እንኮይ።

 

እንኮይ።
 
“አድርገህልኛል እና አመሰግንለሁኝ።“
 
 No photo description available.May be an image of fruit and textMay be an image of fruit and stone-fruit tree
 
• እንኮይም ለጤና ጠቃሚ ይመስለኛል። ቅጠሉም ሻይ ቅጠል ይሆናል ብየ ነው
እማስበው። እንኮይም ለጤና ጠቃሚ ይመስለኛል። ቅጠሉም ሻይ ቅጠል ይሆናል ብየ
ነው እማስበው። ጣፋጭነቱ የማንጎን ያህል አይደለም። ጠረኑ የሙሽራ ዓይነት ነው።
 
• ጣፋጭነቱ የማንጎን ያህል አይደለም። ጠረኑ የሙሽራ ዓይነት ነው። ራህብ ያስታግሳል፥
የቸኮሌት ያህል አቅም እንዳለው አስባለሁኝ።
 
• እንኮይ …
 
አንተ ለስላሴ ሉል እንኮይ
የእመየ መሳይ …
የውስጥነት - አወያይ።
እንክብል ጠረንህ - ያምሮት የሲሳይ
የሁነት ለዛ - የሰናይ
ፍሬህ ያማረ ምርጥ - ዘር
ጹዑመ ጤና - `ያገር
የባላገሩ - ርስተ - መንበር።
ጣፈጭ - ዘለላ
የእኔ - ወለላ።
አልጠግብህም ሁሌም
የለህም - ልግም።
እንኮይ ገር - ገራገር
ልዩ የልጅነት የፍቅር - ክር
ትዝታ - የምታከብር
ህብረ - ዘር።
የአድዮ - ቤተኛ
የሰንደቃችን - ማህለኛ
የእኛ - ሁነኛ።
 
• እንኮይም …
 
ዱር በቀል፡ ብሩህ ቢጫማ ቀለም ያለው፡ መጠኑ
እንደ ኮሽም ወይንም እንደ ትንሽዬ ቲማቲም ሲሆን
እንደ ኮሽም አይሆመጥጥም። ጣፋጭ ነው። በሌላ
በኩል የኮሽም ሽፋኑ ትንሽ ኮስኮስ ይላል። የእንካይ
ግን በጣም ለስላሳ ነው። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/02-06/2026
 
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።