"አዲሱ የዩኬ ጠ/ሚ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅድ ተግባራዊ አይሆንም አሉ"
"አዲሱ የዩኬ ጠ/ሚ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅድ ተግባራዊ አይሆንም አሉ" • https://www.bbc.com/amharic/articles/cq5x4rn573yo 7 ሀምሌ 2024 «አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የወጣው ሕግ “የሞተ እና የተቀበረ ነው” በማለት ዕቅዱ ተግባራዊ እንደማይሆን አረጋገጡ። «የሌበር ፓርቲ መሪ በቀድሞው የዩኬ ወግ አጥባቂ ፓርቲ መንግሥት የቀረበውን ስደተኞችን “በሕገ-ወጥ መንገድ” ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅድን እንደሚያስቆሙ ተናግረዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተደረገውን ምርጫ ያሸነፈው ሌበር ፓርቲ እስካሁን አገሪቱን 310 ሚሊዮን ፓውንድ ያስወጣውን ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅድን እንደሚሰርዝ ሲገልጽ ቆይቷል። ሰር ኪር ከጽህፈት ቤታቸው ፊት ለፊት ሆነው በሰጡት መግለጫቸው “የሩዋንዳው ዕቅድ ገና ሳይጀመር የሞተ እና የተቀበረ” ሲሉ ዕቅዱን ተችተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕገ-ወጥ ስደተኞችን ፍልሰት የሚገታ የተሻለ ያሉትን ዕቅድ መንግሥታቸው እንደሚያስተዋውቅም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ መንግሥት ተግባራዊ ያደረገው ዕቅድ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዩኬ ከሚገቡ ስደተኞች መካከል 1 በመቶ ብቻ የሚሆኑትን ወደ ሩዋንዳ የሚልክ ስለነበረ ጨርሶ ውጤታማ የሚሆን አይደለም ብለዋል። አዲሱ የሌበር መንግሥት ይህን ዕቅድ ውድቅ ማድረጉ በአገሪቱ ላይ የሚያደርሰውን የገንዘብ ኪሳራ መጠን እስካሁን ገልጽ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪም በቀድሞው አስተዳደር ወደ ሩዋንዳ ለመላክ በዝግጅ ላይ የነበሩ 52 ሺህ ስደተኞች ዕጣ ፈንታ ገልጽ አይደለም። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ስደ...