ዶቅማ ናልኝ የእማማ …
ዶቅማ ናልኝ የእማማ …
“አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“
***** ቅጠሉ ለሻይ ቅጠል፤ ፍሬው ለቀለም የሚጠቅም ይመስለኛል።
መልከ ... ቀና
ወይንጠጅማ የእኔ ገናና
የልጅነት ትዝታ ፋና።
ቅርጸ¬ ~~~ የፅንሰት ሚስጢረ - ጎልማማ...
እንቁላልማ።
ሞላላ
የሚበላ።
ዶቅማ...
… ገብያ ለገብያ ሲሄድ
ወዳጁ ብዙ መንገዱ ገድ።
አቤት ሲጣፍጥ ጣዕሙ
ከሩቅ ሲጣራ ጠረኑ
ይላል ኑ! ኑ~ ኑ~
ዶቅማ ~~~~~~
ጣፋጭ ዞማ።
ዶቅማ ...
በወለላይቱ ጎንደር አንድ የፍራፍሬ ዓይነት ነው። አንጀት የሚያለሰልስ ይመስለኛል። ቀለሙ ጥቁርማ የወይን ጠጅ ሆኖ፣ ዱር በቀል ነው፣ ነገር ግን ገብያ ላይ ይውላል - ይሸጣልም፣ ዶቅማ አንድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የፍራ ፍሬ ዓይነት ነው።
ልክ እንደ ብርቱካን ተወዳጅም ፍሬ ነው። አብዛኛው የገጠሩ ነዋሪ የለመደው እና የሚመገበው ነው። በተጨማሪም በአመዛኙ ልጆች በፍቅር የሚበሉት ተወዳጅ ፍሬ ነው። አሁን አሁን ሳስበው ለጸጉር ቀለምም ሊሆን እንደሚችል አስባለሁኝ። ከኪሳችን ወይም ከደብተር ፖርሳችን ውስጥ እያለ ከፈረጠ ቀለሙ ቶሎ አይለቅም።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/06/2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ