ፍቅር የጸሐይ መውጪያ እንጂ መግቢያ አይደለም!

ፍቅር ዕዳ አይደለም።
„አቤቱ አንተ ምህረትህን ከ እኔ አታርቅ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ!“
(መዝሙር ምዕራፍ ፲፩ ቁጥር ፴፰)
ከሥርጉተ©ሥላሴ
(ከኮሽ እይሏ ሲዊዝሻ)
17.07.2018


  • ·       መነሻዬ

የኤርትራው ዕርቅ ፈተና ይጠብቀዋልይለናል ዋዜማ ራዲዮን፤ 
ዘሃበሻ እና ሳተናው ማዕዴ ናቸውና ከሳተናው ባገኘሁት ሁለት ጉዳይ ላይ የምለው ይኖረኛል። ሁለቱም ተያያዥ ባይሆኑም ተቀራራቢ ናቸው፤ ይሄኛው ትንሽ ከተስፋ ጋር ይገናኛል ሁለተኛው ግን ጨልምተኛ ነው።  

ኤርትራው እርቅ ፈተና ይጠብቃዋልፈተና አልባ ህይወት፤ ፈተና አልባ ኑሮ፤ ፈተና አልባ ነፍስ አይፈጠረም። ፈተና በአንድም በሌላም የኖራል። ፍቅር ደግሞ እንደ ተፈጥሮ አባልነቱ ተፈታኝ ነው። እንዲያውም የበዛው ፈተና በእሱ እና በአርበኞቹ ላይ ነው። እንኳንስ ሰው አንሰሳት ነፍሳትም ሚዳቋ ከፈተና ለመዳን ነው ጉድጓድ እምትቆፍረው ... አሳን ለማጥመድ ነው መረብ የሚሠራው ...  
 
ወደ ቀደመው ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ጉዳዬ ምለሰት ሳደርግ፤ የፈለገ ጫን ተደል ፈተና ይኖር የፍቅር ተፈጥሮ መርሆዎች ድል የማድረግ አቅማቸው ከሰውኛው በላይ ነው። በፍቅር ተፈጥሯዊ መርሆዎች ጥናት ለማድረግ ቢታሰብ የመዋለ ዘመን ክስተት መሆኑን መረዳት ይቻላል። ፍቅር ፈታኝ ሁኔታዎችን የሚፈታበት መሳሪያው በእጁ ነው ያለው። 

ከሁሉ በላይ የፍቅር መርህ ተፈጥሯዊና ሰውኛ ስለሆነ ለቁስ፤ ለማተርያል፤ ለሸቀጥ ጊዜ አያባክንም። አቅምም አያፈስም። የፍቅርን ስጦታ በመለኪያ አትሰፍረውም ወይንም በድርጎ አትመጠነውም፤ ወይንም በሜትር አትመትራውም ፍቅር ረቂቅ መንፈስ ነው። 

ለፍቅር የሚሰጠው ስጦታ ራስን ነው ኢትዮጵያ ፍቅሯን ለኤርትራ ስትሰጥ አራሷንም ነው፤ ኤርትራም ፍቅሯን ለኢትዮጵያ ስትሰጥ ራሷንም ነው። ይህ በፍቅር ተፈጥሮ መርሆዎች ላይ አጀንዳቸው ላልሆኑ ስብዕናዎች ሊከብድ ይችላል፤ ግን በዛ ውስጥ ቀሪ ዕድሜን ለማሳለፍ ለወሰኑ፤ ለመነሻ የሆኑ ነገሮችን እዬሠሩ ላሉ ነፍሶች ግን ለፍቅር ዳር ደንበር እንደማይበጅለት ጠንቅቀው ያወቁታል። ፍቅር ዳር ድንበር የለውምና። 

ፍቅር ሚዛን ልተበጀለትም። ሰውንም ያበጀው ግን ፍቅር ነው። ተፈጠሮንም ያበጀው ፍቅር ነው። ሃይመኖትንም ያበጀው ፍቅር ነው፤ አገርንም የሚሠራው ፍቅር ነው። ጥበብንም የሠራው ፍቅር ነው። መታመን የተፈጠረው ለፍቅር ነው። 

ማክብር የተፈጠረው ለክብር ነው። ማድነቅ የተፈጠረው ለፍቅር ነው። ዕቅውቅና የተፈጠረው ለፍቅር ነው። ቸርነት የተፈጠረው ለፍቅር ነው። ትህትና የተፈጠረው ለፍቅር ነው። ልስሉስነት የተፈጠረው ለፍቅር ነው። ቅንነት የተፈጠረው ለፍቅር ነው። ዕውነት የተፈጠረው ለፍቅር ነው። ርህርህና የተፈጠረው ለፍቅር ነው። ምስጋና የተፈጠረው ለፍቅር ነው። አዛኝነት የተፈጠረው ለፍቅር ነው። ድንገተኛ ደስታ የተፈጠረው ለፍቅር ነው። ትውልድ ራሱ የተፈጠረው ለፍቅር ነው።

ፍቅር ጊዜንም፤ አቅምንም፤ መዋለ ንዋይንም ይቆጥባል። መንገዱ አጭር ጊዜውም ፈጣን ነው። ስለምን? ፍቅር ብርሃን ስለሆነ ... ከብርሃን የቀደመ ክስተት ፕላኔታችን አስተናግዳ አታውቅም ... ፍቅር የጸሐይ መውጫ እንጂ የጸሐይ መግቢያ አይደለም፤፡  

የፍቅር ትርፍ ተጠንቶም አያልቅም። ለዚህ ነው እኔ ዓለም ሚስ ያደረገቸው ነገር የፍቅርን ተፈጥሮ በት/ ደረጃ እንዲሰጥ አለመዳርጓ፤ ፍቅር ኮመን ሳብጀክት አለመሆኑ፤ ወደ ታላላቅ ተቋማት ተማሪዎች ሲገቡ በዚህ ሰብዕና ውስጥ ስለመኖራቸው መረጋጋጥ አለመቻሉ አለማችን አስፈሪ አስደንጋጭ እና አስጊ ከማድረጉም በላይ ነገ ጉም ለብሶ ይታዬኛል ብዬ እምሞገታው።

የሆነ ሆኖ የዋዜማ ስጋት እና ተስፋን የያዘ ነው። ያው ከኤርትራ ጋር ሊደረጉ ያሰቡ ውሎች ጥንቃቄ ሊደርገባቸው ይገባል ነው ጥቅል ዕድምታው። በሌላ በኩል ትርፍና ኪሳራውም የግንኙነቱ ሊመዘን ይገባል የሚል ነው። 

ሌላ ጸሐፊም „የእነ ቶሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ ባይ“ ናቸው። 
ይህ ባጣም ጨልምተኛ የወሆነ ሃሳብ ነው። የሆነ ሆኖ ሁለቱም የአገርን ጉዳይ የእኔ ያሉ መንፈሶች ናቸው ቅኖችም ናቸው ብዬ ነው የወሰድኳቸው።

ያ ስጋት እና ጥርጣሬ እንደ ቀደመው ቢሆን እኔም ለረጅም ጌዜ እሰገበት የነበረው ጉዳይ ነበር። ምክንያቱም የኤርትራ ጉዳይን ከልጅነት ጀምሮ አብሮኝ ያደገ የፖለቲካ ሁኔታ ስለነበር። 

ስለዚህ በማናቸውም መሥፈርት ኤርትራ ለነፃነት ፈላጊዎች ታደርግ የነበረው መልካም ነገር ጥግ ስለሆነ ባከብረውም ግን በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ሊኖር የሚገባው የፖለቲካ መስምር እና ትስስር ሁልጊዜ የስጋት ምንጬ ሆኖ መኖሩን አውቃለሁኝ።

አሁን ያለውን ቅናዊ ደፋር እርምጃ ግን እሰቀድሜ ነበር እኔ የተቀበልኩት። ለዚህም ነው የባድም ዕድምታ በሥርጉተ ዕዬታ የጻፍኩትን። ለዛውም የቤተ መንግሥቱን አንቱ ምርጥ ጋዜጠኛ ሞግቼ። 

ስለምን? አሁን ኢትዮጵያ እኛ ከምናስበው ከምናውቀው በላይ እጅግ በላይ ሙሉ አቅም ያለው መሪ ስላለን። ብቻውንም አይደለም የጀርባ አጥንቶቹ ሁሉ ፍሬ ዘለቅ ናቸው። በሌላ በኩልም ኤርትራም አይታዋለች። ምን ያህል መንፈሳዊ ትርፍ እንዳገኘች! ጊዜ ያስተምራል … ጊዜም ታሪክ ይሰራል።

ውሳኔው እራሱ ቁሳዊ አልነበረም። በፍቅር አሸነፊ እና ተሸናፊ የለም፤ ድል የሚያደርገው ዓለም አቀፍ ህግ ነው ሁሉ ጽፌያለሁኝ። ስለምን ጠረኑ ንጹህ ነው። ብጣቂ ሴራ አልነበረበትም የኤርትራውያን የኑልን ጥሪ። 

እኛ የደንበር፤ የወሰን ጉዳይ አይደለም የምንፈልገው እኛና እናንተ የመንፈስ ሃዲድ እንፍጠር፤ ለእኛ ከእናንተ በላይ የሚሆንብን ምንም ነገር የለም ነው። ያ ነበር የመጀመሪያው የመጋቢት 24ቱ የሹመት የፍቅር ግብዣ።

ከዛ የቀጠለው የውሳኔው ይዘት „ያለምንም ቅድመ ሁኔታ“ እጅግ የጀግና ደፋር እርምጃ ነበር። ቆፍጣና ውሳኔ ነበር። ኤርትራ ለመልሱ ስትዘገይ እኔ አልተረበሽኩኝም። ምንም አልጻፍኩኝም። ምክንያቱም „የረጋ ወተት ቅቤ“ እንሚወጣው አሳምሬ አውቃለሁኛ እና። 

ከዛም በላይ ሁልጊዜም እንደምለው ብዙም የሚዲያ ጥመኛ አይደሉም ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ። ግድ ካልሆነባቸው ሚዲያ ላይ አይወጡም። ስለዚህ አደብ ገዝቼ ነበር የተከታተልኩተኝ።

ከዛም መልሱ ታምራዊ ነበር። ጉራጌ ዞን መዳፍ ነው። መዳፍ ደግሞ ሁለመና ነው። በዛ መፍትሄ ይሆናል ብዬ ህልም ነበረኝ። ግን ፈቃዱን ፈጻሚው የተመረጠው ሌላ መሪ ሆነ። ይህ በራሱ በመንፈሳዊ ትርጉሙ ለእኔ ሌላ ማብራሪያ፤ ሌላ ቀጨሬ መጨሬ፤ ሌላ የጥርጣሬ ሰነድ የሚያስመዝዝ አልነበረም። 

27 ዓመት ሙሉ ለሽ ብሎ ከርሞ ጉራጌ „ክልል እንሁን“ ጥያቄውን እንዲያነሳ ቆሽቋሽ ቢኖርም ያ ሳብያ ነበር። ከዛ በፊት ሦስት የሰማይ ታምሮች ታይቷል። 

መጀመሪያ ፈጽሞ ያልተለመደ ድምጽ፤ ቀጥሎ ፈጽሞ ታይቶ የማይታወቅ ዝናብ፤ መጨረሻ መሬት ከሁለት ተቀረደደ። ይህ ሁሉ ምክንያት ነበረው። የፈጣሪ ምህረት ሲወርድ ጉራጌ መሬት ላይ ነበር ግን ቅብዕ ለተሰጠው። የሆነው ይሄ ነው። ቁርጥ ያለ የእዮር ውሳኔ ነበር። ቅብዕ የፈጣሪ ነው …


ያ መሬት ለታምር ነው የተፈጠረው። ከዚህ ጋር አብሬ ማዬት የቻልኩት ሚስጢር ከዛ ሁሉ የጋህዳዊ የስብሰባ ቁጣ፤ የሰማይ እና የጋህዱ ዓለም ጥያቄዎች በመለስ የሆነው ነገር ደግሞ እዮራዊ ነበር። እዮራዊነቱ የአብዩን መንፈስ ደግፈው ሲወጡ ይዘውት የወጡት ሰንደቃቸውን ነው። 

ያ የምህረት አዋጅ ብቻ ሳይሆን የውስጣቸውን ንጽህና ያበሠረልኝ ልዩ መክሊት ነበር። እንግዲህ ዶር. አብይ አህመድ እዛ እያሉ ነበር የፕ/ ኢሳያስ አፈውርቂ አዎንታዊ ምላሽ ያገኙት።

„የኖረ መከራ አሸክማችሁኝ ብተረተርላችሁ ምን ትጠቃማለችሁ“ ብለው ክፍት ባላቸው ሰዓት ያ የምሥራች ዜና መጣ። እሳቸውም ውንደሜ ደስ አለኝ ብለው መልስ እዛው ታምረኛ መሬት ላይ ሆነው ላኩ። መንፈስ ቅዱስ የፈቀደው ቅብዕ አብዩን ስለሆነ። ይህ ለዳርቻም በጥልቀት ሊታይ፤ ሊመረመር የሚጋባው እጅግ ረቂቅ እዮራዊ ሚስጢር ነበር።

በቀጣዩ ቀናትም ለዶር አብይ አህመድ አይዞህ አብረንህ እንቆማለን ሲሉ ነው ሉዑኩን የላኩት። እኔም አብሮኝ የኖረ ግን የማላውቀው ስሜት ባለቤት መሆኔን ያወቅኩበት ማዕልት ያን ጊዜ ነበር። የኤርትራው ልዑክ መሬቴን ሲረግጣት ሌላ የማለውቃት ሥርጉትሻ ነበረች። ዕንባዬ ሲወርድ እራሱ የእኔን ፈቃድ አልጠዬቀኘም ...  

ያን ጊዜ እኔ ጥርጣሬዬን፤ ስጋቴን ሁሉ ከባህር ከገደል ጥዬ ወይ ጉድ በመለየታችን ይህን ያህል ከውስጤ ተጎድቼ ነበር ወይ ብዬ አምላኬን አመሰገንኩኝ። ለማናቸውም ውሳኔ ልቤን በንጽህና እና በድንግልና ክፍት አደረኩት። በተሟላ ሁኔታ ተሰናዳሁኝ። የባድመ ጉዳይ መቋጨት ለትግራይ ሳይሆን አትራፊነቱ ለጎንደር የመከራ መብቃት አዲስ ዓዋጅ ነበር።

ጎንደርም በዚህ አጋጣሚ ልብ ብሎ ሊያደምጠው የሚገባው ቁምነገር ይህን ነው። ከእንግዲህ የምንተሶ ፓርቲ አባል እዬሆነ ትወልድን ለተለያዬ የቂም መቋጠሪያ እንዳያደርግ ብርቱ ትምህርት ሊወስድበት ይገባል። አብዩ ለጎንደር ጌጡ ነው! አብዩ ለጎንደር ጌጡ ነው! አብዩ በቂው ነው! ያ የተስተጓጎለው የመስቀል ዓመት ምላሹ ይሄው ነው። ከልቡ ከመንፈሱ ሆኖ እኔን ከልታማዋን ልጁን ጎንደር ማዳመጥ ይኖርበታል።

እኔ እንደማስበው አብዩ መንፈስ ቅዱስ ቅርባቸው ስለሆነ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ኤረትራ ገቡ ሲባል ማረጋገጫ ፍለጋ በዬቦታው ነበር የማሰንኩት። እርግጥ መሆኑ ሳውቅ እና ያን የመሰለ ሳቅ ከፕ/ ኢሳያስ አፈውርቂ ሳይ ከውስጤ፤ ከልቤ ከመንፈሴ ከነፍሴ ደስ አለኝ። ሁልጊዜ ፎቷቸውን ሳይ ሳቅ የለበትም ነበር። አንድ አለ ግን የውስጥ አልነበረም። 

የመልሱ ጉዞም አብረን የነበርንበት ነው፤ ትልቅ የህሊና፤ የአደራ ዕዳ ተሸከምው ነው ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ የተመለሱት። እሳችም እንደ እኛ ፍጡር ናቸው እኮ። ፍቅርን የሚገፉበት አቅም ከእንግዲህ አይኖራቸውም። ቢያስቱም የአብዩ ስበት መግፋት አይቻቸላቸውም እእ! እብዩ ማግኔት ነው!አይጠገበም! መንጠግቦህ ነው እንዲህ ብዬ ሁሉ አንድ ቦታ ላይ ጥፌው ነበር። 

በዛ ላይ እድሜም ብዙ ነገር ያበረክታል። ታሪክንም እንደገና ገንብቶ ማለፍም መታደል ነው። ከሁሉም እሳቸው ዕድለኛ ናቸው። ለዚህ ዘመን በቁ። ቢነጋራቸው አያምኑም ነበር ከማህል እስከ ደንበር ይህን ያህል በልብ ውስጥ ተመስጠረው እንደተቀመጡ …

ስለሆነም በዛ ሁሉ የዕድሜ ልክ እምስ ፖለቲካ የከሰረው ነገር ሁሉ ላይመለሱበት ቁርጥ ውሳኔ እንደሚያሳልፉ እርግጠኛ ነኝ። ስለዚህ ፍቅር ዕዳ አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅሩን ነው የሰጠው። ራሱን ሰጥቷቸዋል። 

ሌላው ለእኔ እንካ ስላንትያ ነው። ገና ይሆናል እዬተባለ የተሰበሰበ መንፈስን ማወክ አይገባም። ገና ደስታውን ከደሙ ጋር ሳያዋደድ ደግሞ ተርታሪ ተጠራጣሪ ወጣሪ መንፈስ እዬፈጠሩ ማወክ ለእኔ የጸላዬ ሰናይ ምኞትን ማበረታት ነው።  

የህዝቡን የፍቅር መንፈስ ባናባክነው ይመረጣል። ብዙ የተደከበት ነው። ብዙ ነፍስ የጠፋበት ነው። ብዙ ዘመን ውስጥ ጥቁር የተለበሰበት ነው። አሁን ደግሞ በቃችሁ ስንባል ይህ ዕድል ብንከባከበው፤ ለአፍሪካም ፍጹም መሠረት ይሆናል፤ 

በሌላ በኩል ውጪ ሆነን ፍቅር ሲመጣለት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንቀናለን የ አላዛሯን ኢትዮጵያ መከራውን ችለን ለመኖር ሳንደፍር፤ ከራስ ጋር መታረቅ ያስፈልጋል፤ ኢትዮጵያን ብናዝነላት ጥለናት አንወጣም ነበር … እዛው የፊታቸው ቀለም ወንዶቹ እስኪቃጠል ድረስ ነው አብረው የተከኑት ... 

ማመን ያተርፋል። መጠራጠር ግን ራስን ውስጥን፤ ቤተሰብ እያወከ በሽተኛ ያደርጋል። ጥርጣሬ ውስጥን እያኘከ አኞማኞ ያደርጋል። ገጽንም ያጠንዛላል። መጠራጠር ጤዛ ነው፤ እምነት ግን ሰብል ነው።
  • ·       ሁለተኛው ጨለምተኛ ሃሳብ።   

"የቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ (በላይነህ አባተ)"

በሌላ በኩል „የእነ ተሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ“ በሚል ሥንኛትንም አንብቤያለሁኝ። ያው የተመደው ታቱ ዥገራ እና ዕንጉልች ቀረብን ዓይነት ነው። በመጀመሪያ ይህ የህዝብ ሃብት ስለሆነ አባባሉ ትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ማሰገባት የመጀመሪያው የጸሐፊ ተግባር ነው። ሌላው ግን ተረቱ ካለቦታው ነው የተቀረቀረው። የግጥሙ ረቂቅነት ግን አሊ አይባልም። ለ አዎንታዊ ቢሆን ሰሃ አይወጣለትም። ለአሉታዊም ቢሆን መብት ነው። ቅናዊም ነው። ምክንያቱም ተዚህ ቀደም አዎንታዊ የሆኑ እድምአተዎችን ሰላነበብኩኝ። 

ወቼ ጉድ ግን ብያለሁኝ ቸኮለ ስለሚል ስንኙ፤ ... ተኖረበት እኮ ስንት ትውልድ ዕዳ ከፈለበት ከአራት ትውልድ በላይ ይህ አይበቃንም። የዛ በርሃ እራት የሆኑ ወንድሞቻችን እኮ አሉን። ሰው እኮ ዳን ካለው፤ ተፈወስ ካለው ቅጽበት ያድነዋል። በሽታን ማዳን እንጂ ማስታገሻ እዬሰጡ ማቆዬት በሽታው እንዲያጠቃ ዕድል መክፍት ነው የሚሆነው። በሽታው መደሃኒት ላይደነው ከማይችለው ይደርሳል፤ ቀጣዩም ሞት ነው።
  
ስለዚህ ይህም ቢሆን ሃሳብን መግለጽ መብት ቢሆንም አድማጭ ሳያገኝ የሚቀር ተንሳፋፊ ጉዳይ ነው። ፍቅር ሌላው ሳይቀበለው ቢቀር እንኳን ለጋህዱ ዓለም ሳይሆን ለሰማዩ አለም ቀጥ ያለ የጽድቅ መንገድ ነው። ፍቅርን የደፈረ መሪ ኢትዮጵያም፤ አፍሪካም የማግኘት እድሏ ጠባብ ነው የነበረው።

ፍቅር የወደደ አይዋሽም፤ ህዝብ አያታልም፤ የሆነውን ሆነ ያልሆነውን አልሆነም፤ የሚያደርገውን አደርጋለሁኝ የማያደርገውን አልችልም ነው የሚለው። ፍቅን የደፈረ መሪ ተከታዮችም ፍቅርን እንዲደፍሩ እንጂ ፍቅርን እንዲፈሩት አያደርግም። ፍቅርን የደፈረ መሪ ህገ እግዚአብሄር የገዛው ስለሆነ ለመንፈሳዊ ሃባቶች ሐዋርያ ነው። 

ፍቅርን የደፈረ መሪ ተፈጥሮን አክብሮ ስለሚነሳ የዋለበት፤ ያደረበት፤ የተገኘበት ሁሉ እሽት ነው …

ዛሬ ልባችን ሞልተን የሚናገረን መሪ ስላለን፤ አንገታችን የምንደፋበት ሙሴ ስላለን፤ የመንግሥት ሚስጢር ካልተዘረገፍለን ብለን የወለሌ ገበታ አንልም፤ ይልቅ ባለፈው እንደተናገርኩት ያልታሰቡ አዲስ የምሥራቾች ስለሚኖሩ ለዛ እንዘጋጅ። 

ፍቅር ስስታም አይደለም እንደ እኛ፤ ፍቅር ቆንቋና አይደለም እንደ እኛ፤ ፍቅር ማስመሪያም፤ ፐርሰንተም እንደ እኛ አያስፈለገውም፤ ፍቅር ስርክራኪ የጎሸ አይደለም፤ ፍቅር ጥርት ያለ ልቅም አለ ክውን ያለ ጠፍፍ ያለ ንጥረ ነገር ነው። 

ፍቅር ጥራት እንጂ የብዛት ኮረጆ ተሸካሚ አይደለም። ፍቅር የፍሬ እንጂ የሙጃ ቤተኛም አይደለም። ስለሆነም በፍቅር መንገድ ተስፋ በርቶለት ነው የሚገኘው። ፍቅርን የሚመራው መንፈስ ቅዱስ ነውና! …

የፍቅር ሐሤቱ ሰላም ነው!

የፍቅር ሙሴው መንፈስ ቅዱስ ነው!  
የፍቅር ሙሴው መንፈስ ቅዱስ ነው!  
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ!



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።