BBC "በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሱ ያሉ ‘የጅምላ ጭፍጨፋዎች’ ሆን ተብለው እየተፈጸሙ እንደሆነ የአውሮፓ የፍትሕና ሕግ ማዕከል የተባለ ድርጅት አስታወቀ"
https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n10p0elr7o በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሱ ያሉ ‘የጅምላ ጭፍጨፋዎች’ ሆን ተብለው እየተፈጸሙ እንደሆነ የአውሮፓ የፍትሕና ሕግ ማዕከል የተባለ ድርጅት አስታወቀ የፎቶው ባለመብት, Getty Images 2 ግንቦት 2024 የአውሮፓ የፍትሕና ሕግ ማዕከል የተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት “ድምጽ አልባው የአማራ ሕዝብ ስቃይ በኢትዮጵያ” በሚል አርዕስት ባወጣው ሪፖርት በክልሉና ከክልሉ ውጭ ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ዘርዝሯል።በአውሮፓ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ላይ የሚሰራው ማዕከሉ የአገሪቱን የረጅም ዘመን ታሪክና የተወሳሰበ የፖለቲካ ስርዓት ቃኝቶ ሪፖርቱን የሚጀምር ሲሆን፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ ጉልህ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ጨምሯል ብሏል።በግጭቶች የሚባባሰውና በዋናነት በአማራ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዓለም አቀፍ ትኩረትን ማግኘታቸውን የሚጠቅሰው ሪፖርቱ፤ በተለይ ግን በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመው በደል የጥልቀቱን ያህል በቂ ሽፋን አያገኝም ብሏል። መቀመጫውን ፈረንሳይ ያደረገው እና ከአውሮፓውያኑ 2007 ጀምሮ በተባበሩት መንግሥታት ልዩ የአማካሪነት ስፍራ እንደተሰጠው የጠቆመው ማዕከሉ ይህን ክፍተት ለመሙላት በአማራ ማሕበረሰብ ላይ እየደረሰ ነው ያለውን በደል በደንብ በመፈተሽ ሪፖርቱን ስለማውጣቱ ጠቅሷል።የሪፖርቱ ግኝት በአማራ ሕዝብ ላይ አሳሳቢ፣ ሰፊና የተያያዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እተፈጸሙ እንደሆነ ጠቁሟል። ለዚህም አሁንም ድረስ እተፈጸሙ ናቸው ያላቸውን ጥሰቶች የሚያነሳ ሲሆን፤ እልቂቶች፣ ያለ ፍርድ ግድያዎች፣ የድሮን ጥቃቶች፣ በኃይል ማፈናቀል እና የጅም...