ኮሽም።

 

ኮሽም።
 
“አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“
 May be an image of treeNo photo description available.May be an image of fruit and longan
 
 
• ሎሚ ከዚህ ቅዱስ መዳህኒት ይባላል። ኮሽምም ሎሚ ያለው አቅም ይኖረዋል ብየ
አስባለሁኝ። ቅጠሉም እንደ ወይራ ቅጠል ለጤና ይጠቅማል ብየ አስባሁኝ። ኮሽምም
ከእናት ዓለም ጎንደር የሚበቅል ፍራፍሬ ነው።
 
ኮሽም ... ኩርሽም
አትሽኮርመም።
ወርቃማው - ኮሽም ...
እባክህ አትለግም?
ጣፋጩ - ኮሽም ...
አትበል ዝም።
 
ድንቡልቡል - ኮሽም ...
ፈልግ እባክህ የአገር ልጅ ልባም።
ፈገግ በልልኝ ዓጤ ኮሽም ...
ላድርግህ! ኩርሽምሽም።
 
• ኮሽም ... ዱር በቀል ነው። ገበሬዎች ግን ገብያ ላይ ያውሉታል።
ትንሽ ሆምጠጥ ይላል። ወደ ሎሚም ይወስደዋል። ቀለሙ
ደመቅ ያለ ሉሚ ዓይነት ነው። መጠኑ ደግሞ ድቃቃ
ወይንም ትንሽ ቲማቲም ያክላል።
 
• አትለግም ... መለገም ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን፣ ማድረግ፣
እየቻልክ አትስነፍ። ልበ ቅን ሁን። ትጋት ይኑርህ ለማለት
ነው። ከዚህ ላይ ግን እኔ ልበላህ ፈልጌለሁ እና ለመበላትም
ሆነ ለመወደድ ተዘጋጅ ለማለት ነው።
 
• ኩርሽምሽም ...ድቅቅ አድርጌ በፍቅር እያጣጣምኩኝ ልብላህ ለማለት ነው። 
 
• ፈገግ በል … ሳቅ በል፣ ፍካ በል፣ ደስ ይበልህ፣ ፊትህ ይብራ …
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/02/2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።