ልጅነታቸው የተዘረፈ። ወላጅ አልባ ልጆች።
ልጅነታቸው የተዘረፈ። ወላጅ አልባ ልጆች።
ግን ወላጅ የሆኑ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች የእድሜልክ ድካምን አልቦሽ ያደርገዋል። በዚህ ውስጥ ኃላፊነት እና ተጠያቂነቱ ለሁሉም ስለሁሉም ይሆናል። ትውልድን አጀንዳው ያላደረገ የኢጎ ድርድር ውጤቱ ይህ ነው። የሚገርመው ይህ መከራን በመምህርነት ለመቀበል ጋዳ መሆኑ ነው። ለአንድ ፖለቲከኛ ትውልድ አጀንዳው ካልሆነ???
ልጅ መሳይ መኮነን ጠቅላይ ሚር አብይን ደግፌ የተጋሁበት ዘመኔ ተቆርጦ ይውጣልኝ ሲል በምሬት ከኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ጋር በነበረው ቆይታ ሲገልጽ ሰማሁ።
ልጅ ሞገስ ዘውዱ በሃሳብ ገበታ ሚዲያው ትናንት 2/05/2024 አማራ የህልውና ትግል የለበትም እያለ ሲሞግት ነበር እና የፍትህ የነፃነት ያለውንም እለፈኝ ብሎ ከእንግዲህ በአማራ ጉዳይ እንቅፋት አልሆንም እራሴን አገላለሁ ከሚል እድምታ ላይ ትናንት ደረሰ። ገርሞኝ ደግሜ አዳመጥኩት።
ሁለቱን ለናሙና ወስደን አጋ ተለይቶ በተበተነ ፍላጎት፣ በቆዬ ቂም እና የማራቅ፣ የማራራቅ ፖለቲካ ቆይታው እንደምን ታርቆ ለእነኝህ ልጆች እንድረስ??? የህሊናው ቡርሽ መቼ ይፈቀድለት???
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ሥርጉትሻ 2024/05/03
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ