ፍቅር የጸሐይ መውጪያ እንጂ መግቢያ አይደለም!
ፍቅር ዕዳ አይደለም። „አቤቱ አንተ ምህረትህን ከ እኔ አታርቅ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ!“ (መዝሙር ምዕራፍ ፲፩ ቁጥር ፴፰) ከሥርጉተ©ሥላሴ (ከኮሽ እይሏ ሲዊዝሻ) 17.07.2018 · መነሻዬ https://www.satenaw.com/amharic/archives/60747 „ የኤርትራው ዕርቅ ፈተና ይጠብቀዋል “ ይለናል ዋዜማ ራዲዮን፤ ዘሃበሻ እና ሳተናው ማዕዴ ናቸውና ከሳተናው ባገኘሁት ሁለት ጉዳይ ላይ የምለው ይኖረኛል። ሁለቱም ተያያዥ ባይሆኑም ተቀራራቢ ናቸው፤ ይሄኛው ትንሽ ከተስፋ ጋር ይገናኛል ሁለተኛው ግን ጨልምተኛ ነው። „ የ ኤርትራው እርቅ ፈተና ይጠብቃዋል “ ፈተና አልባ ህይወት፤ ፈተና አልባ ኑሮ፤ ፈተና አልባ ነፍስ አይፈጠረም። ፈተና በአንድም በሌላም የኖራል። ፍቅር ደግሞ እንደ ተፈጥሮ አባልነቱ ተፈታኝ ነው። እንዲያውም የበዛው ፈተና በእሱ እና በአርበኞቹ ላይ ነው። እንኳንስ ሰው አንሰሳት ነፍሳትም ሚዳቋ ከፈተና ለመዳን ነው ጉድጓድ እምትቆፍረው ... አሳን ለማጥመድ ነው መረብ የሚሠራው ... ወደ ቀደመው ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ጉዳዬ ምለሰት ሳደርግ፤ የፈለገ ጫን ተደል ፈተና ይኖር የፍቅር ተፈጥሮ መርሆዎች ድል የማድረግ አቅማቸው ከሰውኛው በላይ ነው። በፍቅር ተፈጥሯዊ መርሆዎች ጥናት ለማድረግ ቢታሰብ የመዋለ ዘመን ክስተት መሆኑን መረዳት ይቻላል። ፍቅር ፈታኝ ሁኔታዎችን የሚፈታበት መሳሪያው በእጁ ነው ያለው። ...