አባ ወኔ ባንባ …

 

ባንባ …
 
“አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“
 
 
 
• ባልዘገይ ኑሮ ለጥር ጎንደር የሄዱ ቅን ወገኖቼ ሊዩት ይችሉ ነበር። ፋሲደስ ጥምቀተባህሩ ግቢ ይገኛል። የጎንደር ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት እንደ ቅርስ እና ውርስ አይቶ ጥንቃቄ ያደርግለት ዘንድ በጥትና አሳስባለሁኝ። 
 
አሁን አሁን ሳስበው የዓጤወቹ ቤተኛ እንደነበር አስባለሁ። በንፋስ ጊዜ ዳንሱን ፯ኛ ርግብ በር መጸሐፌ ላይ ርዕስ ሰጥቼ ከድምጽ መግራት ጋር ቀልል ባለ ግራፊክ ለማስረዳት ሞክሬያለሁኝ። ጠረኑ ፍጹም ልዩ ነው። ከፍሬው በተጨማሪ የጎንደር ዩንበርስቲወች ምርምር ቢያደርጉበት ምርጫየ ነው።
 
• የባንባ ፍሬ ቅጠሉ ሰፋፊ ነው። ቀጥታ ብርቱካንማ አይደለም ተቀራራቢ ነው። አመቱን ሙሉ አረንጓዴ ነው። ሲበስል ሙክክ ያለ ነው። በራሱ ጊዜ መሬት ላይ ይወድቃል። ገብያ ላይ አይቼው አላውቅም። 
 
የስሜን እና በጌምድርን አብዛኞን የገበሬ መንደሮችን ቆላ፣ ደጋ ወይና ደጋውን በአካል አውቃቸዋለሁኝ። ባንባን ግን አይቼ አላውቅም፤ ወይራ ፤ ሾላ ፤ አጋም ቀጋ፤ ሎሚ፤ በርቶ ሎሚ፤ ኮክ በጫካው ሁሉ በነፃ ይገኛል።
 
• አባ ወኔ ባንባ … 
 
ጥላ ከለላ የአንባ
ከእርጋ ጋር የተግባባ
ደፋር ነው የማይባባ ስኩን
የማያባባም ደጀን
ብርቱካናማ ዳማ - ባንባ
የዓጤው የትውፊት ዘገባ
ና! እንወያይ እንግባባ።
ፈልጌህ ነበር ላወርድህ
--- ግን አልደረስኩብህም …
ግን ለምን ላይላዩን አሰኜህ?
እንደ ልቤ እንዳልሆንልህ …
ስለምን ይሆን መራቕህ`?
በል ተሎ ውረድ
ጉድ ሳይወርድ።
ተሎ! - ድረስ
እንድትጎርስ።
ባንባ ኮረጆዬን በል ሙላ!
ተስፋዬ እንዲፈካ
የዓጤው የትውፊት ዘገባ
ማንነቴ እንዲጎላ
አጃዬ ቲፍ ብሎ እንዲሞላ
በል ሁንልኝ የእኔ ገላ።
 
ባንባ ...
 
በከተማም ይገኛል መልኩ ወደ ብርቱካንማ ያደላል ...
እንደ በሰለ ማንጎ ዓይነት ሲሆን ትልቅ ዛፍ ላይ ነው
የሚገኘው የዛፉ አበቃቀል ደግሞ ዋርካ ይመስላል። ሲበስል
ሆድም ያሞላል። ይጣፍጣልም።
 
በልጅነት ጊዜ ሰፊ ትዝታ አለው። ጎንደርን የምታውቁት
የዛሬን አለውቅም በፊት ግን ፋሲል መዋኛ ነበር።
 
በሚበስልበት ወቅት ከትምህርት ቤት ወጥተን እሱና
ሳንቀምስ ቤት አይታሰብም ነበር።
 
ዳማ ... ቀይም ጠይም ሳይሆን ማዕክላዊ ቀለምን ያመለክታል።
ዳማ ደማም ነው። ውበቱ ይማርካል። 
 
• ትክክለኛውን የባንባ ፍሬ አላገኜሁትም። ዛፋ ይመስላል ያልኩትን መርጫለሁኝ።
ዛፋ እንደዋርካ እና እንደ ሾላ ዓይነት ነው።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/02-06/2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።