ልጥፎች

? የመጨረሻው ዳርቻ የት ነው?!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ? የመጨረሻው ዳርቻ የት ነው?! „አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?“ መዝሙረ ዳዊት ፳፩ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 22.02.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። አሁን አንድ ዜና ሰማሁኝ። ዶር ለማ መገርሳ የለገጣፋው መፈናቀል እንዲቆም ማዘዛቸውናን እና ከህዝቡ ጋር ለመነጋገር መፍቀዳቸውን። እንግዲህ ነፍሰ ጃውርውያን አቶ ንጉሹ ጥላሁን እና አቶ አዲሱ አረጋ አነ ሰውር ሐዋርያቱ ከጎበኙ በኋዋላ የተሰጠ ተስፋ መሆኑ ነው።   ዜናው ዕውነት ከሆነ መልካም ነው። እኔ ግን መጨረሻው ፍርጥርጥ ብሎ መታወቅ አለበት ባይ ነኝ። ብልጥ  የኦሮሞ አክቲቢስቶች ቀስ ብሎ መከወን ነበር እያሉን ነው። ይህ ማለት ሙሉ ለሙሉ መደላደል ከተረጋገጠ በሆዋላ እንደማለት ነው። ያን ጊዜ 5ቱ የኦሮሞ ድርጅቶች መግለጫ ሲያወጡ ያሉትን ነው የደገሙት አሁን መሆን አልነበረበትም ብለውን ነበር። መቻል እኮ መቻል ከተሰጠው ባለመክሊት ብቻ ነው የሚገኘው … እውነት ደግሞ ቀን አይቀጠርለትም ለውጡን እንመራለሁ የሚለው ቲም ለማ ኢትዮጵያዊ ለውጥ ወይንስ የኦሮሞ ኢንፓዬር ለመገንባት ነው እዬተጓዘ ያለው? ይህ በፈጣጣው በግልጥ መንገድ ሊገለጥ ይገባል። ልክ ያጣ ነገር እኮ ነው እዬታየ ያለው። ቲም ጃዋር እኮ ስለመምራቱ ምንም አያጠራጥርም። ራስ እግሩ እኮ ህዝብ የሚያሸብር እና ስጋትን ያዘመተ ድርጊት ነው እዬተፈጸመ ያለው። ፋታ ጠፋ እኮ? ለዛውም ጉድጓዱን ህወሃትን አስቀምጦ። የሚገርመው አገር ጠቅልለው የገቡት የቆረበ ሰው ይመስል አፋቸውን ዘግተው በተረታው መስመር የተሰጣቸውን ብቻ እዬከወኑ ይገኛሉ። ድንቅ ያለኝ ደግሞ ስንት ጊዜ በሚበላው የኮሚሽን አባልነቱኝ እሰዬው ብ...

የስውሩ መንግሥት ዘመንተኞቹ በለገጣፎ።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የስውሩ መንግሥት ዘመንተኞቹ በለገጣፎ። „ ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣   የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ   እኔ ግን በ እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። “ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰ የተባረከ አሜን ለተባረከ ትውልድ! ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። የለውጡ ስውር ውጋት! ·        መነ ሻ።  https://www.youtube.com/watch?v=WurKLDQ_GoA አቶ ንጉሱ ጥላሁንና አቶ አዲሱ አረጋ በለገጣፎ ጉብኝት አደረጉ እኔም ያልኩት እኮ ይኸው ነው። አጃን ነው የወቅቱ መሪ ነው ያልኩት። የመንፈስ ጠላፊዎቹ እነሱ ናቸው። ከዚህም ላለፈ ጉዳይ ቢያስኬድ ይቻላል። ቀድሞ መገፋት ያለበት ተገፍትሯል። ጠርጣሬ እንደሆነ አፈር ሆኗል እንደ ወጣ ቀርቷል። ሌላም ቀጣይ ይኖራል። ባለቤት የሌለው ህዝብ እዬሸኙ ዝም።  የሆነ ሆኖ ዛሬ ፋና እንደዘገበው „ ጃ“ ሲቀር „አ“ እና „ን“ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል ይላል ፋና ከሰቆቃው ውቅያኖስ ጨላልፎ። ይህን ነገር እጅግ በቀደመ ሁኔታ ተቸክችኳል። አድማጭ የለም እንጂ። የህፃናት የሰቆቃ ዕንባ የናፈቀው፤ የእናቶች የማህጸን ደም ዕንባ  ለሚያሰኘው ይህ እርካታ ነው። ጉዳዩ እና ዓላማው በዚህ መከራ ውስጥ በዚህ ጨለማ ውስጥ መከራን እዬመነዘሩ ፌስታ ነውና። የኢትዮ...

አዝነን አዝነን እኛም ገርጥተን ሀዘን ሆነን አረፍነው።

ምስል
አዝነን አዝነን እኛም ገርጥተን   ሀዘን ሆነን አረፍነው። „አቤቱ ለምን ርቀህ ቆምክ?“ ምዕራፍ ቁጥር፲፩ ከሥርጉተ © ሥላሴ  Sergute © Selassie  21.02.2019 ከእመ ሲዊዘርላንድ። ግራጫማ መንፈስ ዘመነ ጃዋርውያን እንዲህ አና ብሎ ሲያውጅ አዝንን አዝነን እኛም የጠለሸ ግርጫማ ሀዘን ሆነን አረፍነው ደማችንም ማቅ ለባሽ። ይህ የሆነው ደግሞ ከሐምሌው ዝምታ በኋዋላ የሆነ ነው። ከዚያ በኋዋላ የሚሆነው ሁሉ ብልጭ ድርግም በሚል ናዳና ፈገግታ የዋጀው ነበር። በዛ የዕቀባ፤ የእግዳ ሰሞናት እንጨርሰዋለን ያሉት ነፍስን በፈጣሪ ጥበብ መትረፉ ሌላ ጥርስ አስነክሶ ሌላ ድቅድቅ ትዕይንት ቤተ መንግሥት አካባቢ ያው አፋኙ ቡድን ፈጠረ። አታስታውሱም ውዴቼ አንድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ጉባኤ ላይ አኮ የቀድሞዋ ደልዳለ እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ነበር ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት።  ስለምን ይህ ሊሆን ቻለ ብዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ በወቅቱ … ተወራራሽነት ያላቸው ሰፊ ምልክቶች ነበሩ። ከልቤ ሳዳምጠው በነበረው ጭብጥም ወስኜ የአብይ ዲታ መንፈስ ተጠለፈ ብዬ ጣፍኩኝ። መጣፍ ብቻ አይደለም ሁኔታውን በተደሞ አስቤበትም እንዲያው ለአንድ ዕውቅ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ደውዬ ተናገርኩኝ። በሳምንቱ እሱ እራሱ ኢትዮጵያ መግባቱን ሰማሁኝ። እኔ ኢትዮጵያ ለመግባት ስለመወሰኑ ምንም ዕውቅት አልነበረኝም፤ ግን መተንፈሻ ያጣው፤ ሚስጢር እንዳያወጣ ማዕቀብ የተጠለ በ ት ነፍስ እንዳለ ለሚያውቃቸው አካላት ሹክ እንዲል እና ሁኔታውን በወፍ በር እንዲከተተሉት ነበር ምኞቴ። ምክንያቱም „አክ“ ወሬ በሚል ስጋቱ ብን እንዲል ቅኖች ደግሞ ያን ጥርጣሬ ይታገሉት ስለነበር። የሆነው ግን ያ ዕውነት ነበር...

ዴሞክራሲ ሲቀርጡበት። ሳይቀጥሩበት ሳይቆርጡበት።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዴሞክራሲ ሲ ቀ ርጡበት። ሳይ ቀ ጥሩበት ሳይ ቆ ርጡበት። „ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፤ በመከራቸውጊዜ ግን ተነስተህ አድነን ይላሉ።“   ትንቢተ ኤርምያስ ፪ ቁጥር ፳፯ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie 20.02.2019 ከእም ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ዴሞክራሲ ነጭ ከረሚሎ ነው። ሁሉ ይወደዋል። ሁሉም ይሳሳለታል። ሁለም ሰፍ ብሎ  የትናጋው ማሟሻ  ያደረገዋል። እስታሁን ባለው ዘመን ስልጣንን ፈቅዶ በማስረከብ ኮ/ጎሹ ወልዴን አይተናል። የራስን ክብር ዝቅ አድርጎ ሌላውን ከፍ በማድረግ በዶር ለማ መገርሳ አይተናል።  እንዲሁም ሲነሪቲውም የመሆን መቻል አቅሙም እያለ እሱን እለፈኝ ብሎ ለኢትዮጵያ ሲባል እራስን ገርቶ በመገኘት ደግሞ በአቶ ደመቀ መኮነን አይተናል፤ የህውሃት የቆይልን ተማህጽኖ እያለም ግን በቃኝ ብሎ ሥልጣንን በፍሰሃ በማሰረከብም በአቶ ሃይለማርያም ደስአለኝም አይተናል። እንደ ድርጅትም በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ታሪኩን አሳልፎ በመሸለም እረገድ ብዴን አንደኛ ነው ዲከርድም በጣሽ ነው። ባይሆን ...  ሌላው የተወካዮች ምክር ቤት አብዛኛው እጅ የ108 ድምጽ ተቀብሎ ጠ/ሚሩ በሚሰጡት መመሪያ ሥር ራሱን አስገዝቶም አይተናል ከኮንፌድሬሽኗ ትግራይ በስተቀር። ዴሞክራሲ መራራ መሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ ህውሃት በአካል ያዬታዬበት ዘመን ይህ ነው። ፈተናውን ድርጅቱ ማለፍ አልቻልም።  ወደቀ ። ስለምን በፊትም አልነበረበትምና። 33ቱ አባላቱ የተቃወሙትን፤ በአብዛኛው ድምጽ የጸደቀውን የተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ አሻም ብሎ በድጋሚ ውይይት በማድረግ የበላይ አካሉን ውሳኔ አልቀበልም ሲል ዴሞክራሲ ቀድ...