„ላሜ ... ቦራ“

 

„ላሜ ... ቦራ“
 
 May be an image of child and text
 
 
“አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“
 
„ላሜ ቦራ“ ...
 
የ ~~ አባቴን ነገር አደራ
የ ~~ እናቴን ነገር አደራ
የ ~~ እህቴን ነገር አደራ
የ ~~ ወንድሜን ነገር አደራ!
 
„ላሜ ቦራ“ .
..
የ ~~ እቴቴን ነገር አደራ
የ ~~ አባዬን ነገር አደራ
የ ~~ እታታን ነገር አደራ
የ ~~ ወለላን ነገር አደራ!
 
„ላሜ ቦራ“ ...
 
የ ~~ ጋሽዬን ነገር አደራ
የ ~~ መኩሬዬን ነገር አደራ
የ ~~ ጥላዬን ነገር አደራ
የ ~~ ክንድዬን ነገር አደራ!
 
„ላሜ ቦራ“ ...
 
የ ~~ እቴ አንጀቴን ነገር አደራ
የ ~~ እታለምን ነገር አደራ
የ ~~ እትዬን ነገር አደራ
የ ~~ እቴዋዬን ነገር አደራ!
 
„ላሜ ቦራ“ ...
 
የ ~~ ትልቋን ማሚ ነገር አደራ!
የ ~~ ታሪኬን ነገር አደራ!
የ ~~ ባንዴራዬን ነገር አደራ!
የ~~~~~~ የ አፈሬን ነገር አደራ
 
„ላሜ ቦራ“ ~~~~
 
እንዳትረሽ አደራ
አደራ! ተቀባይ ሁኝ አደራ!
አደራ! አውጭም ሆኝ አደራ!
 
• „ላሜ ቦራ“ ... 
 
ላሜ ቦራ በልጅነቴ አንድ መጽሐፍ ውስጥ ያገኛሁት ታሪክ
ነው። ታሪኩ ... አንዲት ወላጅ ልጆቿን ትታ እንድትሄድ
ሞት ያስገድዳታል። በዚያ ወቅት ጭንቀት በያዛት ጊዜ
ላሜ ቦራ የምተባለውን ላሟን ትጠራ እና ልጆቿን አደራ
ለላሜ ቦራ ትሰጣታለች።
 
... ከዛ የልጆች እናት ትሞታለች። „ላሜ ቦራም“ ልጆችን
ወተቷን እያጠባች አሰደገቻቸው። „ላሜ ቦራ“ አደራዋን
የተወጣች የደግ ላም ስም ነው። የቀደምት ጸሐፍት
ትውፊት ለማስቀጠል ታስቦ የተሰራ ነው።
 
• ሌላው ዛሬ ዛሬ እዬከሰመ ያለው ግን ልዩ የነበረው …
በባህላችን ታናሾች ታላለቆችን ሲጠሩ በአክበሮት የፍቅር
ቅጥያ ስም አውጥተው ነው። ስለሆነም ... ሴቶችን ....
ወለላ፣ እታለም፣ አሽኮይ፥ ወተተይ፤ አባዬ፣ እትዬ በማለት…
• ወንዶችን ... ደግሞ ... ጋሽዬ፣ መኩሪዬ፣ ጥላዬ፣ እያያ ብለው አቆላምጠው ይጠሯቸዋል
እናንተስ ልጆች ማን ብላችሁ ነው ታላላቆቻችሁን የምትጠሩት።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/06/2026
 
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።