ልጥፎች

«ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ግልጽ ደብዳቤ ለዶ/ር ዓቢይ አህመድ አሊ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር

ምስል
«ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ግልጽ ደብዳቤ ለዶ / ር ዓቢይ አህመድ   አሊ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር   ሲያደክሙን ከባጁት ደጋፊወቻቸው ዬተጣፈ ነው። ፍቅር ሲያልቅ ትዕግስት ይሰደዳል። ሙሉ አምስት ዓመት ለወደመው እኛነት ተጠያቂው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ብቻ??? ወይንስ በሙሉ አቅም አፈርጥሞ ጭካኔ እንዲጨፈጭፈን ያስደረገ ቤተ - ደጋፊ? ይቅርታው? ፀፀቱ? ንስኃስ?   «ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ግልጽ ደብዳቤ ለዶ / ር ዓቢይ አህመድ   አሊ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የካቲት 29 ቀን 2015 ዓም (March 8, 2023) ለተከብሩ ዶ / ር ዓቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ ሀገራችን ትውልድና ታሪክ ተሻጋሪ የሆነ ለውጥ ያመጣሉ በሚል ተስፋ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ እርስዎንና መንግሥትዎን እስከዛሬ ድረስ በሙሉ ልብ ድጋፉን በመስጠት፤ ወደእናት ሀገሩ የእርዳታ ገንዘብ በመላክ፤ መዋዕለ ንዋዩን በማፍሰስ፤ በድርቅና በግጭት በመፈናቀል ብዙ ጉዳት የደረሰባቸዉን ዜጎቻችንን በመርዳትና መልሶ በማቋቋም፤ በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በሞያ የተደገፈ ምክር በመስጠትና በቁሳቁስ በማገዝ ዳያስፖራው ለሀገሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ከእነዚህ በተረፈ፣ ለዐባይ የህዳሴ ግድብ ስኬት ገንዘብ በማዋጣትና በዲፕሎማሲው መስክ ድጋፍ በመስጠት ሰፊ የሆነ ያልተቋረጠ እገዛ አድርጓል። ሀገራችን ኢትዮጵያ በሰሜኑ የትግራይ ጦርነት ሳቢያ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ በገባችበት ወቅትም ዳያስፖራው ከእርስዎ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ከመከላከያና የ...