ፤ የጋሞ ህዝብ ምን ዋጋ ከፈለ። ቡራዩ ለገዳዲ አዲስ አበባ ፦ ብቻ ፈተና ኢትዮጵያን ፈተናት። ቀውሱ በመንግሥትም ታቅዶ፤ መንግሥት ውስጥ ባሉትም ተመስጥሮ እንዲሁም በፊት በምን አቅሙ እል የነበረው #ህወሃት መራሽ ሴራም በሚችለው ሁሉ በቀውስ አምራችነት ላይ ተሳትፎ እንደ ነበር ዛሬ ባለው የህውሃት የትርምስ ማሳቸው ለመገንዘብ ችያለሁኝ። ከዚህ ጋር ተያይዞም የህወሃት ሆነ የኢህዴግ #ተስፈኞችም ተመሳሳይ ትጋት እንደ ነበራቸው ቢዘገይም ምልክቶቹ ዛሬ ይፋ ናቸው። በምን መሥፈርት ህወሃት እንደሚናፍቅ ባይገባኝም። የሆነ ሆኖ በህወሃት እና በብልጽግና #ልግዛህ እና #አልገዛም ጦርነት፤ በብልጽግና እና በአማራ ትጥቅ ፍቱ፤ አንፈታም የነፍጥ ተጋድሎ፤ በኦነግ የጫካው እና በብልጽግና፤ በኦነግ መንፈስ እና በአማራ ህዝብ የደረሰው ሰቆቃ ውስጥ የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያወች #ቤተ - ሳይለንት ማጆሪቲው ውስጥ ነበሩ። እርግጥ መጀመሪያ ላይ ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጋር በነበራቸው የጋራ ቆይታ ጥያቄያቸውን ከሞላ ጎደል ማንሳታቸውን አስታውሳለሁ። ይህም #በራሳቸው #ጉዳይ ላይ ብቻ ነበር። የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያወች በየትኛውም ሁኔታ፤ በማናቸውም ጊዜ የሙያ...