#መፍቻ ።

 

 
“አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“
 
#ምዕራፍ ፲፰።
 
 
 
ዛሬን ለእኔ ሰጠሁት። ሚሞሪን እያሞቀ ከሚገኘው ለህትም ከበቃው ሦስተኛው የዓዋቂወች የግጥም መድበሌ ላይ የተወሰደ ነበረ። በደራሽ ጉዳዮች፤ በሰብአዊነት ጉዳዮች፤ በኢትዮጵያ ዕናቶች አመክንዮ ጉዳዮች ላይ አበክሬ ስለምሰራ እኔን ስቶር ውስጥ ወይንም ሚሞሪው ውስጥ አስቀምጬ በፌስቡክ ለ፮ ዓመታት፤ በሚዲያ ከ፳ ዓመታት በላይ፤ በፖለቲካ ከጋሜዬ ጀምሮ ተኖረበት። ለእኔ ቀን ሰጥቼው አላውቅም።
ይህ ሚዲያ የእኔን እኔም ላስተዋውቀው ፈለግሁኝ። ስለሆነም ዛሬን አጠገብኩት። ጹሁፎቹም ሆኑ ግጥሞቹ ከ፲፭ ዓመታት በላይ የቆዩ ናቸው። ሳድስ ላይ ስለምገድፍ እሱን እና አንዳንድ ጉዳዮችን ለማጠናከር ሞክሬያለሁኝ። እርዕሶች ጭብጡ አልተቀየረም። ማስተካከያው ፩% እንኳን አይሆንም።
 
መክሊት መጸሐፌ ለውዷ እናቴ፤ ለበሞቴ ልዕልቴ፤ ለእሽታ ንግሥቴ ለእብዬ ሆዴ የተሰጠ ነው። ስለሆነም በባህል፤ በትውልድ፤ በትውፊት በማህበራዊ ኑሮ፤ በዕውነት ላይ ያተኮረ ነው። ፖለቲካ የለበትም።
 
#መፍቻ የመክሊት መጸሐፌ ማሳረጊያ ነው። ዛሬ ስክሪብቱ ላይ ሳነበው ገረመኝ። ከፊደል እርማት በስተቀር ቅንጣት አልተጨመረበትም። እንሆ መፍቻን ………
 
ግን የእኔ የቅንነት ውቦች ብሩሆቼም እንዴት አላችሁልኝ። ሁልጊዜም፤ ምንጊዜም ቅንነታችሁ #ቁሞ ያስተምረኛል። ዘለግ ስላለው ትዕግስታችሁ በትሁት አክብሮት አመሰግናችኋለሁኝ። 
 
1) የነገ የፍላጎታችን #መፍቻ ምንድ ነው?
2) ወይንስ #ማን ነው?
3) ነገን ስናስብ ዛሬ ለነገ ምን እንዲያቆዬው? --- ምን #እንዲያሰናዳለት አዘጋጅተነዋል?
3) ነገ ለራሱ ብቻውን ዕጣ #ነፍሱን መቆም ይችላል ወይ?
4) ነገን "ነገ" እንዲያገኜው በምን #ሐረግ ተያይዟል?
 
ብቻ በዚህ ዙሪያ ብዙ መሰረታዊ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻል ይመስለኛል። መፍቻ የተዛጋ በር መክፈቻ ቁልፍ ነው። ወይንም በጥንቃቄ የምናስቀምጠውን እቃ እንዳይበላሽ ወይንም ሰው እንዳይወስድብን ልንቆልፈው እንችላለን። ስንፈልገው ግን መፍቻ ያስፈልገናል።
መፍቻ መፍትሄ ነው። የፍላጎት። አንድ ሰው ከአላአበደ በቀር ነገን ማዬት ይፈልጋል። ነገን ለማዬት ደግሞ መሰረቱ የነገ ተራካቢ #ልጆች መሆናቸውን መቀበል ግድ ይላል። የምነሳሳላት ሐገራችን ኢትዮጵያ፤ ከነክብሯ ለዘላለም እንድትኖር ነገን አብዝተን እንፈልጋዋለን። ይህ እንዲሆን ደግሞ መሰረቱ #ዛሬን በአግባቡ ማደረጀት ያሰፈልጋል።
 
የዛሬ በአግባቡ መሰናዳት የነገን #እርግጠኝነት ያውጃል። ስለዚህም ለነገ - ነገ ሳይሆን ዛሬን መቅደም ያሰፈልጋል። ዛሬ ካለፈን ነገ የለም። ነገ ከሌለ ደግሞ እኛ የለነም። እኛ ከሌለን እናታችንም አትኖርም። 
 
ይህ ደግሞ መረገመት ወይንም እርግማን ነው። ከዚህ እንድን ዘንድ ዛሬ አዎን! ዛሬ በርትተን ልንሰራበት፤ ልንተጋበት የሚገባው ጉዳይ በነገ ፍሬዎች፤ በዛሬ እንቡጦች ላይ የምንከውናቸው በጎ፤ ሩሁሩህ፤ #ርትሃዊ ተግባራት ወሳኝ ይሆናሉ።
 
መሰረቱ ደግሞ መልካም ጋብቻ ሲሆን፤ ጋብቻን ስናስብ ከኛ አብራክ እና ማህጸን ስለሚፈጠሩ ልጆች አስቀድምን አዎን! አስቀድምን መንፈሳችን ማዘጋጀት አለብን። አቅሙ ከሌለን ጋብቻውን ሳይሆን መውለዱን በአተዕቅቦ ማደረጉ መልካም ነው።
 
ለእኔ የአንድ ጋብቻ አብነት መለኪያ ንብረት ወይንም ዝና ሳይሆን፤ ከዛ ጋብቻ የሚመረተው ምርት ምርጥ ዘርነት ይመሰለኛል። በመልካም ጋብቻ ውስጥ ደግሞ ልጆችን በአግባቡ ቀርፆ፤ ኮትኩቶ፤ ተገቢውን አትኩሮት ሰጥቶ ማሳደግ ትውልዳዊ ድርሻን የመወጣትን ብቃት ይለካልናል። 
 
ስለሆነም ልጆች ከማህበረሱ ከሚወርሱት መልካም ነገሮች በተጨማሪ ከባህላቸው፣ ከወጋቸው፣ ከልማዳቻው፣ ከታሪካቸው፣ ከማንነታቸው፣ #ከብሄራዊ ስሜቶችቻቸው ጋር በቅጡ ተዋህደው መንፈሳቸውም፤ አካላቸው #እኩል ያድግ ዘንድ መጠነ ሰፊ ጥረት መደረግ አለበት።
 
ጥረቱ መጀመር ያለበት ከቤተሰብ ነው። ከመሰረት የተጀመረ፤ ነገ ከስሩ በሥርዓት የተገነባ ቁምነገር ማንም፤ ምንም ነገር ከቶውንም ሊያበላሸው፣ አረም ሊያበቅልበት አይችልም። አንድ አትክልት ገና ከጅምሩ እዬተገራ ከአደገ፤ የምርጥ ዘር ባለቤት መሆኑ አይቀሬ ነው። #ዋስትናችን ግን ተግባራችን ነው።
 
ስለሆነም ትውልዳዊ የቤት ሥራችን አህዱ ማለት ያለብን ከራሳችን፣ ከውስጣችን መሆን ይኖርበታል። ዓለም አድጓል። የማደጉ መሰረትም ነገን በተገባው ማቀዱ፣ ማደራጀቱ እና መምራቱ ነው።
 
የዛሬ የዓለም ዓይን መሠረቱ የተገነባው ከልጆች ላይ ነው። አበባ ሁሉም ያዬዋል። ሁለምም ይወደዋል። የደስታ ምንጭ፣ የመልካም ብሥራት ቁንጮ፣ የብሩህ ራዕይ #ቀንድ በመሆኑ። 
 
አበባ ፍቅር ነው። አበባ የሠራ አካለት ትንፋሽ ነው። አበባ መንፈስን አዳሽ ነው። አበባ ውብ የሆነ የመልካም ምኞት መግለጫ ነው። አዎን! ልጆችም የዓለም አበባዎች ናቸው። አበባነተቸው ለሰሞነት ሳይሆን ቋሚ አምድ ነው።
 
ለዛሬም፣ ለነገም፣ ለነገ ወዲያም፣ ለዚያ ወዲያም፣ አበባ አብቦ ደስታ ሆኖ ደስታ ፈጥሮ ነገን በሐሤት ሞሽሮ በተግባር ድሮ ኩሎ፣ #አደራ ዘውድ ይደፋ ዘንድ ሁሉም አበባን በመንከባከብ ተግባር ላይ በተጋት ይሰማራ …. ዛሬም ለነገ ድርጊትን ይቀለብ ….
 
የፈጠረን አምላክ እዬሱስ ክርስቶስ ልጆቻችን ባረኮ ይስጠን፣ #ይቀድስ፣ ይጠብቅ አሜን።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/06/2026
 
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።