2.05.2020 የት ላይ ነን? ጥያቄው ሁላችንም ይመለከታል።

 

 

 
የት ላይ ነን? ጥያቄው ሁላችንም ይመለከታል።
ከእንግሊዝ አገር ከቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ያጋራሁት ልብ የሚነካ የነርሷ የመጨረሻ ቃል ልቤን መሰጠው እና እራሴንም ጠዬቅሁት። የሌላው አገር ሁሉም የተደራጀ ሆኖ መንግሥትም እያላቸው ኮሮና ነው አሁን አገር እዬፈታ ያለው። እኛ ሁሉ የሌለንስ?
የት ላይ ነን ሞት እንዲህ በሆነ ሁኔታ በዬሰከንዱ እዬፈተነን ለመሆኑ እኛ የት ላይ ነው። ማንስ አለን ለጋህዳዊው ዓለም መኖር? የዶር አብይ መንግሥትስ የት ላይ ነው? ምን እዬሠራ ነው።
ያው ይህ እንዲሆን ቀድሞ የሰራው ነገር በሲነሪትም በመደበኛ ዕውቀትም ይበልጠኛል ያለን ዶር አንባቸው መኮነን አስወግጿል።
ህልሙ ምዕራብውያኑና አውሮፓውያኑ ተፎካካሪ አሳተፉ እንዲባል ኢዜማን አማራ ክልልን ወክሎ እንዲወጣ ማድረግ ነበር። አልተቻለውም።
ምን እዬሆነ ነው?
የመስቃ ዱላውስ እስከመቼ ነው? ይህ ሁሉን ሰብዕና አንደርማይን የማድረጉ ሂደት ለዚህ ወቅት እንደ ቢታሚን ቢ ተቆጠረ ይሆን?
ለመሆኑ እኛስ እኔን ብቻ አድምጡ የሚለው ብቸኛው አራጊ ፈጣሪ ዱለኛው የአብይዝምን መታበይ፣ ማፌዝ፣ ዱላ፣ መስቃ እንዴት እናዬዋለን? ሥርዓት የለም። የመንግስታዊ ለቦታው የሚሰጥ። ልቅ ሰብዕና።
ገራሚው 60 አመት ሙሉ ፖለቲካ ድርጅት ስንፈጥር፣ ስንስረው ስንበትነው ኖረን ዛሬ ይህን ዱለኛ ሥርዓት የመተካት አቅም ከዜሮ በታች ሲሆን ህይወታቸውን የሰጡት ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ እና ቤተሰቦቼን አስቤ በውነት አነባሁኝ።
በቃ በድፍረት አገር ለመምራት የሚያስችል ቁመና ላይ አይደለንም ይላሉ ተፎካካሪዎች። ትውልዱ አያሳዝንም በዬዘመኑ የከፈለው አሁንም ያላባራው መስዋዕትነትስ ከዬት ይጠጋ?
አሁን ትናንት የተፈጠረ ይህ የጨረቃ ቤት ብልፅግና ፓርቲ ሆኖ ይህን ያህል መስቃውን ሲያወርደው እልሁ፣ ቁጭቱ ፖለቲከኛ ነኝ የሚለውን ሁሉ አስተኝቶት አድሮ ይሆን?
አቅሙን አውቆ አንተው ብታድነኝም ብትገድለኝ ያለውን የግንቦቱን ኢዜማ አይመለከትም ሃሳቤ። ደግ አደረገ የሌለውን የት ያመጣዋል። ቅባም አልተሰጠውም። ለዚህ ነው ዕድሜ ልኩን በአዳዲስ ሙሽራ ሥሞች እዬተሞሸረ የሚንገጫገጨው።
ድሮም ያለ አቅሙ የነበረ ሲሆን ሥርዓት ያለው ቢሮዊ መስተዳድርን ያልፈጠረ በቀዘቀዘ ቁጥር አዳዲስ ለብታዎችን እያሟሟቀ በግጭት፣ በህውከት፣ ሌሎችን በመፈረጅ፣ በማሳቀቅ፣ በማክሰም በመዋጥ ጊዜውን መፍጀቱ ቀደም ባሉ ዓመታት ስለሞገትኩት ደረጃውን አውቆ እጁን መስጠቱ ወሸኔ ነው። ተስማምቶኛል። ሁለት ቦታ በምፅዋት ካገኜ ይበቃዋል። ለጥ ብሎ ሰግዶ ሲታገለው ከኖረ ድርጅት ከኢህአዴግ እርሾ።
እርግጥ ነው እጁን የሰጠለትም ቢሆን ከእሱ የሚሻል አቅምም ክህሎትም ግን የሌለው መሆኑ የእሱን የበታችነት ስሜት በውል እንድንመረምር መንገድ ይጠርጋል። መደቡ ከእነ አቶ ትዕግስቱ አወሉ ጋር ሆኖ አረፈው። ማህከነ!
ግንቦት 7 በሰራው ሴራ መካቹን ዶር አንባቸው መኮነን እንዲወገድ ካስደረገ በኋላ፣ አላረፈም። የሚገርመው እራሱ ፍርስራሹ ላይ ሆኖ እዬቆዘመ አብን እንደለመደበት ለማፍረስ፣ በቅርቡ ባልደራስ ተፈጠረለት እሱንም ለማክሰም መንገታገቱ ምርኮኝነት ለሁላችንም ሎተሪ ያውጣ የሚለው የቸከ የመነቸከ መንገዱ ሲታሰብ ውሽክን ይሸለማል።
የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ በ60 አመት ውስጥ እንዲህ ጥቃት የሚያወጣ የተደራጀ፣ ተቋማዊ የሆነ አሰባሳቢ ድርጅት፣ መንፈስ ርዕዮት የሌላት ሆኖ ከማዬት በላይ ሞት የለም። አሁንም ሽራፊው ኢህአዴግ ከእኔ ወዲያ ላሳር ነው እያለ እዬፎከረ ነው። ዝርክርክ።
ግን የት ላይ ነው ያለነው?
የዶር አብይ ጆሮዎች ልብ የተገጠመላቸው ምርጥ ዘሮች ስብሰባ በዱላ ሲጠናቀቅ እኔን የተሰማኝ ለእያንዳንዱ ተሰብሳቢ የሬሳ ሳጥን ተዘጋጅቶለት በቁሙ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከተቆለፈ በኋላ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ እንዳሽካኩ ነው። ለዚህ ነው እኔ አብይወለማ መንገዱ የመቃብር ሥፍራ ነው የምለው።
አሁን የጨረቃ ቤት ብልፅግና ፓርቲ ሆኑ አሳታፊ ሰብሳቢ ሲባል አይገርምም? በዬትኛው ጉባኤ፣ በዬትኛው ማዕከላዊ ምክር ቤት፣ በዬትኛው አዲስ በመለመላቸው አባላት እና አካላት ነው ይህን ያህል ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው። ከእሱ ይልቅ የግንቦቱ ኢዜማ የኦነጉ ብልፅግና ዬእግር ሚዜው ፕሮሲጅራል የሆኑ የፓርቲ የአደረጃጀት መርሆችን ተከትሏል።
ወገኛ ናቸው ዶር አብይ አህመድ።
የአዲስ ፓርቲ መስራችነት ዕውቀት ይጠይቃል። በዚህ መቼም እኔን ሞግተው መርታት አይቻላቸውም። ጉራቸውን በመርኽ በወቅቱ በዓናቱ ስለዘቀዘቅኩት። እሳቸውን ብቻ ሳይሆን ምርጫ ቦርዳቸውንም።
የሆነ ሆኖ ከኢህዴግ ዚታ ወደ ብልፅግና የገለበጧቸውን አባላት የባለ ራዕዩን የሄሮድስ መለስ ዜናዊ የጡት ልጆች ተሸክሞ እንዲህ ቦታ አይብቃኝ ብሎ መፎግላት ጎንደሮች ለማያውቅሽ ታጠኝ ይሉታል።
ለመሆኑ ከሳቸው ውጪ አንድ ሌላ ሰው ማቅረብ ይችላሉ ሞጋች? አዲስ ማለቴ ነው ግርፈ ህወሃትን እነ አቶ ዛዲግ አብርኃምን ማለቴ አይደለም። እሳቸው ፁሁፍ እዬበተኑ አገርን ይወኩ።
ሌላ ኦርጅናል የኦነጉ ብልፅግና የፈጠረው። የሚገርመው በኢህአዴግ ግዚ የተከወነው ሁሉ ብልፅግና የከወነው ይላሉ። መጀመሪያ እራሱን ችሎ ይቁም። ተቃዋሚዎች አገር የገቡት በዶር አብይ መልካም ፈቃድ አይደለም። ለሥልጣንም የበቁት በራሳቸው ጥረት አይደለም።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን ብስሉ ጉዳይ ማኒፌስቶውም፣ መዋቅሩም፣ ህገ መንግሥቱም ህወሃት ሠራሽ ነው። በደመቀው ምጣድ ገልብጦ የራስን አቅም አግንኖ አውጥቶ የበቃሁ ነኝ ማለት ያሳፍራል። እግዚኦ ስለእርስዎ።
ይህን በሚመለከት የጨነገፈ ሂደት በሚገባ ስለወቃሁት እዚህ ላይ ገትቼ ሰብዕናውን ለማስገሰስ ለሚሄደው ተስፈኛ ተሰብሳቢ ግን የትውልዱ መርግ ዕዳ ስለመሆኑ አጠይቄ በዚህ ላቁም።
እ። የረሳሁት ህወሃትን ሲተቹ እሳቸው በበላይነት የሚመሩት ኦዴፓስ የትኛውን ድርጅት ይሆን ያሳተፈው?
እሳቸው እራሳቸው መሰብሰብ ይችላሉን? ከአንቦ በኢሊኮፍተር መመለሳቸውን፣ ሐረር ላይ ምህረት መጠዬቃቸውን እረሱትን? ወገኛ ናቸው።
ከሳቸው የተሻለ ይህ ችግር እንደሚመጣ አውቆ የመፍትሄ መንገድ የቀረፀው አብሮነት ሰነዱን አንብቤዋለሁኝ ይመሰገናል።
በልተዛነፈ የፖለቲካ አቅም፣ ቀጥ ባለ የጠራ መስመር፣ ብቃት ባለው የሰከነ ትንበያ ከፖለቲካ ሊሂቃን ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ከሙሁራን አንባ ዶር ደረጀ ዘለቀ አገር ቤት ትውልድን የሚያተርፍ ደፋር የሆነ የፖለቲካ አቅም እንዳላቸው አይቻለሁኝ።
በሌላ በኩል የዶር አብይ አህመድ ጥልቅ ብቃት እና ወሳኝ እርምጃ ብዬ ቡማይናወፅ ሁኔታ እማመሰግናቸው አቶ ሙስጠፌን ያመጡበት መንገድ ብቻ ሳይሆን ስኬታማም ነው።
አብይን ያመነ ጉም የዘገነ ነው እንጂ ካላጠፏቸው አቶ ሙስጠፌ አገር የመምራት ሙሉ አቅም እንደ ኢንጂነር ይልቃል፣ እንደ ዶር ደረጀ ዘለቀ አላቸው ብዬ አምናለሁኝ። ጠቅላይ ሚሩ ሁሉም ቀውሰኛ እኔ ብቻ አዋቂ ቢሉም እኔ ከተከታተልኳቸው ፖለቲከኞች ቋሚ በሆነ ዲስፕሊን ይህን ታዝቤያለሁኝ። ተስፋ አለ። ድፍንም፣ ድንብልብልም አይደለም።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
የሚያሸብር እራስ ወዳድ ሳይሆን አይዟችሁ የሚል መሪ ፈጣሪ ይስጥ። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።