ልጥፎች

ወረተኝነትን ።

  ወረተኝነትን ።   “አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“ መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር ብቻ መጀመር…   --- የጀመሩትን ሳይጨርሱ አዲስ መጀመር መጀመር ብቻ መጀመር ... ወረተኝነትን መዘመር ቋሚ ባህሪን መወርወር ነውር ነው ነውር ማንነትን የሚሰረስር በርብር።    • ወረተኝነት ...   ፀያፍ ባህሪ ነው። አንድ ሰው የጀመረውን ፈፅሞ አዲስ መጀመር ሲገባው ሁልጊዜ ዬጀመረውን ሳይጨርስ እንደገና ደግሞ አዲስ መጀር ጥሩ ያልሆነ ባህሪ ነው።   ልጆች ጓደኛም ሲይዙ ቋሚ በሆነ ባህሪ ከጓደኞቻቸው ጋር በፍቅር ለረጅም ጊዜ መቆዬት አለባቸው። በዬጊዜው ከአዳዲስ ጓደኛ ጋራ የሚጓዙ ከሆነ ብዙም ጥሩ አይደለም።   በተለይ ጥሩ ካልሆኑት ጋደኞች አዳዲስ ባህሪያትን እዬወሰዱ ተፈሮዊ ባህሪያቸው ሊይጎብጥ ይችላል። በሌላ በኩልም በዬጊዜው መጀማመር ጊዜንም ይበላል ተፅእኖም አለው። ወላጆችም ልጆች ከወረት ጋር እንዳይጣበቁ በቅርብ መርዳት ይኖርባቸዋል።    • ነውር ...   እጅግ በማህበርሰቡ ዘንድ የተጠላ የተወገዘ የማይወደድ የተከለከለ ፀባይ ማለት ልቻል ይሆን።   ሰኔ 14 ቀን 2001 ዓ.ም ክላይነአንደልፊንገን ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን። ቅን አስበን፤ ...

ብሩህ ህይወትስ ….

ምስል
  ብሩህ ህይወትስ ….   “አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“     እዮራዊው ዘዴ ነው የክቴ፤ ዝባድ ውዴ። ልበ-ሙሉነት የውስጣዊነት ስስቴ በራስ መተማመን የመስተጋብር ህብስቴ የጀግንነት ቤተ - ስልቴ።   ማስተዋል ቢሆን የጎዳናየ - ድሌ ነው የደሜ - ሞራላዊው የአደራ ------ ውሌ። መታገስ . ም . እኮ ይምጣልኝ ስስቴ ..... ነው ዘንጣፋ ልስልሴ የግርማ ሞገስ ግሤ የክብር ካባ ልብሴ።   ጥሩ ዐይነት ነው ብር አንባሬ የአወንታዊነት ማተብ የክሬ። የቀለሜ --- ቀንድሌ --- ዓውድ ዐመቴ --- ትህትናት ሆይ! አለልኝ፤ መጠሬየ የአንጀቴ ስዋሰው ግጥሜ፤ ማድመጥ … ቢሆን … ክህሎቴ ፈርጤ፤ ከሁሉ የሚበልጥ የልኬ፤ ዬህሊናጆሮ ልዩ ጌጥ።   - የደግነት ዓውራነት … ትጉህነትም አለህኝ አብነት ... ... የትውልዱ ግንባታ መሰረት! የተስፋ ቅመም የህብረት ዀህተ - ብርኃናት።   * አብነት ... ለጥሩ እና ለመልካም ነገር አርያ፡ ምሳሌ መሆን ማለት ነው።    ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን። ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።   ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02/06/2026 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው። ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።

ወረተኝነትን ።

  ወረተኝነትን ።   “አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“   መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር መጀመር ብቻ መጀመር…   --- የጀመሩትን ሳይጨርሱ አዲስ መጀመር መጀመር ብቻ መጀመር ... ወረተኝነትን መዘመር ቋሚ ባህሪን መወርወር ነውር ነው ነውር ማንነትን የሚሰረስር በርብር።    • ወረተኝነት ...   ፀያፍ ባህሪ ነው። አንድ ሰው የጀመረውን ፈፅሞ አዲስ መጀመር ሲገባው ሁልጊዜ ዬጀመረውን ሳይጨርስ እንደገና ደግሞ አዲስ መጀር ጥሩ ያልሆነ ባህሪ ነው።   ልጆች ጓደኛም ሲይዙ ቋሚ በሆነ ባህሪ ከጓደኞቻቸው ጋር በፍቅር ለረጅም ጊዜ መቆዬት አለባቸው። በዬጊዜው ከአዳዲስ ጓደኛ ጋራ የሚጓዙ ከሆነ ብዙም ጥሩ አይደለም።   በተለይ ጥሩ ካልሆኑት ጋደኞች አዳዲስ ባህሪያትን እዬወሰዱ ተፈሮዊ ባህሪያቸው ሊይጎብጥ ይችላል። በሌላ በኩልም በዬጊዜው መጀማመር ጊዜንም ይበላል ተፅእኖም አለው። ወላጆችም ልጆች ከወረት ጋር እንዳይጣበቁ በቅርብ መርዳት ይኖርባቸዋል።    • ነውር ...   እጅግ በማህበርሰቡ ዘንድ የተጠላ የተወገዘ የማይወደድ የተከለከለ ፀባይ ማለት ልቻል ይሆን።   ሰኔ 14 ቀን 2001 ዓ.ም ክላይነአንደልፊንገን ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን። ቅን...

„ላሜ ... ቦራ“

ምስል
  „ላሜ ... ቦራ“         “አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“   „ላሜ ቦራ“ ...   የ ~~ አባቴን ነገር አደራ የ ~~ እናቴን ነገር አደራ የ ~~ እህቴን ነገር አደራ የ ~~ ወንድሜን ነገር አደራ!   „ላሜ ቦራ“ . .. የ ~~ እቴቴን ነገር አደራ የ ~~ አባዬን ነገር አደራ የ ~~ እታታን ነገር አደራ የ ~~ ወለላን ነገር አደራ!   „ላሜ ቦራ“ ...   የ ~~ ጋሽዬን ነገር አደራ የ ~~ መኩሬዬን ነገር አደራ የ ~~ ጥላዬን ነገር አደራ የ ~~ ክንድዬን ነገር አደራ!   „ላሜ ቦራ“ ...   የ ~~ እቴ አንጀቴን ነገር አደራ የ ~~ እታለምን ነገር አደራ የ ~~ እትዬን ነገር አደራ የ ~~ እቴዋዬን ነገር አደራ!   „ላሜ ቦራ“ ...   የ ~~ ትልቋን ማሚ ነገር አደራ! የ ~~ ታሪኬን ነገር አደራ! የ ~~ ባንዴራዬን ነገር አደራ! የ~~~~~~ የ አፈሬን ነገር አደራ   „ላሜ ቦራ“ ~~~~   እንዳትረሽ አደራ አደራ! ተቀባይ ሁኝ አደራ! አደራ! አውጭም ሆኝ አደራ!   • „ላሜ ቦራ“ ...    ላሜ ቦራ በልጅነቴ አንድ መጽሐፍ ውስጥ ያገኛሁት ታሪክ ነው። ታሪኩ ... አንዲት ወላጅ ልጆቿን ትታ እንድትሄድ ሞት ያስገድዳታል። በዚያ ወቅት ጭንቀት በያዛት ጊዜ ላሜ ቦራ የምተባለውን ላሟን ትጠራ...

የዕውቀት ሀይቅ ጥልቅ።

ምስል
    “አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“   የዕውቀት ሀይቅ ጥልቅ።   ምንም አያሳፍራም መጠየቅ? ያልገባኝን ብጠይቅ ... ዕውቀት እንደ ሆነ አያልቅ። ዕውቀት ምንጊዜም ነው--- ብርቅ ጣፈጭ መረቅ የሚያደምቅ። የዕውቀት ሀብል ወርቅ ሁልጊዜ የሚያፈልቅ። ድንቁርናን ያደቀቀ ስንፍናን ያማቀቀ ጥብብን ያጠለቀ። ፍጹም ደማቅ! ነው ትልቅ! የሚያልቅ ማይጠገብ ድንቅ የዕውቀት ሀይቅ። ነው ጥልቅ! ዓለምን የሚያደምቅ ቀለማም የሚያበራ ፍልቅ፣ የማያልቅ! * ማላቅ … ትልቅ ፣ ታዋቂ የሚያደርግ። የሚያስከብር: * ዕወቀት ... ከትምህርት የሚገኝ፣ የሰለጠነ አእምሮ ውጤት ነው። ሌባ የማይዘርፈው የህሊና ሀብትም ነው። በሁሉም የሙያ ዘርፎች መሰረቱ ጥልቅ ሰፊ ነው። ይህ በቀለም ትምህርት ወይንም ሃይማኖት ገብ በሆነ ሁኔታ የሚገኝ የዕውቀት ዘርፍን ይተረጉማል። ሊቃውንት የሚባሉ መደቦችንም ይፈጥራል። ከዚህ ውጪ ግን በፈጣሪ ጸጋ ከምንም የእውቀት ዘርፍ ጋር ሳይገናኝ እስከ ዊዝደም የሚያደርስ የዕውቀት ዐይነት ይኖራል፨ ይህ ሊህቅነት ይባላል። ኢትዮጵያን ያበጃት ይህ የማይመረመር የፈጣሪ ሥጦታ ልቅና ነው። ዘመን አመጣሹ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይህን ዕውቅና አይሰጠውም። ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን። ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02/02/2026 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው። ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።

ኦ፧ ሻሸመኔ! እግዚአብሄር ይደነግጣል፤ ገደሉ ተደፈረ ። ለመሰናክላዊ አዲስ ገረጭራጫ ዘመን ይለፍ ተሰጠው። ኑ! አ...

ምስል

#Timing.

ምስል
  #Timing . መረጃው ዘገዬ፤ የአብይዝም መንገድ ……… ምን ልበለው???   ********     "Timing refers to the #strategic selection of the #exact #moment for an #action to #achieve the #best #result or the or the #regulation of when event occur."       https://www.youtube.com/watch?v=gWLfcwf1dS0   “የቀይ ባሕር ጉዳይ አይደለም ችግር የፈጠረው”   • ዛሬ የኤርትራ መንግሥት መልስ ስለሰጠ አያይዠዋለሁኝ። ለዳኝነትም ለታሪክም መንገዱ ይህ ስለሆነ። ሁለቱም የሚመሩት ህዝብ አለ። ህብራዊነት ውህድ ማንነትም አለ። ከስሜት የጸዳ ጠንቃቃ ተግባር መፈጸም ይገባል። ኃላፊነት የሁሉ ኃላፊነት ነውና። ****   እስከዛሬ ስለምን #አምቀው ፤ #ተጭነውም አቆዩት ይህንን ሃቅ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጥያቄ ነው። በወቅቱ ተናግረውት ቢሆን ኖሮ፤ ብዙ መካረሮችን #ሊያረግብ ይችል ነበር። በተለይ መንግሥት እና ህዝብን #የሚያቃቅር ወሳኝ ጉዳይ ብዙ ነገር ስለሚያሳጣም። የሆነ ሆኖ #timing አጤ ጉግል እንዲህ ይተረጉመዋል።   "Timing refers to the #strategic selection of the #exact #moment for an #action to #achieve the #best #result or the or the #regulation of when event occur."    ጊዜን በጊዜው በሰጠው ጊዜ ማናገር ይገባል። ለቀኑ ቀን ሲሰጠው ለቀኑ ቀኑ እራሱ መፍትሄ ያመነጫል የሚል የእኔ ፍልስፍና አለኝ። ቀን ...