የዕውቀት ሀይቅ ጥልቅ።
“አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“
የዕውቀት ሀይቅ ጥልቅ።
ምንም አያሳፍራም መጠየቅ?
ያልገባኝን ብጠይቅ ...
ዕውቀት እንደ ሆነ አያልቅ።
ዕውቀት ምንጊዜም ነው--- ብርቅ
ጣፈጭ መረቅ
የሚያደምቅ።
የዕውቀት ሀብል ወርቅ
ሁልጊዜ የሚያፈልቅ።
ድንቁርናን ያደቀቀ
ስንፍናን ያማቀቀ
ጥብብን ያጠለቀ።
ፍጹም ደማቅ!
ነው ትልቅ! የሚያልቅ
ማይጠገብ ድንቅ
የዕውቀት ሀይቅ።
ነው ጥልቅ!
ዓለምን የሚያደምቅ
ቀለማም የሚያበራ ፍልቅ፣
የማያልቅ!
* ማላቅ … ትልቅ ፣ ታዋቂ የሚያደርግ። የሚያስከብር:
* ዕወቀት ...
ከትምህርት የሚገኝ፣ የሰለጠነ አእምሮ ውጤት ነው።
ሌባ የማይዘርፈው የህሊና ሀብትም ነው።
በሁሉም የሙያ ዘርፎች መሰረቱ ጥልቅ ሰፊ ነው። ይህ በቀለም ትምህርት ወይንም ሃይማኖት ገብ በሆነ ሁኔታ የሚገኝ የዕውቀት ዘርፍን ይተረጉማል። ሊቃውንት የሚባሉ መደቦችንም ይፈጥራል። ከዚህ ውጪ ግን በፈጣሪ ጸጋ ከምንም የእውቀት ዘርፍ ጋር ሳይገናኝ እስከ ዊዝደም የሚያደርስ የዕውቀት ዐይነት ይኖራል፨ ይህ ሊህቅነት ይባላል። ኢትዮጵያን ያበጃት ይህ የማይመረመር የፈጣሪ ሥጦታ ልቅና ነው። ዘመን አመጣሹ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይህን ዕውቅና አይሰጠውም።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/02/2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ