ብሩህ ህይወትስ ….

 

ብሩህ ህይወትስ ….
 
“አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“
 
 May be an image of one or more people, braids and people smiling
እዮራዊው ዘዴ
ነው የክቴ፤ ዝባድ ውዴ።
ልበ-ሙሉነት የውስጣዊነት ስስቴ
በራስ መተማመን የመስተጋብር ህብስቴ
የጀግንነት ቤተ - ስልቴ።
 
ማስተዋል ቢሆን የጎዳናየ - ድሌ
ነው የደሜ - ሞራላዊው የአደራ ------ ውሌ።
መታገስ . ም . እኮ ይምጣልኝ ስስቴ
..... ነው ዘንጣፋ ልስልሴ
የግርማ ሞገስ ግሤ
የክብር ካባ ልብሴ።
 
ጥሩ ዐይነት ነው ብር አንባሬ
የአወንታዊነት ማተብ የክሬ።
የቀለሜ --- ቀንድሌ
--- ዓውድ ዐመቴ ---
ትህትናት ሆይ! አለልኝ፤ መጠሬየ
የአንጀቴ ስዋሰው ግጥሜ፤
ማድመጥ … ቢሆን … ክህሎቴ
ፈርጤ፤
ከሁሉ የሚበልጥ የልኬ፤
ዬህሊናጆሮ ልዩ ጌጥ።
 
- የደግነት ዓውራነት …
ትጉህነትም አለህኝ አብነት ...
... የትውልዱ ግንባታ መሰረት!
የተስፋ ቅመም የህብረት
ዀህተ - ብርኃናት።
 
* አብነት ... ለጥሩ እና ለመልካም ነገር አርያ፡ ምሳሌ መሆን ማለት ነው። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/06/2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።