ልጥፎች

ህይወት የጥያቄ እና የመልስ ጭማቂ ናት በእኔ ፍልስፍና።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ   ብሎግ በሰላም መጡልኝ። ዕለተ ሮቡ ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ በከበቡሽ ቁራሽ እንጀራ በቢሆነኝ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   „ ሰነፍ ሰው ቁጣውን ያወጣዋል ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል። “ ( ምሳሌ 29 ቁጥር 14)   ·        ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ ፈንገጥ ያሉ ዕይታዎቼ የሚቀርቡበት ነው። የሃሳብ ቀን። ከዚህ ቀደም የሠራኋቸው ያደሩ ጉዳዮችን በቋሚነት በዬዕለቱ የምሠራባቸው ዘርፎችን ነው። አሁን ወደ መደበኛው ተግባር።፡ ዛሬ አንድ የራሴ የሆነ ነገር ላቀርብ ፈለግሁኝ። ምን ስለምን ?   ህይወት የጥያቄ እና የመልስ ጭማቂ ናት በእኔ ፍልስፍና። ህይወት እራሷ ጥያቄ እና መልስ ናት። ትጠይቃለች ወይ ትምለሳለች። ህይወት ኑሯዋ ጥያቄና መልስ ነው። ኑሯዋ ብቻ ሳይሆን የመኖሯ ዛይቢያ መተንፈሻ ቧንቧዋ ጥያቄ እና መልሰ ነው። ኦክስጅኗ። እህል አብስሎ ለመብላት እሳት፤ ፈጭቶ ለመብላት ወፍጮ፤ ለመጓጓዝ የየብስ - የሰማይ እና የባቡር መጓጓዣ።   እህል ለማምረት ማረስ - መዝራት - ማረም - ማብቀል - ማጨድ - መከመር፤ መውቃት - በመንሹ መለዬት። ከዛ ማስቀመጫሳ ? ሲባል እንደ አካባቢው ሁኔታ ዕቃ እንዲህ እንዲህ እያለ አቤቱ ህይወት ለራሱ እራሱን እዬጠዬቀ ኑሮውን የሚያቃልል መሳሪያ ፈለሰመ። ፍልስፍናው ምንጩ ህይወት የሚያቀርበውን ጥያቄ ለመመለስ ነው።   ...