አብይ ኬኛ ለነባቢት ርትህኛ!
የበደል ናፍቆት ግራጫዎችን አመሳቸው።
„አህዛብን ገሠፅህ፣ ዝንጉዎችን አጠፋህ፣
ስማቸውን ለዘላለም ደመሰስህ።“
(መዝሙር ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፭)
ከሥርጉተ©ሥላሴ
(17.07.2018)
የአላዛሯ ኢትዮጵያ ክብር እዬጎላ መምጣት ያመማቸው እርኩሞች አሁንም እንደ ማህበረ ሳዖል በተለመደው የሴራ ገመዳቸው ኢትዮጵያን አቧራ ለብሳ የጥላሸት ጠቀራ መደብር ትሆን ዘንድ እዬታተሩ ነው።
እራሱ ከዛ መከራ የወጣው አርበኛ ያ ሰቀቀን እናዳይደገም ይህ አብያዊ መንፈስ የዘላለም የፈወስ መንገድ እንዲሆን ከማበረታት ይልቅ ጨዋታው ሌላ እና ሌልኛ ሆኗል።
ያ የሚያንገፈግፍ እና የሚያነዘፈዝፍ የ27 ዓመት መከራ ደግሞ ይመጣ ዘንድ በቀለኞች አጋጣሚውን አግኝተው የልባቸውን ይወጡ ዘንድ ቅዱሱን የአብይ መንፈስ ብስጩ እና ገርጭራጫ በማድረግ የተለመደ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እዬታተሩ ነው።
በዚህ ሁኔታ የታሰበው የሽግግር መንግሥት ዕውንነትን ለማምጣት ነው ትልሙ። ግን ለአንዱም ሳይሆን ፈሶ ይቀራል። እርስ በርሳቸው መተማመን አይደለም ሰላምታ እንኳን የማይለዋወጡ ናቸው።
በአንድ ከተማ እዬተኖረ በአንድ የነፃነት ማዕዶት መስዋዕትነት እዬተከፈለ አንዱ ሌላውን ሲያደባ፤ ሲሰልል፤ ሲያሳድም ነው የኖረው።
ዛሬ ይህ በምድር ሊሆን ይችላል ተብሎ የማይታሰብ ቅናዊ ንጹህ ቅዱስ መንፈስ ወደ ፊት መጥቶ ሁሉንም በመፈውስ እርምጃ ሲጀመር የለመደባቸውን የጭካኔ እሾሕ ሰራሽ ሸንክነታቸውን በ አንድም በሌላም እአስተዋል ነው።
ያን ገመና እንደ ተሸከሙ ሌላ ሴራ በደባ በመምራት እንደገና በምንትሶ፤ በቅብርጥሶ ድርጅት እዬተባለ አዲሱ ወጣት ደግሞ ተለቅሞ እስር ቤት ገብቶ የድርብ ጥቃት ሰለባ እንዲሆን እዬተፈለገ ነው።
የአገሬ ልጆች የበፊቱን አይታችሁታል ሰምታችሁታል። ማብራሪያ የሚያስፈልገው አይደለም። በቄሮ እና በአማራ ተጋድሎ የድል እርካብ እና የታሪክ ሁነኛነት ድብን ብሎ የበገነው ጸላዬ ሰናያዊ መንፈስ እንዲህ ዕድሉን በመንግሥት ካገኜ አጋጠመኝ ብሎ ዓይናቸው እያዬ እዬሰማ ይዘለዝላቸዋል።
ለዚህ ህጋዊ ሥልጣን ይሰጠው ነው አሁን እየተፈለገ ያለው … „የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ ያሰጠወም ይሄው ነው፡“ ለውጥ እንፈልጋለን በሚለው ሚዲያ፤ የፖለቲካ ሊሂቅ፤ ጋዜጠኛ አክትቢስት የአብይ መንፈስ እጅግ ተገፈተረ …
የአብይን መንፈስ ተፈጥሮ ይህ የወል የሴራ ደቦ እዬፈተነው ያለው። ግራጫማው አማሽ መንፈስ ግርፉ ይሄው ነው።
የአብይ መንፈስ ቁጡ፤ ቁንጥንጥ፤ ትእግስት አልባ፤ ገርጭራጫ ሆኖ በመደዴ ለሚደረሰው ጥቃት ተጠያቂ ለማድረግ ነው ሸር ጉዱ … የጸሐፊውም፤ የአክቲቢስቱም፤ የሚዲያው ዕለታዊ ተግባር ይሄው ነው።
በሌላ በኩል ትናንት ሁሉም ነገር በኤርትራ ይመካኝ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ያ ሲከስም ሌላ አዲስ አሽክለሌ ተፈጥሮ የሽግግር መንግሥት ህልመኞች በአንድም በሌላም የህዝብን ስሜት በመክፍል እና በመሰንጠቅ የሴራቸው ተባባሪ በማድረግ በዬ አካባቢው ግጭት እና ሁከት ሰፍኖ አብይ በቃኝ ተረከቡኝ እንዲል ወይንም ወደ ተለመደው የመንጥር ዘመቻ እንዲሄድ እዬተገፋፋ ነው። እጅግ ያሳዝናል።
በዚህ ማህል ለ43 ዓመት የልጅ ሊኳንዳ ቤት በማህጸኗ ከፍታ የሥም ሉዑሎችን፤ የዝና አክተሮችን፤ የኩራት ንግሥና ቅጥልን፤ ድንቅና ግርማ ሞገስን ለሊሂቃን ስታቀዳጅ የኖረቸው የአላዛሯ ኢትዮጵያ እናት ላዳግም የሰው ብርንዶ ትሰናዳ ነው ትግሉ የአሁኑ።
በሌላ በኩል የስሜን አሜሪካኑ የስፖርት ግብዣ ሲቀር አሁን ደግሞ ሁከቱ አይሎ ለሰላም ዓለም አቀፍ ሽልማት የታጨው ኢትዮጵያዊ መንፈስ፤ ሸላሚው ድርርጀት ቀውሱ አልበረደም ብሎ ጥርጣሬ መረቡ እንዲሆን ለማድረግ ሆን ተብሎ ታቅዶ ነው እዬተከወነ ያለው።
በደል መታረድ አካል መጉደል መንኮላሸት ዘር መጥፋት መፈናቀል አልበቃንም እና አብይ ደግሞ ይህን ድገመን እና አሳያን፤ ያን ጊዜ ጎሽ የእኛ ጀግና በማለት መስጥረን እንልህ እና 4 ኪሎን በአቋራጭ እኛው ለእኛው ይሆናል ነው።
የ4ኪሎው ቀይ ምንጣፍ እስተወንበሩ ካልተረጋገጠ የኢትዮጵያ ሳላማዊ ሽግግር ምን ሲያደርጋላቸው ለእነሱ። ለዚህ ካለሆነ እንደ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ በምራባውያን ታግዞ በመሪነት ተኮፍሶ የድል አርበኛ አስካልተሆን ድረስ ምን ሲባል? እንደ ተርታ ዜጋ ወድቆ ተነስቶ ዓላማን ለማሳካት ጥሮ ግሮ ቆላ ደጋ ኳትኖ አደራጅቶ ምን ሲባል የሥልጣን ፉክክር ነው ሂደቱ … የብራናውም የማይኩም ውሎ አዳሩ ይሄው ነው።
ለዚህ ነበር ደቡብም ላይ ምስራቅም ስሜንም ላይ የሚታዬው የሴራ ሸር ጉድ … እኔ ደግሞ የምለው ለቄሮም ለአማራም እውነተኛ የህልውና ታጋዮች ይህ የአብይ ካቢኔ እጅግ በጣም የበቃ ነው።
ለሁሉም ነገር የጸደቀ ነው። ሰዋዊም ተፈጥሯዊም ነው። ቁሳዊ አይደለም። ወንበራዊም አይደለም። ለእኔም - ለአንተም - ለንቺም - ለሁላችንም እኩል መንፈስ ያለው ንዑድ መንፈስ ያለው እጅግ ቅን እጅግም አዛኝ ነው።
ስለዚህ አላዛሯ ኢትዮጵያ በሴራ ተወራ ድልህን ሳትቀማ አሁኑኑ ጊዜ ሳታጠፋ ለዚህ ልዕልናዊ መንፈስ እራሰህ ዘብ ቁምለት ቄሮም አማራም ታገድሎም።
እራስህ አለሁህ በለው። ዋናው ቁም ነገር ሰንጣቂ፤ ተርታሪ፤ መንፈስ አዋኪ ጹሁፎችን አታንብ። ሚዲያም ከሆነ አታዳምጥ። ወደ መንፈስህ የቀረበውን ከሴራ ጋር ምንም ንክኪ የሌለበትን የእውቀት ዓወደ ምህረትን ብቻ አዳምጥ። በቃ ሴራው በራሱ ጊዜ በቅሎ በራሱ ጊዜ ይከስማል።
ሌላው ለትግራይ ልጆች ከመቼውም ጊዜ በላይ አንተ እራስህ ዘብ ቁምላቸው። ጠብቃቸው። ዝንብቸውን እሺ እንዳይባልም ተንከባከባቸው። አሁን የሚፈለገው ቁርሾና ቂም ገንፍሎ ማዕቱ እዛ ላይ እንዲነድ እና እርስ በእርስ ለማዋጋት የታሰበው ስለከሸፈ በዛ መልክ ለማትረፍ ነው።
ስለሆነም አንተ እራስህ ፍቅርህን ሳትሰስት ከእውነት እና ከልብ ስጣቸው፤ ያን ጊዜ አንተ እራስህን ያሸነፍክ የጀግኖች ቁንጮ ትሆናለህ። አትርሳ ዘራእይ ደረሰን! ይህን የጣስክ ዕለት ፈጣሪ ይከፋብሃል።
መልካምነትን ምራኝ ካልክ ግን አንተ ራስህን የገራህ ሰማዕት እና ጻድቅም ነህ። ከዬትም ይምጣ መወራጨት ከጆሮህ አታንጠልጥለው። ለሰው ልጅ መኖሩን የሚሰጠው ፍቅር ብቻ ነው። ትውልድን የሚገናባው ፍቅር ብቻ ነው። ትውፊትን የሚያቆዬው ፍቅር ብቻ ነው።
ታሪክን የሚያበቅለው ፍቅር ብቻ ነው። ይህን አብነታዊ ጉዞ እኔ ባልጠበቅኩት ሁኔታ አገሬ መሬት ላይ ሲጀመር እጅግ ይገርመኛል። እጅግም ያለሁባት መሬት አዲስ ፕላኔት እንደሆነች ይሰማኛል።
ምኞቴ የእኔ ስካንዳንብያ አገሮች ጋር አንዱ አገር ላይ ይጀመራል ነበር፤ አሁን አገሬ የፍቅር ቀን ሁሉ አውጃለች … የሰው ልጅ ሁሉንም መከራ ለመሸከምም መፍትሄ ለማምንጨትም አይችልም፤ የፍቅር ተፈጥሯዊ መርህ ግን ይችላል።
የሰው ልጅ አንዱን ችሎ ቢያሳልፍ ሌላው ላይ ሊታክተው ይችላል፤ የፍቅር ተፈጥሮ መርህ ግን ከሰው ልጅ በላይ ቻይ እና ታጋሽ ነው። ስለዚህ ከፍቅር ጋር በተለያዬ ሁኔታ ግብግብ እዬገጠሙ ያሉትን አውሬያዊ መንፈሶች ከዬትም ይምጣ፤ ከሰማይ መላዕክም ይምጣ አደራ እንዳታስጠጋው!
የአገሬ ልጆች የምትናፍቁኝ፤ የምሳሳለችሁ አዳራ እንዳታስጠጉት ይህን የኖረ የተበከለ እምል የሴራ እድፍ!
ታጋሽ መሪ ብዙ የሚፈታተነው ሃይል አለ። ትእግስቱ ያለቀ ቀን ፍቅር ይሰደዳል … ይህን እንዳያደርግ አዲሱ የአብዩ ካቢኔ እጅግ ልንጠነቀቅለት እና የሚለውን አድምጠን በፍጥነት ለመተርጎም ዘብ አደሮች መሆን ይገባናል! ይርዳን አዶናይ! „አሜን!“
ፍቅር የነፍስ ሞድ ነው!
አአብይ ኬኛ ለነባቢት ርትህኛ!የኔዎቹ ኑሩልኝ!
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ