ሾላ።
ሾላ።
“አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“




• እዚህ ሲዊዝ ሾላ አንድ የፍሬ ዐይነት ነው። እንደ እኛ የጫጫ አይደለም። የደላው ነው። ርጥቡም ደረቁም ይሸጣል። ጣፍጭነቱ ከሥኩር በላይ ነው። ብዙ የጤና ጥቅም እንዳለውም ይነገርለታል።
አዬ! ሾላ
በላ
ተበላ!
ወፍን አታብላ
ከእኔ ጋር
ዋላ!
በላ ተበላ
ፍቅርዬ - ሾላ
ፍሬህን ሳትሳሳ
አብላ~~
ፍቅሬም ልክ የለው በጣም
ከነፍሬህ ስገምጥህ ልዩ ጣም።
ሾላ ተራ በርሬ
አንተንም አባርሬ
ስመለስ ከደብሬ
ሞላ ጎተራዬ
ኮረጆዬ።
አንትን አግኝቼ ምንስ ሆኜ …
እንደምታጠግበኝ ተማምኜ …
ሾላ ፍሬ የትዝታ ልዩ ቀለበት
ፍቅር አመጣ የልጅነት ----
የዛች ልዕልት እመቤት ---
የእናት ሀገር ኢትዮጵያ ህይወት ---
የክብርት መሰረት ---
ናፍቆቱ አለው ምህረት ---
የነፍስ ድህነት።
ሾላም ...
ሜዳ በቀል ሲሆን የገጠሩም ሆነ የከተማው ነዋሪ
የሚያውቀው በልጅነት ወቅት እየተለቀመ የሚበላ
ፍሬ ነው።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/06/2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ